Get Mystery Box with random crypto!

በዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ እንደማይደረግ ተገለፀ የትምህርት ሚኒስቴር | እንደወረደ ®✔

በዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ እንደማይደረግ ተገለፀ

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ የጸጥታ ችግር አጋጥሞ በነበረባቸው አካባቢዎች የተገኘው ውጤት ከሌላው ጊዜ የተለየ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ዘንድሮ በ43ቱ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከ187 ሺ በላይ ተማሪዎች ይገባሉ ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በበኩላቸው በእርማት ወቅት የነበሩ ስህተቶችን በወቅቱ አስተካክለናል፡ የሚሻሻል የነገር የለም ብለዋል።

@endewerede1