Get Mystery Box with random crypto!

እንደወረደ ®✔

የቴሌግራም ቻናል አርማ endewerede1 — እንደወረደ ®✔
የቴሌግራም ቻናል አርማ endewerede1 — እንደወረደ ®✔
የሰርጥ አድራሻ: @endewerede1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.71K
የሰርጥ መግለጫ

Broadcast & media production company
Addis Ababa, Ethiopia 🇪🇹

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-09 18:17:20
በደላንታ ወረዳ በደረሰ እሳት አደጋ 52 ቤቶችና 1 መስጊድ ሙሉ ለሙሉ ወደሙ

በደላንታ ወረዳ፤ 16 ቀበሌ ሰንበሌጥ ቆላ ልዮ ቦታው ሸንቦቆ ጉጥ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ትናንት የካቲት 29 ቀን 2014 ከቀኑ 5:30 ላይ በጥንቃቄ ጉድለት በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 52 ቤቶችና 1 መስጊድ ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተገለፀ።

በመሆኑ አሁን ላይ እኒህ ጉዳት የደረሰባቸው ህብረተሰቦች የዕለት ምግብና ልብስ የሌላቸው በመሆኑ ሁላችንም ካለን በማካፍል ልንደርስላቸው ይገባል ሲል የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጠይቋል።

@endewerede1
1.3K viewsedited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 20:52:25
1.4K viewsedited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 15:32:45
#Dessie

ደሴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ የሚያስችል ከ605 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ከፌቤላ የዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር በመተባበር በተያዘው ሳምንት ለነዋሪዎች እንደሚከፋፍል የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የዘይት አቅርቦቱ በ 'ሸማች ማህበር' በኩል ይቀርባል የተባለ ሲሆን በገበያው ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል የቁጥጥር ስራም እየተሰራ ነው ተብሏል። 

በከተማዋ በሸማች ማህበራት በኩል የሚቀርበው የዘይት ዋጋ ፡-

1. ባለ 3 ሊትር 290 ብር ከ06 ሳንቲም

2. ባለ 5 ሊትር 474 ብር ከ40 ሳንቲም

3. ባለ10 ሊትር 936 ብር ከ69 ሳንቲም

4. ባለ 20 ሊትር 1 ሺህ 834 ብር ከ66 ሳንቲም

5. ባለ 25 ሊትር 2 ሺህ 277 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

 @endewerede1
1.2K viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 15:32:45
#Kombolcha

የኮምቦልቻ ከተማ ከሶስት ቀን ቡኃላ የምግብ ዘይት ስርጭት ይከናወናል ብሏል።

የከተማው ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት ከ3 ቀን በኃላ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ፅ/ቤቱ ከሚያደርገው የቁጥጥር ሥራ በተጨማሪ አቅርቦቱ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ስለሆነ ነዋሪዎች በተፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት አላስፈላጊ ወጪ እንዳያወጡ አሳስቧል፡፡

የዋጋ ንረትን ለማባባስ ከሚሰሩ ህገወጦች ጋርም ተባባሪ እንዳይሆኑም ጠይቋል።

ከነገ ሰኞ ጀምሮ በሚያደርግ ቁጥጥር ነጋዴዎች የገዙበትን ደረሰኝ እንዲያቀርቡ ካልሆነ ደግሞ አሁን የተጨመረ የዋጋ ጭማሪን ያለምንም ምክንያት ባስቸኳይ ወደ ነበረበት ዋጋ ሽያጭ እንዲመልሱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ማህበረሰቡ ለሚደረገው ሕግ ማስከበር ሥራ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ መቅረቡን ከኮምቦልቻ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@endewerede1
982 viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 15:32:45
994 viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 07:24:58 #Point

የ2014 የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ እስከ እሮብ ድረስ ይፋ ይደረጋል። መቁረጫ ነጥቡ በቅሬታ ማስተካከል እና በአንዳንድ ምክንያቶች እስከ ዛሬ ሳይነገር ቆይቷል።

በዚህ አመት ብሄራዊ ፈተናው በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወሳል። የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥቡ በምን መልኩ መሆን አለበት በሚል ጉዳይም ክርክሮች እንዳሉ ተነግሯል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ የሚነገርበት ቀን በትክክል ያልተገለፀ ስሆን ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሮብ ድረስ ልለቀቅ ይችላል ተብሏል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው የሚማሩ ተማሪዎች ከግማሽ በላይ( 50% እና ከዛ በላይ) ያመጡ ተማሪዎች በድጋሚ ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሲሆን እና አዲስ ነገር ስኖር በፍጥነት የሚናደርሳችሁ ይሆናል።

መረጃ ና አስተያየት ለመስጠት
  @Ethiostudent4bot

ለተጨማሪ የ 12ኛ ክፍል መረጃዎች
@endewerede1
@endewerede1
1.1K views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ