Get Mystery Box with random crypto!

Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

የቴሌግራም ቻናል አርማ emislene — Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ E
የቴሌግራም ቻናል አርማ emislene — Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ
የሰርጥ አድራሻ: @emislene
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.57K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ይፋዊ የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ገጽ ነው፡፡
በዚህ ገጽ
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት የጠበቁ ትምህርቶችን እናሰራጫለን፡፡
- የቅድስት ቤተክስቲያናችን እና የሰንበት ት/ቤቱን እንቅስቃሴ ወቅታዊ መረጃ እናደርስበታለን፡፡
ገጹን ለሌሎችም እያጋራችሁ የቤተክርስቲያናችንን አገልግሎት እናፋጥን፡፡ @EMislene_28Bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 10:31:37
ዜና እረፍት

በደብረ ገሊላ ከመጀመሪያ የሰንበት ት/ቤት ሊቀ መንበርነት ጀምሮ የካቴድራሉ ምክትል አስተዳዳሪ በመሆን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ አባታችን ሊቀ ትጉኀን ሙሉጌታ አሸኔ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ሊቀ ትጉኀን ከካቴድራላችን ውጪ ጀሞ ደብረ ትጉኀን ቅዱስ ሚካኤልን፣ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን እንዲሁም ገዳመ ኢየሱስን በዋና አስተዳዳሪነት አስተዳድረዋል። በመቀጠልም ድካም ሲጫናቸው ተመልሰው ወደ ካቴድራላችን በመምጣት በሕመም ምክንያት እቤት መዋል እስከጀመሩበት ቀን ድረስ በባራኪነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ሊቀ ትጉኀን ነሐሴ 25/2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የአባታችንም ክቡር አስከሬን ወደ ማደሪያው የገባ ሲሆን ዛሬ ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም ለብዙ ዓመታት ሲያገለግሉበት በነበረው በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ይፈፀማል። አባታችን አማኑኤል ለቤተሰቦቻቸው ለወገን ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን ያድልልን ፤በረከታቸው ይደርብን።

t.me/EMislene
686 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:56:08

863 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:36:07
     ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች
ልዩ የውይይት መርሐ ግብር ተሰናድቷል።

#ሌሎችን_ይጋብዙ!

°•°•°•°•°•°•°•°°•°•°•°•°•°•°•°
በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡



የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
542 viewsedited  15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:28:18 ስለ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዕረፍት፦

ከዚህ በኋላ በአዲስ ተጋድሎ ጀመረች። ደናግላን ልጆቿን ሰበሰበችና "ከእግዲህ እርስ በራሳችሁ በመፈቃቀር ኑሩ እግዚአብሔርንም በመፍራት ተቀመጡ" አለቻቸው። ይህንንም ካለች በኋላ በ1079 ደናግል ወይም መነኰሳት አስተዳዳሪ እመ ምኔት ሾመችላቸው። "ከወሰንኩላችሁ ሕግ ወይም ከሰራሁላችሁ ሥርዓት አትተላለፉ ከእግዲህ ከዛሬ በስተቀር በመንፈስ እንጂ በሥጋ አንገናኝምና" አለቻቸው። ይህንንም ተናግራ ከእነርሱ ስትለይ አንዲት መነኵሲት ወይም መበለት ጠርታ ሹል የሆኑ ብረቶች አምጭልኝ" ብላ አዘዘቻትና አመጣችላት።

ከዚያም በእናታችን ክርስቶስ ሠምራ በቁመቷ ልክ ጉድጎድ አስቆፈረችና በውስጡ ዕፀ ከርካዕ ወይም የሎሚ እንጨት አስተከለችበት። ዳግመኛ "ከእግዲህ እግዚአብሔር ይቅር እስኪለኝ ድረስ ከዚህ አልወጣም" ብላ ከጉድጓዱ ውስጥ ገባች። ሦስት የተሳሉ ጦሮች በፊቷ ሦስት ጦር በኋላዋ፣ ሦስት ጦር በቀኝ ጎኗ፣ ሦስት ጦር በግራዋ ጎን ተከለች። መበለቲቱም የፊጥኝ ወይም የኋሊት በገመድ አሰረቻት። ከዚህም በኋላ ስለ ዓለሙ ሁሉ ሕዝብ ይልቁንም ለኢትዮጵያ ሰዎች አጥብቃ ትጸልይና ታዝን ጀመር።

በዚህ ዓይነት ተጋድሎ ሰውነቷን ወይም ሥጋዋን በልዩ ልዩ ፀዋትወ መከራ ስትፈትን ኖረች። ፈጥና በክንፈ ረድኤት ወደ በዓቷ የምትመለስበት ጊዜ አለ። በዚህ ዓይነት ግብር ለብዙ ዘመን ኖረች። በምትሰግድበት ጊዜ ወደፊት ስትል ደረቷን ወደኋላ ስትል ጀርባዋን ወደቀኝ ስትል ቀኝ ጎኗን ወደግራ ስትል ግራ ጎኗን ጦሩ እየወጋት ከቊስሉ የተነሣ ጦሩ የወጋት ፡ገመዱ የከረከራት መላ ሰውነቷ ሸቶ ተልቶ ለዐሥራ ሁለት ዓመት ተጋድሎ አደረገች።

እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታለችና ከጉድጉድ ወጥታ በጣና ባሕር ውስጥ ገብታ እንድትጸልይ የእግዚአብሔር መልአክ አዘዛት ከዚያም በባሕሩ ውስጥ እየጸለየች ሦስት ዓመት ተቀመጠች።

ከሦስት ዓመት በኋላ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በጣና ባሕር ውስጥ ሳለች ለጌትነቱ ክብር ምስጋና የሚገባው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደእርስዋ መጣ። ከሱም ጋር ቅዱሳን ሚካኤል፣ ገብርኤልና ሩፋኤል እናቱ ማርያም መጡ። ዐሥራ አምስቱ ነቢያት ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ሰባ ሁለቱ አርድእት ጻድቃን ሰማዕታት ደናግልና መነኰሳት ሌሎች ሁሉም በየሥርዓታቸውና በየማዕረጋቸው በየነገዳቸው መጡ። ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት አለቃቸው ሕፃኑ ቂርቆስን ተከትለው እንደዚሁም ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት በየነገዳቸውና በየወገናቸው መጡ።

ከነዚህ ሁሉ በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ዳዊት መጥቶ "ልጄ ሆይ ስሚ ጆሮሽን አዘንብይ ወገንሽንና ያባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ውበትሽን ይወዳል እርሱ ጌታሽ ነውና" እያለ በገናውን ይደረድር ነበር። እንዲህም እያለ በሚዘምርበት ጊዜ በዚያ ያሉ ቅዱሳኖች በሙሉ "የእግዚአብሔር ባለሟል ወይም ወዳጅ ይህች ክርስቶስ ሠምራ በእውነት ብፅዕት ነች" እያሉ ዘመሩ።

በዚያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዛሬ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ላስተላልፍሽ መጥቻለሁ" አላት። "ድካምሽ ወደ ዕረፍት ኃዘንሽ ወደ ደስታ ችግርሽ ወደ ብልጽግና ተለውጦልሻል። እውነት በእውነት እልሻለሁ ወይም እነግርሻለሁ በፍጹም ደስታ መታሰቢያሽን ያደረገ በመንግሥተ ሰማያት አስደስተዋለሁ። በችግሩ ወይም በጭንቁ ጊዜ በመታመን ስምሽን ቢጠራ እኔ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ።

የገድልሽን ዜና የሚናገረውን መጽሐፍ የጻፉ ወይም ያስጻፉ እኔ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፍላቸዋለሁ። ቤተ ክርስቲያንሽን የሠራ ወይም ያሠራ ያሣነፀ ወይም ያነፀ እኔ በመንግሥተ ሰማያት ንጹሕ አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ። በስምሽ ለተራበ ያበላ እኔ በዕለተ አርብ ከተቆረሰው ሥጋዬ አበላዋለሁ። በስምሽ ለተጠማው እፍኝ ውሃ ያጠጣ እኔ በዕለተ ዓርብ ከጎኔ በፈሰሰው ደሜ አረካዋለሁ። በዓልሽ በሚከበርበት ዕለት ጧፍ፣ ዕጣን፣ ወይም ዘይት ንጹሕ ስንዴ የመሰለውንም ሁሉ መባ ያገባ መሥዋዕቱን እንደ አብርሃምና እንደ መልከ ጼዴቅ መሥዋዕት አድርጌ እቀበልለታለሁ" አላት

በዚህ ጊዜ "አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ባርያህ ባለሟልነትን በፊትህ ካገኘሁስ አንድ ጊዜ እናገር ዘንድ ፍቀድልኝ" አለችው። እርሱም "ትናገሪ ዘንድ ፈቅጄልሻለሁ" አላት። " አቤቱ ሥጋዬ የሚቀበርበትን ወይም የሚያርፍበት ቦታ ወዴት ታዝዛለህ" አለችው። መቃብርሽ በዚች ጓንጒት በምትባል ደሴት ውስጥ ነው" አላት። "ነገር ግን ሥጋሽ በመሬት ውስጥ ይቀበራል ስላልኩሽ ኀዘን አይግባሽ በኋለኛው ዕለት እኔ አስነሣዋለሁና" አላት።

"አቤቱ እንዲህ ከሆነ መታሰቢያዬ እያደረገ ስሜን እየጠራ በስሜ በታነጸው ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ የሚቀበረውን እስከ ስንት ትውልድ ድረስ ትምርልኛለህ?" አለችው። "እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ" አላት። ይህንም ቃል ኪዳን በሰጣት ጊዜ ፈጽማ ተደሰተች።

ዳግመኛም "ይህች ደሴት እንደ ደብረ ታቦርና ደብረ ዘይት ስሟ የተጠራ ይሁን" አላት። "እንደዚሁ ይህችን ሥጋሽ የምታርፍበትን ቦታ ቀደስኳት አከበርኳት። መጽሐፍ የተናገረውን አልሰማሽምን ቦታ ሰውን የሚያከብረው አይደለም ሰው ቦታን ያስከብረዋል እንጂ። ስለዚህ ነገር ስላንቺ ይቺን መካነ መቃብርሽን ቀደስኳት አከበርኳት። ስሟም ደብረ ፍቅር ደብረ ምሕረት ተብሎ ይሰየም ወይም ይጠራ። እውነት እውነት እልሻለሁ ሥጋሽ ከተቀበረበት ሄዶ መካነ መቃብርሽን የተሳለመ የእናቴን የማርያምን መካነ መቃብር እንደተሣለመ ይቆጠርልታል። እውነት እውነት እልሻለሁ አንቺን ያከበረ ሁሉ እኔ በሰማያዊ መንግሥቴ አከብረዋለሁ። አንቺን የወደደ ወይም ያፈቀረሽን እኔ አፈቅረዋለሉ።

ዳግመኛም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ይህ የዛሬው በዓልሽ የደስታና የተድላ ቀን ነው" አላት። ይህንንም ብሎ በብዙ ወገን ወይም ሠራዊት ላይ ሾማት። "ክብርሽ ከአሮንና ከሙሴ፣ ከጴጥሮስና ከጳውሎስ፣ ሰይጣንን ድል ከአደረገው ከሕፃኑ ቂርቆስ፣ ከእንጦንስና ከመቃርስ፣ ከፀሐየ ልዳ እየተባለ ከሚጠራ ከጊዮርጊስ ጋር ክብር ጋር ትክክል ነው" አላት።

በደብረ ጽዮን ከሊቀ ዲያቆናት እስጢፋኖስ ጋር ትዘምሪ ዘንድ በክብር ተካከልሽ። በእውነት አንቺን የሚያፈቅሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው" አላት። ነቢዩ ዳዊት "አቤቱ እግዚአብሔርን ከሚያከብሩ ወይም ከሚፈሩ በስተቀር በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል በተቀደሰውስ ተራራ ላይ ማን ይኖራል" ብሎ ተናግሯልና። ስለዚህም አንቺን የሚያከብሩ ሁሉ አንቺ ካለሽበት ቦታ ገብተው ከአንቺ ጋር ይደሰታሉ"።

ከዚህም አምላካዊ ቃል ጋራ በነሐሴ 24 ቀን የአባታች ተክለ ሃይማኖት በዓል የሚከበርበት ዕለት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች። በዚህ ጊዜ የነጎድጓድ ብልጭልጭታ ሆነ ነቢዩ ዳዊት "በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ለእግዚአብሔር እልል በሉ" ብሎ እንደተናገረ የመላእክት ሠራዊትና ጻድቃን ሰማዕታትም ሁሉ እልል እያሉ አመሰገኑ። እርሷም ከነርሱ ጋር እየተደሰተች አመሰገነች። ከዚያም መላእክት ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አድርሰዋት ወይም አሳርገዋት በአሸናፊው በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሰገደች።

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳኗ ይማረን።
582 views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:24:18
እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለታላቁ አባት ለከበረ ሐዲስ ሐዋርያ ለትሩፋትም መምህር ለሆነ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሰን።

መድኃኒታችንም እንዲህ አለው "ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ"። አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ።

ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና ነሐሴ 24 ቀን ዐረፈ። በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ተክለ ሃይማኖት ጸሎት ይማረን ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡



የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
570 viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:56:21
ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔ
‹‹ለበጎ ነው››

በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የአዲስከተማ፤ ልደታ እና ቂርቆስ ክፍላተ ከተሞች ውስጥ ከሚገኙ ሰንበት ትምህርትቤቶች መካከል የገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ኲኲሐ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት፤የደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰ/ት/ቤት፤ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ደብረ መዊ ሰ/ት/ቤት እና የብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስወ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ከደብሩ የስብከተ ወንጌል ክፍል ጋር በጋራ በመተባበር ‹‹ለበጎ ነው›› በሚል መሪ ቃል ሶስት ቀን መንፈሳዊ ጉባዔ አዘጋጅተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ተጋባዝ መምህራን፤ዘማሪያን እና የየሰንበት ትምህርት ቤቱ መዘምራን በጋራ ያገለግላሉ፡፡ እርሶም በዚህ ልዩ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡

ከነሐሴ 22 እስከ 24 በገዳመ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

ከነሐሴ 26 እስከ 28 በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተክርስቲያን

°•°•°•°•°•°•°•°°•°•°•°•°•°•°•°
በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡



የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
935 viewsedited  19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 09:05:21 በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ላለማየት ሳይወለዱ በእናታቸው ማኅፀን 7 ዓመት ከ6 ወር የቆዩት ታላቁ አባት አቡነ አብራኒዮስ

አባታቸው ወልደ ክርስቶስ እናታቸው ወለተ ትንሣኤ የሚባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የተወለዱት በ1624 ዓ.ም ምሥራቅ ጎጃም አካባቢ ልዩ ስሙ እነብሴ ይሁን እንጂ ተጋድሏቸውን ያደረጉትና ገዳማቸውን የገደሙት በዛሬዋ ኤርትራ ውስጥ ነው፡፡ ገዳሙ ኤርትራ ውስጥ ዞባ ድባርዋ ደቂ ድግና በተባለ አካባቢ ይገኛል፡፡ የገደሙት ጻድቁ በ1705 ዓ.ም ነው፡፡

አቡነ አብራኒዮስ የተፀነሱት በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት ነው፡፡ ነገር ግን ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ጻድቁ በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ላለማየት ሳይወለዱ በእግዚአብሔር ፈቃድ በእናታቸው ማኅፀን 7 ዓመት ከ6 ወር ተቀምጠዋል፡፡ በዚህም ወቅት እሳት ልትጭር ከጎረቤቷ የመጣች አንዲት ሴት የአቡነ አብራኒዮስ እናት "የማትወልጂው ምን ሆነሽ ነው?" ብላ ስትናገር ጻድቁ በእናታቸው ማኅፀን ሆነው "…ለምን ክፉ ትናገሪያለሽ?" ብለው መልስ ሰጥተዋታል፡፡ ይህም ቅዱሳን ልክ እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ገና በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ እንደሚመረጡ አንድ ማሳያ ነው፡፡

በርካታ ምእመናንን በሰማዕትነት ከገደሉ በኋላ በመጨረሻም ዐፄ ሱስንዮስ በመቅሰፍት ተመተው ሊሞቱ ሲሉ "ሃይማኖት ይመለስ፣ ፋሲል ይንገሥ" ብለው የቤተ ክርስቲያን ሰላም መልሰው ንስሓ ገብተው ሞቱ፡፡ አቡነ አብራኒዮስም ይህ የቤተ ክክርስቲያን የመከራ ዘመን ሲያልፍና ሃይማኖት ሲመለስ ተወለዱ፡፡ ገና በ5 ዓመታቸው ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍትንና ምሥጢራትን ሁሉ ተምረው ዐወቁ፡፡ በ12 ዓመታቸው መነኰሱ፡፡ ዲቁና ሲሾሙም ጳጳሱ "ገና ሕፃን ነው፣ አሁን አልሾመውም" ሲሉ የሰማይ መላእክት "ይባዋል" ብለው መስክረውላቸዋል፡፡

በልጅነታቸውም መነኰሳቱ ወደ ጫካ ሔደው ዕንጨት እንዲሰብሩ ሲያዟቸው ጌታችን ግን ለአቡነ አብራኒዮስ ኃይል ሰጥቷቸው በነፋስ ሠረገላ እየሔዱ የ6 ሰዓቱን የእግር መንገድ እሳቸው ግን ዕንጨቱን ሰብረው በቶሎ ይመለሱ ነበር፡፡ ይህም ሲታወቅባቸው ውዳሴ ከንቱን ንቀው ከዚያ ገዳም ወጥተው ወደ አቡነ ተጠምቀ መድኅን ዘንድ ሔዱ፡፡ በዚያም በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኋላ አቡነ ተጠምቀ መድኅን "በአንተ ምክንያት ብዙ ነፍሳት ይድናሉ፣ ክፍልህ በዚያ ነው" ብለው አሁን ገዳማቸውን ወደገደሙበት ቦታ (ኤርትራ) ላኳቸው፤ ሲመጡም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል እየመሯቸው እንደመጡ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ጻድቁ ወደዚህ ገዳም ሲመጡ በፊት ይቀመጡባት የነበረችው ትልቅ ድንጋይ በተኣምር ከመሬት 7 ክንድ ከፍ ብላ አብራቸው መጥታለች፡፡ ድንጋይዋ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው በክብር ስለተቀመጠች ምእመናን እየዳሰሷት ይባረኩባታል፣ መካኖች ይወልዱባታል፣ ሕሙማን ይፈወሱባታል፡፡

አቡነ አብራኒዮስ በቅዳሴ ጊዜ ጌታችንን በዕለተ ዐርብ እንደተሰቀለ ሆኖ ይመለከቱት ስለነበር በኀዘን በተመስጦ ሆነው ይቆዩም ስለነበር ሕዝቡም "በቅዳሴ ሰዓት ይተኛል" እያሉ ያሟቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ጻድቁ ወደ አካለ ጉዛይ በመሔድ በዘንዶ ላይ አድሮ ይመለክ የነበረውን ሰይጣን በጸሎታቸው አጥፍተው ዘንዶውን ገድለው ሕዝቡንም አስተምረው በንስሓ መልሰው አጥምቀዋቸዋል፡፡ ወደ ታላቁ ገዳም ደብረ ቢዘንም ሲሔዱ 6400 አጋንንትን አግኝተው በጸሎታቸው አጥፍተዋቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት አቡነ አብራኒዮስ "ሰዳዴ አጋንንት-አጋንንት አባራሪ" ተብለዋል፡፡

አቡነ አብራኒዮስ ወደ ሌላ ቦታ ሔደው ሰለዳዋ የምትባል ቦታ ላይ ሆነው ሳለ አንድ ሰው ወደ ገዳማቸው ገብቶ አንዲትን ዛፍ ሲቆርጥ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት አዩት፡፡ ቆራጩም ሰው "ተው አትቁረጥ" የሚል የአባታችንን ድምፅ ሰማ፣ በአካል የሉም ብሎ እምቢ አለ፣ ነገር ግን በመቅሠፍት ተመቶ ወዲያው ሞተ፡፡ በአንድ ዕለትም ልጃገረዶች እየዘፈኑ ሲሔዱ ብዙ አጋንንት በዘፈናቸው ተደስተው አብረዋቸው ሲጨፍሩ አባታችን በመንፈስ ተመልክተው ለልጃገረዶቹ ዘፈን የአጋንንት መሆኑን እንዳስተማሯቸው ገድላቸው ይናገራል፡፡

ለአቡነ አብራኒዮስ ዕረፍታቸው ሲደርስ ክብርት እመቤታችን ተገልጻ "ቤተ ክርስቲያን በስሜ አንጽልኝ" አለቻቸው፡፡ እርሳቸውም ውብ አድርገው በእመቤታችን ስም አነጹ ነገር ግን ፍጻሜውን ሳያዩ በዕለተ ቀኗ ነሐሴ 21 ቀን ዐረፉ፡፡ በዕረፍታቸውም ወቅት ጌታችን ተገልጦ ታላቅ ቃል ኪዳን ሲሰጣቸው "...ዋስ እፈልጋለሁ፣ ዋስ ስጠኝ" አሉት፡፡ ጌታችንም "ሐዋርያት፣ ሰማዕታት፣ ከአንተ በፊት የነበሩ ጻድቃን ያልጠየቁኝን አንተ እንዴት ጠየከኝ?" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "አምላኬ ሆይ! አንተ መሐሪና በጽድቅ ፈራጅ ቃልህም የማይለወጥ እንደሆንክ አውቃለሁ" አሉት፡፡ ጌታችንም "ይሁን የምትሻውን አላሳጣህም" በማለት ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች ክብርት እመቤታችንንና ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ዋስ አድርጎ ቃል ኪዳን ከገባላቸው በኋላ ነሐሴ 21 ቀን 1713 ዓ.ም በሰላም ዐረፉ። ከታላቁ ጻድቅ ከአባታችን አቡነ አብራኒዮስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!።

ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።

በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡



የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
943 views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:50:34 https://vm.tiktok.com/ZMNvQKmcp/
879 views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:47:14 ትክክለኛው መልስ "ቅድስት እናታችን ዜግነቷ ኢትዮጵያዊ አይደለም " የሚለው ነው። ምክንያቱ ደግሞ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ኢትዮጵያዊት ስለኾነች ሲኾን፡ ይህ አረፍተ ነገር የተሳሳተ በመኾኑና ጥያቄውም ትክክል ያልኾነውን ለዩ በማለቱ ነው። የሞከራችሁ ሁላችሁንም እናመሰግናለን።
አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳኗ ይማረን።
973 viewsedited  17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:40:17
' በደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል '
እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት

"ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናቹ"
መዝ118፥26

ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ያስመርቃል።

ዕለተ እሑድ ነሐሴ 29/2014 ዓ.ም

ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ

በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ

ቃለ ወንጌል
ያሬዳዊ ወረብ
ተውኔት
የሽልማት መርሐ ግብር

የቤተ ክርስቲያን ደስታ ደስታችን ነውናማንም እንዳይቀር በዐማኑኤል ስም ተጋብዛችኃል።

"ኢንኅድግ ማኅበረነ እግዚአብሔር ምስሌነ"

°•°•°•°•°•°•°•°°•°•°•°•°•°•°•°
በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡



የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
1.1K viewsedited  20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ