Get Mystery Box with random crypto!

ዜና እረፍት በደብረ ገሊላ ከመጀመሪያ የሰንበት ት/ቤት ሊቀ መንበርነት ጀምሮ የካቴድራሉ ምክት | Egziabher Meslene እግዚአብሔር ምስሌነ

ዜና እረፍት

በደብረ ገሊላ ከመጀመሪያ የሰንበት ት/ቤት ሊቀ መንበርነት ጀምሮ የካቴድራሉ ምክትል አስተዳዳሪ በመሆን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ አባታችን ሊቀ ትጉኀን ሙሉጌታ አሸኔ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ሊቀ ትጉኀን ከካቴድራላችን ውጪ ጀሞ ደብረ ትጉኀን ቅዱስ ሚካኤልን፣ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን እንዲሁም ገዳመ ኢየሱስን በዋና አስተዳዳሪነት አስተዳድረዋል። በመቀጠልም ድካም ሲጫናቸው ተመልሰው ወደ ካቴድራላችን በመምጣት በሕመም ምክንያት እቤት መዋል እስከጀመሩበት ቀን ድረስ በባራኪነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ሊቀ ትጉኀን ነሐሴ 25/2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የአባታችንም ክቡር አስከሬን ወደ ማደሪያው የገባ ሲሆን ዛሬ ነሐሴ 26/2014 ዓ.ም ለብዙ ዓመታት ሲያገለግሉበት በነበረው በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ይፈፀማል። አባታችን አማኑኤል ለቤተሰቦቻቸው ለወገን ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን ያድልልን ፤በረከታቸው ይደርብን።

t.me/EMislene