2022-08-26 09:01:01
ብሒለ አበው
‹ራስህን በሐሰት አትውቀስ ራስን መክሰስ ትህትና አይደለም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው።›
/ቅዱስ ስራፕዮን/
‹‹የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።››
/መጽሐፈ ምክር/
‹‹አንደበቱን ከቧልት ከሐሜት ያየውንም ምሥጢር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኀልዮ ኃጢአት ያርቀዋል።››
/አረጋዊ መንፈሳዊ/
‹‹ ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን፡ ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ።››
/ማር ይስሐቅ/
‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ጥበብ ይለየዋል።››
/አረጋዊ መንፈሳዊ/
‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።››
/አባ እንጦንስ/
‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻለን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለናል?››
/ቅዱስ አትናቴዎስ/
‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ጸጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም። የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢአተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደነደደ ይኖራል።››
/ቅዱስ ሚናስ/
‹‹በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍረዱ። ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።››
/ታላቁ አባ መቃርስ/
‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናለሁ። በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።››
/ቅዱስ አርሳንዮስ/
‹‹ቤተ ክርስቲያን መጠጊያችን ነች። ቤተ ክርስቲያን የኖኅ መርክብ ነች። በውስጧ እንጠለላለን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።››
/ቅዱስ እንድርያስ/
‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከሆነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ፡ከበደል በንስሐ ንጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።››
/አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/
‹‹ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።››
/ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
‹‹የቤተ ክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።››
/ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር።››
/ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/
‹‹ኃጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ፡ኃጢአታችንን እኛ ረስተን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።››
/ቅዱስ እንጦንስ/
በማኅበራዊ መገናኛዎቻችን ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org
1.3K views06:01