Get Mystery Box with random crypto!

Dr. Eyob Mamo

የሰርጥ አድራሻ: @dreyob
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.56K
የሰርጥ መግለጫ

Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 86

2022-09-06 11:59:00
ስለ ተለያዩ በሽታዎች ሲያወሩ እኔም ያለብኝ ይመስለኛል ምን ላርግ?
5.5K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 10:33:55
ጥያቄ፡-

ጤና ይስጥልኝ ዶ/ር እኔ ልቀርፈው ያልቻልኩት ነገሮችን ጀምሮ ያለመጨረስ ትልቅ ችግር አለብኝ ነገሮችን አስቤባቸውና በሙሉ ፍላጎት እጀምራቸውና ቶሎ ይሰለቸኛል።

መልስ፡-

“አንድ ነገር መጀመር የነገሩን ሃምሳ በመቶው እንደማጠናቀቅ ነው” ይባላል፡፡ ብዙዎች ጭራሹኑ አንድን ነገር የመጀመር ችግር አለባቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ነገሮችን የምትጀምር ሰው በመሆንህ ደስ ሊልህ ይገባል፡፡ ከዚያም የቀረውን ሃምሳ በመቶ ስራ ለማጠናቀቅ መጣጣርና ልማዱን የማዳበር ሂደት መጀመር አለብህ፡፡ ለዚህ የሚረዱህን ጥቂት ሃሳች ልሰንዝር፡-

ምንም ነገር ከመጀመርህ በፊት ነገሩ ከውጪ ግፊት የመጣ ሳይሆን አንተው ያመንክበት ነገር መሆኑን እርግጠኛ ሁን፡፡ በውጭ ኃይልና ተጽእኖ ብቻ የተጀመረ በውጭ ኃይልና ተጽእኖ ይቆማል፡፡

በመቀጠልም፣ የምትጀምረውን ነገር ለመቀጠል የሚያበቁህን ነገሮች በሚገባ አጥንተህ በማወቅ ከመጀመርህ በፊት እነዚያ ነገሮች መሟላታቸውን እርግጠኛ ሁን፡፡

እንዲሁም፣ የምትጀምረው ነገር ሁል ጊዜ እንቅፋት ሊያጋጥመው እንደሚችል አውቀህና አምነህ ተቀብለህ ለዚያ የሚመጥን የስነ-ልቦና ዝግጅት ያስፈልግሃል፡፡

በመጨረሻ፣ አንድን ነገር ስትጀምር የመቀጠልህን ጉዳይ በመከታተል “የሚቆጣጠርህን” ሰው አጠገብህ ለማድረግ ሞክርና ለዚያ ሰው ሙሉ ስልጣን ስጠውና በሃላፊነት ይጠይቅህ፡፡

የተለያዩ የሚጀመሩ ነገሮች የተለያዩ ብልሃቶችን ይጠይቃሉ፡፡ ከላይ የጠቀስኩል አጠቃላይ መመሪያዎች ናቸውና ለመከተል ሞክር፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
6.4K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 05:00:00
ቀላል እውነታ!

እጥር ምጥን ያለች እውነታ ላስታውሳችሁ . . .

• አገልጋይ ሆኖ የማያውቅ ሰው ወደፊት አለቃ መሆን ያስቸግረዋል፡፡

• ተከታይ ሆኖ የማያውቅ ሰው ወደፊት መሪ መሆን ያስቸግረዋል፡፡

• ሰራተኛ ሆኖ የማያውቅ ሰው ወደፊት አሰሪ ለመሆን ያስቸግረዋል፡፡

• ልጅ ሆኖ የማያውቅ ሰው ወደፊት አባት/እናት ለመሆን ያስቸግረዋል፡፡

• ጨዋ ዜጋ ሆኖ የማያውቅ ወደፊት ጨዋ የሕብረተሰብ መሪ መሆን ያስቸግረዋል፡፡

ዛሬ እነዚህንና መሰል ቦታዎች ላይ የመቆም እድል ሲያገኙ ሰውንና ሕብረተሰብን የሚያተራምሱ ሰዎች እንደዚያ የሆኑበት ሌላ መነሻ ሊኖር የመቻሉ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ዋናው መንስኤ ግን ትናንትና ከታች ያለመጀመራቸው መዘዝ ነው፡፡

በእነዚህና በመሰል ልምምዶች ውስጥ የማለፍ እድል ዛሬ ስታገኙ በፍጹም አትለፉት፣ ተጠቀሙበት፡፡ በሂደቱ የነገው ታላቅና ጨዋ ሰው ወደመሆን ታድጋላችሁ፡፡

Like & Share, please !!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
7.9K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 05:00:00
የአጭር ርቀት ምልከታ ያለው ሰው

የአጭር ርቀት ምልከታ ያለው ሰው ምርጫና ውሳኔዎቹን ሁሉ የሚያደርገው ከዛሬው ደስታና በእለቱ ከሚያገኘው ጊዜያዊ ጥቅም አንጻር ብቻ በመነሳት ነው፡፡

ስለዚህም የአጭር ርቀት ምልከታ ያለው ሰው እዲህ ይላል . . .

• ለዛሬ ይህችን ልብላና ሌላ ጊዜ የአመጋገቤን ሁኔታ አስተካክላለሁ፡፡

• ለዛሬ ስፖርቱን ልተወውና ሌላ ጊዜ እጀምራለሁ፡፡

• ለዛሬ ሳንቀላፋ ልዋልና ሌላ ቀን በተገቢው ሰዓት የመነሳትን ልማድ አዳብራለሁ፡፡

• ለዛሬ ያለኝን ገንዘብ ልንበሽበሽበትና ሌላ ጊዜ ማቀድና መቆጠብ እጀምራለሁ፡፡

• ለዛሬ ስሜቴን ላርካና ሌላ ጊዜ እታረማለሁ፡፡

• ለዛሬ ከጓደኞቼ ጋር ላሳልፍን ሌላ ቀን ትምህርቴን አጠናለሁ፡፡

የአጭር ርቀት ምልከታ አጭር ጊዜ የሚቆይ ደስታን ይሰጠንና ረጅሙን ዘመናችንን በኃዘን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ ማንነታችን ለጠየቀው ጊዜያዊ ጥያቄ መልስ ይሰጥና እስከወዲያኛው በጥያቄና ግራ በመጋባት እድንኖር ያደርገናል፡፡

በተቃራኒው የረጅም ርቀት ምልከታ ያለው ሰው ከፍተኛ የሆነ ዲሲፕሊን ያለው ሰው ስለሆነ የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ከዓላማውና ነገ ለማከናወን ካቀደው አቅጣጫ አንጻር ነው የሚያደርገው፡፡ ትክክለኛ የሕይወት ዘይቤን ለመኖር ይወስናል! ከዚያም መኖር ይጀምራል!

ዛሬ ከአጭሩ ምልከታ ወደ ረጅሙ ምልከታ የመሸጋገር ውሳኔን እንድታስተላልልፉ ፈጣሪ ያግዛችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
4.3K viewsedited  02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 06:55:22
“አመኔታ”

አንዳንድ ሰዎች ሁሉንም ሰው በጭፍንነት የማመን ዝንባሌ ስላላቸው ሁል ጊዜ እየተጎዱ ይኖራ፡፡ ሌሎች ደግሞ ማንንም ባለማመንና በጥርጣሬ ድንበራቸውን አጥረው ብቻቸውን ይንገላታሉ፡፡

ይህ መጽሐፍ ከጭፍን ጥርጣሬና ከጭፍን አመኔታ ጠርዞች ወጥተን ወደ ንቁ አመኔታ እንዴት ማደግ እንደምንችል በግልጽ ያሳያል፡፡ “እመን፣ ነገር ግን አጣራ!” የሚለውን እውነታ ተግባራዊ ያደርግልናል!

የአብዛኛው ማሕበራዊ ቀውሶቻችን መነሻ ተገቢ ያልሆነን ሰው ካለመጠን ከማመን ወይም ማመን የሚገባንን ሰው አጓጉል ከመጠራጠር የሚመነጭ ነው፡፡ በአመኔታ ጥበብ ማደግ የላቀ የወደፊትን ይሰጠኛል፡፡

ይህ መጽሐፍ የዛሬ እሁድ ንባብ እንዲሆንላችሁ ውጡና ከመጽሐፍ መደብር አግኙት! አንብቡ! እደጉ! ተለወጡ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
5.2K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 05:00:00
ብሩህ ቀን እንዲሆንላችሁ . . .

ቀኑ ሲደመደም፡-

በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ላይ እንዲህ በሚል እሳቤ ቀኑን ደምድሙ፡- በዛሬዋ ቀን የምችለውን ነገር አድርጌያለሁ፡፡ አንዳንዶቹ ነገሮች የተሳኩ እንደነበሩና ሌሎቹ ነገሮች ደግሞ ያልተሳኩ እንደነበሩ አውቃለሁ፡፡ ያም ሆነ ይህ ቀኑ አልቋልና እኔም ቀኑን እደመድማለሁ፡፡ ነገ ሌላ አዲስ ቀን ከአስገራሚ እድሎች ጋር ይጠብቀኛልና ወደፊት እመለከታለሁ፡፡

ቀኑ ሲጀመር፡-

በእያንዳንዱ ቀን መጀመሪያ ላይ እንዲህ በሚል እሳቤ ቀኑን ጀምሩ፡- የዛሬዋ ቀን አዲስ ቀን ነች፡፡ በዚህች አዲስ ቀን ሁሉንም ነገር እንደ አዲስ የመጀመር እድሉም፣ ምርጫውም ሆነ አቅሙ አለኝ፡፡ ባለፈው ስኬት ላይ በመገንባትና ካለፈው ስህተት ትምህርት በማግኘት አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡

አዲስ እይታና የማየት እድል! አዲስ ጉልበት የማግኘት እድል! አዲስ ሰው የመተዋወቅ እድል! አዲስ ሙከራ የመሞከር እድል!

አዲስና ብሩህ ዓርብ ይሁንላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
5.3K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:00:13 ሃሳባችሁን ካልተቆጣጠራችሁ ፍጻሜያችሁ ይሆናል!

ብዙ ሰዎች የሁሉ ነገር መጀመሪያው ሃሳባቸው እንደሆነ ይዘነጉታል፡፡ ስለሆነም የሃሳባቸው በር የሆኑትን ነገሮች በመዝጋት ሃሳባቸውን መቆጣጠር ሲገባቸው ራሳቸውን ክፍት አድርገው በማጋለጥ ሃሳብ ከገባ በኋላ የዚያን ሃሳብ ውጤት ይታገላሉ፡፡

የነገውን ሕይወቴን ዛሬ የመቆጣጠሪያው ቀላሉ መንገድ አእምሮዬን በሚገባ ማሰልጠንና የአስተሳሰቤን ንድፍ መቆጣጠር ነው፡፡ ይህንን ቀላሉን መንግድ ካልተከተልኩኝ፣ የሚቀጥለው ደረጃ ከበድ ይላል፡፡

እሱም በሃሳቡ ምክንያት የመጣውን የስሜት ሁኔታ መታገልና ለመቀልበስ መታገል ይሆናል፡፡ ይህ ስሜት በስኬታማ ሁኔታ በቁጥጥር ስር ካለዋለ ደግሞ ወደተግባር ያልፍና ልማድ ፈጥሮ ማንነቴንና ፍጻሜዬን ይወስናል፡፡

በዚህ ይዤላችሁ በቀረብኩት የቪዲዮ ትምህርት አንድ በቀላሉ የተጀመረና ችላ የተባለ ሃሳብ በየት በኩል አቆራርጦ ፍጻሜዬን እንደሚወስን በሚገባ አብራራለሁ፡፡

ከታች የሚገኘውን የዩቲውብ ሊንክ (Link) በመጫን ይከታተሉ ለሌሎችም ያጋሩ፡፡



6.7K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 05:00:00 የተሸከመህ ሸክም

ገና ከጫጩትነቱ ጀምሮ ብረር ብረር የሚለውና በፍጥነቱ ታዋቂ ለመሆን የሚመኝ ወፍ ነበረ ይባላል፣ ምንጩ የማይታወቅ አፈ-ታሪክ፡፡ እናቱ ከልምዷ በመነሳትና ለእርሱ በመጠንቀቅ ተረጋጋ ትለው ነበር፡፡ እርሱ ግን ፈጽሞ አይሰማትም ነበር፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ሄደና በእርግጥም እንደተመኘው ፈጣን በራሪ ሆነ፡፡

ይህ ወፍ በቃ መብረር ይወዳል፡፡ መብረር ከመውደዱ የተነሳ ማታ ሁሉም በጊዜ ወደጎጆው ሲመለስ አይኑ ለማየት የማይችልበት ደረጃ እስኪመሽ ድረስ ሲበር፣ ሲከንፍ ውሎ እያለከለከ ወደ ጎጆው ይገባል፡፡ ማለዳም ቢሆን ለመነሳት የሚቀድመው ወፍ የለም፡፡ ከእርሱ ዘግየት ብለው የወጡ አቻ ወፎቹን ካልተወዳደርን እያለ ስቃያቸውን ነው የሚያላቸው፡፡ ሁሉንም ግን ይቀድማቸው ነበር፡፡

ይህ ወፍ ሌሎቹን ወፎች ሁሉ የመቅደሙ ሁኔታ ስላላረካው አሁንም ከዚያ በበለጠ ሁኔታ ለመፍጠንና ከእርሱ የላቁ የወፍ ዝርያዎች ጋር ለመወዳደር ምኞት አደረበት፡፡ አንድ ቀን አንድ ሃሳብ ብልጭ ያለለት መሰለው፡፡ ብዙ ካሰበ በኋላ፣ “ችግሬ ክብደቴ ነው” ወደማለት ሃሳብ መጣ፡፡ ክብደቱን ለመቀነስ ሲል በየቀኑ አንድ ላባ ከክንፉ ላይ በመንቀል ፍጥነቱን መለካት ጀመረ፡፡ የተወሰኑ ላባዎች ሲነቅል እውነት ይሁን ወይም የስነ-ልቦና እይታ ያመጣው ምልከታ ይሁን ባይታወቅም ፍጥነቱ የጨመረ መሰለው፡፡

ይህ ተግባሩ እንደማያዛልቀው እናቱ በየቀኑ ብትመክረውም፣ “እንደናንተ ያለ ወደኋላ የቀረ አመለካከት ያለው ሰው ነው የጎተተኝ” በማለት አልሰማ አለ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ መብረር እስከሚያስቸግረው ድረስ አብዛኛዎቹን የክንፉን ላባዎች ነቀላቸው፡፡ ከዚያ የተከተለውን ውጤት መገመት ቀላል ነው፡፡ እውነታው የገባው በኋላ ነው፡፡

ለካ ሸክም ሆነብኝ ያለው ነገር እሱን የተሸከመው ነው . . . ሸክሜ ነው ያለው ነገር የመብረሪያ አቅሙ ነው . . . አዎ ሸክም ነው፣ ነገር ግን የጉልበት ምንጭ ነው . . . አዎ ሸክም ነው፣ ነገር ግን ወደከፍታ ለመብረር የተነሳበት መነሻና እንደገና የማረፊያ ምክንያት ነው፡፡

• ይህ የልጆች የሚመስል ታሪክ “ሸክም ሆናችሁብኛል” በማለት ቀድሞውኑ የጉልበት ምንጭ የሆኑትን ቤተቦቹን ነቅሎ የጣለውን ሰው አስታወሰኝ፡፡

• ታሪኩ ውጪ ለተከፈተለት የስኬትና የተቀባይነት እድል መነሻው ቤተሰቡ፣ ትዳሩ፣ ልጆቹና የቅርብ አጋሮቹ ሆነው ሳሉ፣ የሚደርስበትን የስኬት ከፍታ ሲያይ መነሻውን እንደሸክም በመቁጠር ጎድቶ የተነሳውን ሰው አስታወሰኝ፡፡

• ይህ የወፉ ታሪክ ጡንቻ ሲያወጣ፣ አይኖቹ ሲገለጡ፣ ዙሪያውን መመልከት ሲጀምርና ለጋ አቋሙን የሚያደንቁለት ሲበዙ እዚያ ያደረሱትን ወላጆቹንና አሳዳጊዎቹን እንደሸክም የቆጠረውንና ከሕይወቱ ነቅሎ የጣላቸውን ወጣት አስታወሰኝ፡፡

• ይህ ቀላል የሚመስል ታሪክ ተሸክመውት ሳለ እርሱ ግን እንደሸክም የቆጠራቸውን ከእሱ ለየት የሚሉትን የሃገሩን ሰዎች ገንጥሎ ለመጣል የሚቃጣውን የህብረተሰብ ክፍል አስታወሰኝ፡፡

የተሸከመህን ሸክምህን አትጣል!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
588 views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 04:59:00
የተሸከመህ ሸክም
594 views01:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 05:00:00
ቀንደኛው የግንኙነት ቀውስ ምንጭ!

ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት አብዛኛውን ቀውስ በመፍጠር ከሚታወቁ ነገሮች መካከል አንዱ የተዛባና የሌለ ነገር የመጠባበቅ (Unrealistic Expectation) ሁኔታ ነው፡፡

1. ሰዎች ከእናንተ የሚጠብቁት ነገር ሲዛባ፡፡
እናንተ በፍጹም በሃሳባችሁ ውስጥ የሌለን ነገር ሰዎች ከእናንተ ጠብቀው ሲቀርቧችሁ የግንኙነት ቀውስን ስለሚፈጥር ውስጥን ያውካል፡፡ ሰዎች ከእናንት ምን እደሚጠብቁ ሙሉ ለሙሉ የመቀጣጠር አቅም ባይኖራችሁም፣ በተቻላችሁ መጠን የግንኙነትን ሁኔታ ግልጽ ማድረግ ቀውሱን ይቀንሰዋል፡፡

2. እናንተ ከሰዎች የምትጠብቁት ነገር ሲዛባ፡፡
ሰዎች በፍጹም በሃሳባቸው ውስጥ የሌለን ነገር ከእነሱ ጠብቃችሁ ስትቀርቧቸው የኋላ ኋላ የግንኙነት ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም፡፡ ከሰዎች የምትጠብቁትን ነገር የመቆጣጠር አቅሙ ስላላችሁ ከሰዎች ምን እንደምትጠብቁ ለይቶ በማወቅና ሚዛናዊ በማድረግ ቀውስን መቆጣጠር ትችላላችሁ፡፡

አንድ ሰው ከሌላው ሰው እንደሚያገኝ የሚጠባበቀው ነገር በውስጡ የሌለን “እውነታ” የመፍጠር አቅም አለው፡፡ ይህ የሌለ “እውነታ” እንደሌለ የሚገለጽበት ቀን ሲደርስ ነው ቀውሱ የሚጀምረው፡፡

ሰዎች እንዲሆኑላችሁና እንዲያደርጉላችሁ የምትጠብቁትን ነገር ሚዛናዊ አድርጉ፤ ከእወነታው ጋር አጣጥሙ፡፡ መሆንና ማድረግ የማትችሉትን ነገር ሰዎች ከእናንተ በመጠባበቅ የኋላ ኋላ ቀውስ እንዳይፈጠር ደግሞ ለሰዎች የምታሳዩትን ሁኔታ በጥበብ ማድረግን አትዘንጉ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
2.6K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ