Get Mystery Box with random crypto!

Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dotcomtvshow
ምድቦች: ሽያጭ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.01K
የሰርጥ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሰረፀባት፣ያደገች ፣የበለፀገች እና የዓለም ህዝብ ሁሉ የሚመርጣት ምርጥ ሀገር እንድትሆን እመኛለሁ!!
t.me/dotcomtvshow

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-28 17:29:06
ቻይናው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ለተከታዮቹ አልኮል አጠጣጡን እያሳየ ህይወቱ አለፈ

በቻይና በማህበራዊ ሚዲያ የቀጥታ ስርጭቶች ላይ መወራረድ እየተለመደ መጥቷል። ግለሰቡ ሕይወቱ ያለፈው እስከ 60 በመቶ የአልኮል ይዘት ያለው ሶስት ጠርሙስ መጠጥ ከጠጣ በኋላ ነው።

#ጥያቄ

በሀገራችንስ ቲክቶክ ላይ እንዲህ አደገኛ ነገር ምን አስተውላችኋል? ቲክቶክ ላይ የታዘባችሁት አደገኛ ነገር ካለ አካፍሉን።እንማማርበት!

ምንጭ፦ https://am.al-ain.com/article/influencer-dies-live-streaming-drinking



የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
2.9K viewsBahiru Abas, edited  14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 18:00:47 ሙሉ ለሙሉ ነፃ የትምህርት ስኮላርሽፕ የሚሰጡ ዩኒቨርስቲዎች ከነ አድራሻቸው !!

1. Simon Fraser University Scholarships In Canada
https://lnkd.in/dkNEy39J
2. Orange Knowledge Programme In Netherlands
https://lnkd.in/dvvN5pAE
3. Boston University Scholarships In USA
https://lnkd.in/dx4Xn7Z
4. British Council STEM Scholarships In UK
https://lnkd.in/dn77K7dm
5. Deakin University Scholarship in Australia
https://lnkd.in/dUrKBJbe
6. LOCALINTERNational Summer Paid Internship in Turkey
https://lnkd.in/dPBySrM8
7. 300 University of South Australia Scholarships
https://lnkd.in/dRKFAtQ8
8. University of Miami Stamps Scholarship In USA
https://lnkd.in/dZQ_sKnR
9. DAAD Helmut Schmidt Germany Scholarship
https://lnkd.in/dbw36D8n
10. Hokkaido University MEXT Japan Government Scholarship
https://lnkd.in/d6MNJz7i
11. University of Manitoba Scholarship In Canada
https://lnkd.in/dEkcYbA
12. Aalto University Scholarship In Finland
https://lnkd.in/d4WtQ6AN
13. Australian Government Research Training Program
https://lnkd.in/dS2qtT_S
14. University of Dundee Scholarships In UK
https://lnkd.in/dg3b3UrC
15. Luiss University ENI Scholarship In Italy
https://lnkd.in/ddwAAatP

ምንጭ Muhammed Computer Technology

ለሁሉም እንዲደርስ #ሼር_ይደረግ
2.7K viewsBahiru Abas, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 17:33:26 #ለቅድመ_ጥንቃቄ_ይነበብ
አደገኛው የዜውስ ቫይረስ ጥቃት እና የመከላከያ መንገዶች

ዜውስ ቫይረስ በዓለም ላይ እጅግ አደገኛ ከሚባሉ በአጥፊ ሶፍትዌር ከሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃት ዓይነቶች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

እንደሌሎች የቦትኔት ጥቃቶች ሁሉ የዜውስ ቫይረስም ጥቃቱን የሚፈጽመው በበይነ መረብ አማካኝነት፣ እርስ በእርሳቸው በተሳሰሩ ኮምፒውተሮች እና ተያያዥ መሣሪያዎች ላይ እኩይ ሶፍትዌሮችን በማሰራጨትና በመበከል ነው፡፡

የዜውስ ዋነኛ የጥቃት ዒላማዎቹ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት ሲሆኑ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃዎች፣ የይለፍ ቃሎች፣ የባንክ አካውንት መረጃዎችና ሌሎች ሚስጥራዊ ገንዘብ ነክ መረጃዎች ይጠልፋል፡፡ ከዚያም መረጃዎችን ለአጥቂዎች በማስተላለፍ የአጋች ሶፍትዌር ወይንም የራንሰምዌር ጥቃትን ጨምሮ ሌሎች ገንዘብ ነክ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ ያደርጋል፡፡

የዜውስ ቫይረስ ጥቃትን እንዴት እንከላከል?

• ድረ ገጾችን በሚያስሱበት ወቅት በየሰዓቱ እየመጡ የሚያስቸግሩ ያልተፈለጉ አዋካቢ ማስታወቂያዎችን አይክፈቱ፣ አይመልከቱ፤

• ማንኛውንም የኢሜይል መልዕክት (ከሚያውቁት አካል የተላከ ቢሆን እንኳን) ምንጩን ከየት እንደሆነ ሳያረጋግጡ በጭራሽ አይክፈቱ፤

• የማያውቋቸውን ማናቸውም ዓይነት አታችመንቶች ዳውንሎድ ከማድረግ ይቆጠቡ፤

• ማናቸውንም ዓይነት ሊንኮች አይክፈቱ፤

• ጠንካራና አስተማማኝ ፀረ ቫይረሶችን ከአስተማማኝ ምንጭ አውርደው ይጠቀሙ፤

• የሚጠቀሙባቸውን ሶፍትዌሮች በየጊዜው ያዘምኑ፤

ምንጭ፦ INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
1.9K viewsBahiru Abas, 14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 17:33:23
1.5K viewsBahiru Abas, 14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 17:08:54 አሜሪካ ማይክሮ ቺፕስ ቴክኖሎጂ በሰዎች አካል ውስጥ እንዲገጠም ፈቀደች

በኢለን መስክ የተቋቋመው ኒውራሊንክ ኩባንያ በሰዎች አካል ውስጥ ቺፕስ የማስገባት ሙከራ እንዲጀምር ፈቃድ አግኝቷል

በሰው ላይ የሚገጠመው ችፕስ ኩባንያው በቅርቡ ቴክኖሎጂውን በበጎ ፈቃደኞች ላይ እንደሚሞክር ተገልጿል

አሜሪካዊው ታዋቂ ባለጸጋ ኢለን መስክ ኒውራሊንክ የተሰኘ ኩባንያን በፈረንጆቹ 2016 ላይ ነበር የመሰረተው፡፡

ይህ ኩባንያ ዋነኛ ዓላማውም የሰዎችን አዕምሮ የመስራት አቅም ለማሳደግ በሰውነት ውስጥ ማይክሮ ቺፕስ መግጠም ዋነኛ አላማው ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ኩባንያው በ2020 ላይ ወደ ስራ የመግባት እቅድ ቢኖረውም በውጤታማነቱ ላይ ጥርጣሬ የገባቸው ባለሙያዎች እና ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ተቋማት እና ባለሙያዎች ተቃውሞ ገጥሞት ቆይቷል ተብሏል፡፡

ኒውራሊንክ ኩባንያ ማይክሮ ቺፕስ በዝንጆሮዎች ላይ ሲሞክር መቆየቱን ገልጾ የአዕምሮ ውጤታማነትን ማሳደጉ ተረጋግጧል ብሏል፡፡

ኩባንያው ከዚህ በፊት ቴክኖሎጂውን በሰዎች ላይ እንዲተገብር ፈቃድ እንዲሰጠው ለአሜሪካ ምግብ እና መድሃኒት አስተዳድርን ጠይቆ የነበረ ቢሆንም ጥያቄው ውድቅ ተደርጎበት ነበር፡፡

ተቋሙ አሁን ላይ የሰውችን የአዕምሮ ውጤታማነት ለማሳደግ ቴክኖሎጂውን በሰዎች ላይ መተግበር እንደሚችል ፈቃድ መስጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይተገበራል የተባለው ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በሰው አካል ላይ ማይክሮ ቺፕስ በማስገባት ሰዎች ስራዎችን ሲያከናውኑ አዕምሯቸው እንዳይለግም አወንታዊ መልዕክት ወደ አዕምሮ እንዲላክ እና ስራው አልያም ውሳኔው እንዲፈጸም የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ቴክኖሎጂው በመጀመሪያ አልታዘዝ ያሉ የሰውነት ክፍሎች እንዲንቀሳቀሱ ፣ማየት ባልቻሉ ሰዎች ላይ እይታን እንዲጎናጸፉ እና ሌሎችንም ተግባራት ውጤታማ ማድረግ ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡

ቀስ በቀስ ደግሞ በሌሎች የተሟላ አካል ባላቸው እና የቴክኖሎጂ አገልግሎቱን በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ይተገበራልም ተብሏል፡፡

የኒውራሊንክ ኩባንያ መስራች ኢለን መስክ ከዚህ በፊት ስለ ድርጅታቸው እንዳሉት የሰው ልጆች በአርቲፊሺያል ኢንተሊጀንስ ቴክኖሎጂዎች የመዋጥ አደጋ እንደተደቀነባቸው እና ኒውራሊንክ እና መሰል ኩባንያዎች ከዚህ አደጋ የማዳን አቅም አላቸው ብለው ነበር፡፡

የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በበኩላቸው የኒውራሊንክ ቴክኖሎጂ በብዙሃኑ ሰዎች ላይ ከመተግበሩ በፊት ተጨማሪ የጥንቃቄ ጥናቶች እና እርምጃዎች እንዲደረጉ አሳስበዋል፡፡

የስዊዘርላንድ ተመራማሪዎች ከሰሞኑ የሰው ልጅን አዕምሮ ከኮምፒውተር ጋር በማገናኘት መንቀሳቀስ ያልቻለ ሰውን ለአዕምሮው ትችላለህ የሚል መልዕክት እንዲደርሰው በማድረግ እንዲራመድ ማድረግ ችለዋል፡፡

#ጥያቄ

ስለ ኒዩራ ሊንክ ቴክኖሎጂ ምን ታስባላችሁ? ጠቃሚ ይመስላችኋል ወይስ ጎጂ? እንዴት?

ምንጭ፦ https://am.al-ain.com/article/us-allows-microchpis-implant-humans

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
1.7K viewsBahiru Abas, edited  14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 17:08:40
1.5K viewsBahiru Abas, 14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 18:18:49 ዋና ዋና የሀኪንግ ስልቶች እነማን ናቸው?

የእርስዎ የዲጅታል መረጃዎች ከሀከሮች እንዴት መጠበቅ ይቻላል

- ሀከሮች ”Hacker” በቀላል የሀኪግ ”Hacking” ስልት ተጠቅመው፣ የዕርሶን የግል ያልተፈቀዱ መረጃዎች ምን አልባትም እርሶ ለመግለጥ የማይፈልጉት መረጃዎችን ሊያውቁት ይችላሉ። በብዛት የተለመዱትን ወይም የሚታወቁትን የሀኪግ ስልቶች ለምሳሌ፦ Phishing፣ DDoS፣ ClickJacking ወዘተ… የመሳሰሉትን ለደህንነቶ ማወቁ የሚበጅ ነገር ነው።

- ስነ-ምግባር የጎደለው ሀከሮች፣ የሲስተምን በሀሪያት በመለወጥ እና የፕሮግራም ክፍተቶቹን በመበዝበዝ ያልተፈቀደ መረጃን ለማግኘት የሚደረጉት ተግባር ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ተብሎ ሊጠራ ይችላል። ያልተፈቀዱ መዳረሻዎችን ለማግኘት ሀኪግ በርካታ እድሎችን ለሀከሮች በማቅረብ ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንደ የክሬዲት ካር ዚርዝሮች፣ የኢሜል አድራሻ ዝርዝሮች እና ሌሎች የግል መረጃዎችን ለማወቅ ይችላሉ።

- ስለዚህ፣ የእርስዎን የግል መረጃ ባልተፈቀደላቸው መንገድ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሀኪግ ስልቶች አንዳንዶቹን ማወቅ ያስፈልጋል።

Keylogger ኪሎገር

- ኪሎገር(Keylogger) በቁልፍ ሰሌዳዎ ላይ የሚጫኑትን ቁልፎች እና የቁልፎችን ቅደም ተከተል የማስታወሻ መዝግብ ፋይል ውስጥ በኮምፒውተሮ ላይ ፅፎ የሚያስቀምጥ ቀላል ሶፍትዌር ነው። እነዚህ የማስታወሻ መዝግብ ፋይሎች ሌላው ቀርቶ የግል ኢሜል አድራሻ እና የይለፍ ቃሎችን”Passwords” የያዙ ሊሆን ይችላል።

- የኦላይን ባንኪግ ”online Banking” ድረ-ገጾች የራሳቸውን ምናባዊ ሁለገብ የቁልፍ ሰለዶችን(Virtual Keyboards) አማራጭ እንድትጠቀሙ መስጠታቸው ዋነኛ ምክንያት ኪሎገር ነው።

Denial of service (Dos/ DDoS)

- የአገልግሎት ክልከላ ጥቃት አንዱ የሀኪግ ስልት ሲሆን፣ ድረ-ገጽን ወይም ሰርቨርን(Server) አገልግሎት መስጠት ኢዲያቆም በብዙ የአገልግሎት ጥያቄዎች በማጥለቅለቅ ሰርቨሩ ሁሉንም ጥያቄዎች በአንድ ጊዜ ውስጥ ማስተናገድ የማይችልበት ደረጃ በመፍጠር እና በመጨረሻም ተበላሽቶ ከጥቅም ውጭ ማድረግ ነው።

- ሀከሮች ለDDoS ጥቃት ሲባል ብዙውን ጊዜ ቦትኔትን(Botnets) ወይም ዞምቢ(Zombie) ኮምፒውተሮችን በስራ ላይ ያውላሉ፣ እነዚህ ብቸኛው ስራቸው ለጥቃት በታቀደው ሲስተም ላይ በጥያቄ መልእክቶች ማጥለቅለቅ ነው።

Waterhole Attacks

- እርስዎ የዲስከቨሪ ወይም ናሽናል ጆግራፊ ቻናል ትልቅ አድናቂ ከሆኑ፣ የወተርሆል(Waterhole) ጥቃትን በቀላሉ ልታገናኙት ትችላላቹ። ቦታዎችን መመረዝ፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ፣ ሀከሮች የጥቃት ኢላማ በሚያደረጉት በጣም ተደራሽ የሚሆነውን አካላዊ ክፍል ላይ ጉዳት ያደርሳሉ።

- ለምሳሌ፦ አንድ ወንዝ ምንጭ ከተመረዘ፣ በበጋ ውቅት ሙሉ የእንስሳት ዝርያን ይጎዳል። በተመሳሳዩ ሀከሮች ደግሞ የሚፈልጉትን ለማጥቃት ለግኘት በጣም የቀረበውን አካላዊ ቦታን የጥቃት ኢላማ ያደርጋሉ። የዚህ ጥቃት ውስጥ ኢላማ የሚሆኑት የተወሰኑ ቡድኖች(ተቋም፣ ኢንዱስትሪ ወይም ክልል) ናቸው። በዚህ ጥቃት ውስጥ፣ ጥቃት አድራሽው የኤላማው ቡድኖች አብዝተው የሚጠቀሟቸውን ድረ-ገጾችን ይገምታል ውይም ይከታተላል እና አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑትን በማልዌር ”Malware” ያጠቃል። በመጨረሻም በኢላማው የተቀዱት ቡድን አባላት ይጠቃሉ።

Fake WAP(Wireless Application Protocol)

- ለቀልድ እንኳን፣ ሀከሮች የውሸት ገመድ-አልባ ግንኙነት መስመር የሚፈጥር ሶፍትዌር ሊጠቀሙ ይችላሉ። ይህ የተፈጠረው የውሸት ገመድ-አልባ ግንኙነት መስመር ከትክክለኛው ለህዝብ ይፋ ከሆነው ገመድ-አልባ ግንኙነት መስመር ቦታ ጋር ይገናኛል። አንዴ ከዚህ የውሸት ገመድ-አልባ ግንኙነት መስመር ጋር ግንኙነት ከፈጠራቹ፣ ሀከሮች መረጃቹን በሙሉ ማግኘት ይችላሉ። ልክ ከላይ በተጠቀሰው ሁኔታ አይነት።

Eavesdropping (Passive attacks)

- ከሌሎች በፈጥሮ ተፅኖዊ(Active) ጥቃቶች በተለየ፣ ተፅኖ አልባ(Passive) ጥቃቶችን በመጠቀም፣ ሀከሩ ጥቂት የማያስፈልጉ መረጃዎችን ለማግኘት የኮምፒውተር ስርዐቶችን እና ኔትዎርኮችን ብቻ ይቆጣጠራሉ።

- ከኢቭስድሮፒግ ጥቃት ጀርባ የሚኖረው ፍላጎት ሲስተምን ለማበላሸት አይደለም፣ ነገር ግን ሳይታወቅባቸው በጥንቃቄ ጥቂት መረጃዎችን ለማግኘት ነው።

Phishing

- ፊሽግ አንዱ የሀኪግ ስልት ሲሆን፣ ሀከሩ በስፋት ተደራሽ ድረ-ገጾችን አስመስሎ የውሸት ድረ-ገጽ ኮርጆ ይሰራና የጥቃት ኢላማውን#buraakiller ለማጥመድ አትኩሮት መሳቢያ መልእክት በማካተት ሊንክ(Link) ወይም ማስፈንጠሪያ ይልክለታል። ተጠቂው አንዴ login አድርጎ ለመግባት ሲሞክር ወይም የተወሰኑ ዴታዎችን ካስገባ፣ ሀከሩ የተጠቂውን የግል ድብቅ መረጃ በውሸቱ ድረ-ገጽ ላይ በሚሰራው ቶርጃን”Trojan” በመጠቀም ማግኘት ይችላል።

Virus, Trojan etc…

- ቫይረሶች ወይም ቶርጃኖች አደገኛ የሶፍቴር ፕሮግራሞች ሲሆኑ፣ በተጠቂው ሲስተም ውስጥ ይጫኑና የተጠቂውን መረጃዎች ወደ ሀከሩ መላክ ይጀምራሉ።

ClickJacking Attacks

- ክሊክጃንኪግ በተጨማሪ በሌላ ስም ይታወቃል፣ UI Redress። በዚህ ጥቃት፣ ሀከሩ ተጠቂው ሊነካው ወይም ክሊክ ሊያደረጋቸው የሚገቡ ትክክለኛ በይነገጾችን”User Interface” ይደብቃል። በሌላ ቃል፣ጥቃት አድራሹ ተጠቂው ክሊክ በማድረግ በትክክል ሊያገኝ ያላቀደው ወደሆነ ድረ-ገፅ ውስጥ ይጠልፈዋል። ነገር ግን ሀከሩ ተጠቂው እንዲገባለት የሚፈልገው ድረ-ገጽ ነው።

Cookie Theft

- ኩኪስ “Cookies” በብራውዘሮች ወይም የድረ-ገጾች ማሰሻ ፕሮግራሞች ላይ ለምሳሌ፦ የጎበኘናቸው ድረ-ገጾች ማስታወሻ ወይም የአሰሳ ታሪክ፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ የምንጠቀምባቸው#buraakilleer የተጠቃሚነት ስም(Username) እና የይለፍ ቃሎች(Passwords) የመሳሰሉትን የግል ዴታዎችን መዝግቦ የሚይዝ ፕሮግራም ነው። ታዲያ ሀከሩ አንዴ የናንተን ኩኪስ ማግኘት ከቻለ፣ በራሳቹ ብራውዘር ላይ እራሱን እንደ እናንተ በማድረግ የተፈቀደለት ተጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ በናተ ዴታ መጠቀም ይችላል።

Bait and Switch

- Bait እና switch የሀኪግ ስልት በመጠቀም ፣ ሀከሩ ተንኮል አዘል ፕሮግራሞችን ያሰራጫል ታዲያ ግን ተጠቃሚዎች ትክክለኛ የተረጋገጠ ፕሮግራም እንደሆነ ያምናሉ። በዚህ መንገድ፣ ይህን ተንኮል አዘል ፕሮግራም በኮምፒውተራቹ ላይ ስትጭኑት፣ ሀከሩ በኮምፒውተራቹ ላይ ያልተፈቀደለትን መዳረሻ ፍቃድ ያገኛል።

ምንጭ፦ ELATECH

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
2.2K viewsBahiru Abas, edited  15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 17:53:12
ይህ የሆነው ሩቅ ሀገር አይደለም። እዚህ ጎረቤታችን ኬንያ ነው ።
......
ይህች በስልክ እንጨቱ ላይ ያለችው ወፍ ግንደ ቆርቁር ( woodpecker ) ትባላለች ። ግንድ ቆርቁራ ጎጆዋን ትቀልስና ፡ በዛ ለአመታት ትኖራለች ። ቤተሰብ መስርታ ልጆቿንም በዛው ታሳድጋለች ።
.......
በፎቶው የምታዩዋት woodpecker በዚህ የመብራት ፖል ላይ ቆርቁራ መኖር ከጀመረች ቆይታለች ። እና የኬንያ መብራት ሀይል መስሪያ ቤት ይህን ያረጀ ፖል ፡ በኮንክሪት ሊቀይረው ይመጣል ። እና ልክ ፖሉን ለመጣል አስረው ማዝመም ሲጀምር ፡ ከተቆረቆረው ግንድ ውስጥ አንድ woodpecker ወፍ ትወጣለች ።
ነገር ግን ከዛ መራቅ አልቻለችም ፡ ትወጣና መልሳ ለመግባት ትሞክራለች ፡
ሰራተኞቹ ፖሉን ነቅለው አስቀመጡት በዚህ ጊዜ ወጥታ የነበረችው ወፍ መጥታ ተቀመጠች ፡ ሰራተኞች ቀርበው አዩ ። ተቆርቁሮ በተሰራው የወፍ ቤት ውስጥ ጫጩቶች ነበሩ ።
...........
ልክ ይህን እንዳዩ መልካም ልብ ያላቸው የመብራት ሀይል ሰራተኞች ይህችን ወፍ ከነልጆቿ ቤት ማሳጣት ጭካኔ እንደሆነ ተሰማቸውና ቤቷ ያለበትን አካባቢ ሳይነኩ ፡ ከረዥሙ የመብራት ፖል ላይ የተወሰነውን ትንሽ ክፍል ቆርጠው ፡ ከአዲሱ የኮንክሪት ፖል ጋር በዚህ መልኩ አያያዙት ። አውጥተው ሊጥሏት ሲችሉ ፡ አዘኑላት ፡ ለልጆቿ ልባቸው ራራ ።

(Wasihune Tesfaye)

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
2.4K viewsBahiru Abas, edited  14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 15:32:23 Dotcom TV Show pinned a photo
12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 15:32:09
#ጤና_ይስጥልኝ_ወዳጆቼ
የዶትኮም የፌስቡክ ገፅ በቴክኖሎጂ ዙሪያ ተከታዮቹን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የበኩሉን እንደሚጥር የዚህ ገፅ ቤተሰቦች እንደምትመሰከሩ አልጠራጠርም።

ነገር ግን ይህ ገፅ የሚጥረውን ያህል ብዙ ተከታይ የለውም።70,000 ተከታዮች ብቻ ነው እስካሁን ያፈራው።

ፔጁን #Like #Follow በማድረግ ቤቱን ሞቅ ሞቅ ብናረገው ምን ይመስላችኋል ??

በቅድሚያ የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ

ሊንኩ ይሄው ፦
Dotcom Tv Show-ዶትኮም ፕሮግራም
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
2.3K viewsBahiru Abas, 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ