Get Mystery Box with random crypto!

Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dotcomtvshow
ምድቦች: ሽያጭ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.01K
የሰርጥ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሰረፀባት፣ያደገች ፣የበለፀገች እና የዓለም ህዝብ ሁሉ የሚመርጣት ምርጥ ሀገር እንድትሆን እመኛለሁ!!
t.me/dotcomtvshow

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-07-07 17:24:30
ቤቢዬ እያደገች ነው..In My Face
2.9K viewsBahiru Abas, 14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:08:26
ከዛሬ ተመራቂዎች መካከል እማሆይ አንዷ ናቸው።

"እማሆይ ፍሬሕይወት ዘምሁር ገዳመ ኢየሱስ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ በማስተርስ ድግሪ በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል። እናትነትና ምንኩስና ሳይበግራቸው ለዚህ ደረጃ መድረስ ምንኛ መታደልም ነው!" ይህ ነው ጀግንነት!!

(ጴጥሮስ አሸናፊ)
እንኳን ደስ ያለዎት እማሆይ!
4.4K viewsBahiru Abas, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 16:28:12
#ሮፍናን SIDIST-VI.የሚል መጠሪያ የሰጠው አዲሱ አልበም የሽፋን ምስል ይህ ነው።

የሽፋን ዲዛይኑ እንዴት አያችሁት?
3.6K viewsBahiru Abas, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 15:30:24
3.5K viewsBahiru Abas, 12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 14:56:10
የሞባይል ስልክ ፈጣሪዉ የ 93 አመቱ የእድሜ ባለጸጋ አሜሪካዊዉ ማርቲን ኩፐር እኔ ሞባይል ስልክን ከ አምስት ፐርሰንት በታች ነዉ ጊዜ ሰጥቼ የምጠቀመዉ። አብዛኛዉ ጊዚያችሁን ሞባይል ላይ ማጥፋት ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ሕይወታችሁን ያበላሻል።ወደ ሕይወታችሁ ተመለሱ ሲል መክሯል።
2.9K viewsBahiru Abas, 11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:04:56
ሁሉም ነገር ከቀን ወደ ቀን አስፈሪ እየሆነ ነው!
መጨረሻችንን ያሳምርልን!
2.9K viewsBahiru Abas, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 19:46:18
#ሮፍናን "ስድስት" የተሰኘ አዲስ አልበም ሊያወጣ ነው!

ሮፍናን ይህንኑን "ስድስት" የተሰኘ አዲስ አልበሙን በታዋቂው የ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ አሳታሚ ተቋም በሆነው ዩኒቨርሳል ሙዩዚክ ግሩፕ አማካኝነት በቅርቡ ለአድማጭ ጆሮ እንደሚያደርስ ነው ያስታወቀው ፡፡

ሮፍናን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአንጋፋዎቹ ጀምስ ብራውን፣ ስቲቪ ዋንደር ፣ ሪሃና የመሳሰሉ የ ታዋቂ አርቲስቶችን ስራዎች በማሳተም እና በማስተዋወቅ የሚታወቀው ዩኒቨርሳል ሙዩዚክ ግሩፕ (Universal Music Group, the world's leading music company - UMG) ያደረገው ስምምነት በአይነቱ ልዩ መሆኑ ነው የተሰማ፡፡

ከሃገረ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስምምነት ወጥቱን አርቲስ አለማቀፍ እውቅናውን ከፍ ከማድረጉም በላይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በአለም ለማስተዋወቅ ትልቅ እርምጃ ነው ተብልዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ነጸብራቅ በሚለው የመጀመሪያ አልበሙ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳገኘ የሚነገርለት አርቲስት ሮፍናን አሁን
ከህጻናት ጋር በመዋል ቀስሜዋለው ያለውን አዲስ እሳቤ “ስድስት” በተሰኘ አልበሙ ላይ እንዳንጸባረቀው ተናግርዋል ። ይህ "ስድስት" የተሰኘው አዲሱ አልበሙ ሃምሌ 20/2014 ዓ.ም የሚለቀቅ ሲሆን አርቲስቱ ዘጠኝ የተሰኘ ሌላ አልበሙንም ሰርቶ ማጠናቀቁንም በዚሁ ጊዜ አሳውቅዋል፡፡
2.8K viewsBahiru Abas, 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 19:37:04 የመረጃ ማፈላለጊያዎችን #browsers ስንጠቀም ማድረግ ያለብን የጥንቃቄ ርምጃዎች

• የመረጃ ማፈላለጊያዉን ታሪክ(browsing history) ማጥፋት

• ደረ-ገፆችን በኤችቲቲፒኤስ #HTTPS ማገናኘት

• የመረጃ ማፈላለጊያዉን በየጊዜው ማደስ #update

• የተለያዩ የይለፍ-ቃሎችን በብሮዉዘሩ ላይ አለማስቀመጥ

• ዶክመንት ከማውረዳችን በፊት ጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር መጫንና አባሪዎችን መቃኘት #scan ማድረግ

• ለተለያዩ አካውንቶች ተመሳሳይ የይለፍ-ቃል አለመጠቀም

• የህዝብ ወይም ነፃ ዋይፋይ አለመጠቀም

• የመረጃ ማፈላለጊያውን ፖፕአፕ #pop up ብሎከር ማብራት/መክፈት

• የመልእክት ማንቂያዎች ላይ መመዝገብ #register on alerts

ምንጭ፦INSA-የመረጃ መረብ ደህንነት አስተዳደር
መረጃው ጠቃሚ ከሆነ ለሌችም እንዲደርስ #ሼር_ይደረግ

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
2.7K viewsBahiru Abas, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 17:37:48
2.7K viewsBahiru Abas, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:01:29 ጓደኛን ስትመርጥ . . .

አመለካከትህ የምትመርጠውን ጓደኛ ይወስናል፤ አብረህ የምትከርመው ጓደኛ ደግሞ በተራው አመለካከትህን የመወሰን ጉልበት ስላለው ወደ ሕይወትህ ዘልቆ እንዲገባ የምትፈቅድለትን ሰው በጥንቃቄ ምረጥ፡፡

“ጓደኝነት እንደ ሊፍት (Lift / Elevator) ነው፡፡ ወይ ወደላይ ያወጣሃል ወይም ደግሞ ወደታች ያወርድሃል” የሚል አባባል አለ፡፡ ሌላ ረዘም ላለ ጊዜ የከረመ አባባል፣ “በአጠገብህ የሚገኙ የአምስቱ ቅርብ ጓደኞችህ ጭማቂ ነህ” ይላል፡፡ እነዚህ አባባሎች ልቦናን የሚያነቃ እውነት ይዘዋል፡፡ የቅርብ ጓደኞችህን የያዝክበት የራስህ የሆነ ምክንያት ቢኖርህም፣ ለውጥ ለማምጣት በምትፈልግበት ጊዜ በዙሪያህ የሚገኙት ሰዎች ምን አይነት ሰዎች አንደሆኑ ማሰብ መጀመርህ አይቀርም፡፡

ከዚህ በታች ጓደኛን ስትመርጥ ሊኖርህ ስለሚገባ የምርጫ መመዘኛ የሚያስተምሩ ነጥቦችን ታገኛለህ፡፡

1. “ወደ ላይ” ምረጥ፡- የማደግና የመሻሻል ፍላጎቱ ካለህ የምትይዛቸው ጓደኞች ከአንተ ከፍ ያሉ እንዲሆኑ ትመከራለህ፡፡ ከፍ ያሉ ሰዎች ከፍ ያደርጉሃል፡፡ የበሰሉ ሰዎች ብስለትን ያስተዋውቁሃል፡፡ ይህንኑ ተመሳሳይ መርህ በመከተል የአንተን ላቅ ያለ ደረጃ ፍለጋ አንተን የሚቀርቡህ ሰዎች የመኖራቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንተ ግን ወደ ላይ መመልከትህን መዘንጋት የለብህም፡፡

2. ተመሳሳይ መርህ ያለውን ምረጥ፡- በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበት ሳንክድ፣ አመለካከትንና መርህን አስመልክቶ ግን ተመሳሳይነት ያላቸውን ሰዎች መቅረብ ስኬታማ ያደርግሃል፡፡ መርህን አስመልክቶ ልዩነታችሁ ከጎላ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መያዝ፣ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ልዩነትን በማስታረቅ ዙሪያ የሚሽከረከር ግንኙነት ውስጥ እንድትቀር ያደርግሃል፡፡

3. ተመሳሳይ ግብ ያለውን ምረጥ፡- የዚህ ምርጫ ጥቅሙ የመደጋገፍና የመበረታታት ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ አንተ ያለህ ግብ ሕብረተሰብህን የማገልገል ከሆነና የቀረብከው ጓደኛ ዋና ግቡ በገንዘብ የመበልጸግ ብቻ ከሆነ የጋራ የሆነን ሃሳብ በመወያየት የሞራልና የተግባር ድጋፍ መለዋወጥ ሊያስቸግራችሁ ይችላል፡፡

4. በስኬትህ ደስ የሚለውን ምረጥ፡- በተሳካልህ ቁጥር ከአንተ ጥቅምን እንደሚፈልግ የሚያሳይ፣ ስለስኬትህ ስትነግረው ብዙም ሃሳብ የማይሰጥ፣ ስኬትህን አስምልክቶ ከአንተ ጀርባ ለሌሎች የሚያወራና የመሳሰሉት ባህሪይ የሚያንጸባርቅን ሰው ጓደኛ ከማድረግህ በፊት ደግመህ ልታስብበት ይገባል፡፡

5. በውድቀትና በችግር የማይለይህን ምረጥ፡- ሁሉም ነገር በተሟላልህ ወቅት አብሮህ ሆኖ፣ ሁኔታዎች እንደ ቀድሞው አልሆን ሲሉህና ነገሮች ሲፈራርሱብህ ከአንተ ዘወር የሚል ባህሪይ ያለበት ሰው አይበጅህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ከአንተ ከሚያገኙት ጥቅም አንጻር ብቻ የሚቀርቡህ ናቸውና ስሜትህን ጠብቅ፡፡

6. እውነቱን የሚነግርህን ምረጥ፡- እውነቱን የማይነግርህ ሰው ከምታይበት ባህሪ አንዱ አንተ ጋር ሲሆን አንተን ደስ የሚልህን ብቻ እየመረጠ የመንገር ሁኔታ ነው፡፡ እውነተኛ ወዳጅ ግን እየወደደህና እያከበረህ፣ ቢያምህም እውነቱን ይነግርሃል፡፡ ይህ አይነቱ ሰው ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም፡፡ .......
ከየመፃሕት ማዕድ
3.2K viewsBahiru Abas, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ