Get Mystery Box with random crypto!

Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dotcomtvshow
ምድቦች: ሽያጭ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.01K
የሰርጥ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሰረፀባት፣ያደገች ፣የበለፀገች እና የዓለም ህዝብ ሁሉ የሚመርጣት ምርጥ ሀገር እንድትሆን እመኛለሁ!!
t.me/dotcomtvshow

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-21 17:37:31 ኮምፒውተራችን ማንኛውንም #ፍላሽ_ዲስክ እንዳይቀበል ማድረግ እንዴት ይቻላል ?

ኮምፒውተራችን ላይ #ፍላሽ ዲስክ በምንሰካበት ጊዜ ብዙ ጊዜ ፍላሽ ዲስኩ በቫይረስ የተጠቃ በሚሆንበት ጊዜ ቫይረሱ በቀጥታ ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት ኮምፒውተራችንን ስራ ማስተጎጎል እንዲሁም እስከ ማጥፋት ሊያደርስ ይችላል ስለዚህ ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ ሰዎች ወደ ኮምፒተራችን ከተው እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን።

ኮምፒውተራችንን ማንኛውንም ፍላሽ ዲስክ እንዳይቀበል አድርገን እንዴት መቆለፍ እንችላለን።

ወደ ኮምፒውተራችን በመግባት this pc ወይም my computer ላይ Right Click እናደርጋለን።
ከዛም ከሚመጡልን ምርጫዎች ውስጥ Manage የሚለውን እንመርጣለን።
ቀጥሎም Device Manager
ከዛም በቀኝ በኩል ካሉት ምርጫዎች Universal Serial Bus Controllers ከሚለው ስር ያለውን drop down arow ወይም የዝርዝር ቀስቱን እንነካለን።
ከዛም extensible host controller ላይ ራይት ክሊክ እናደርጋለን ።
ከተዘረዘሩት ዉስጥ Disable ክሊክ እናደርጋልን አለቀ
ወደነበረበት ለመመለስ Enable Device የሚለውን ይጫኑ!

አሁን ላፕቶፓችን ወይም ዴስክ ቶፕ ኮንፒተራችን ፍላሽ፣ሃርድዲስክ እንዳያነብ ብሎክ ሁኖል ማለት ነው።

#ሼር_ማድረግ_አትርሱ

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
2.7K viewsBahiru Abas, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 16:58:02 የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡

@mohammed computer technology
መረጃው ጠቃሚ ከሆነ ለሌችም እንዲደርስ
#ሼር_ይደረግ

  የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
2.3K viewsBahiru Abas, 13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 20:41:38
#ተስፋ_አትቁረጥ

በ17 ዓመቷ ከኮሌጅ ተባረረች

በ25 ዓመቷ እናቷን በሞት አጣች

በ26 ዓመቷ ጽንስ ወረደባት

በ27 ዓመቷ ትዳር መሰረተች

ባሏ ከፍተኛ ጭቆና አደረሰባት፥ ሆኖም ግን ሴት ልጅ ተገላገለች

በ28 ዓመቷ ትዳሯ ፈረሰ፥ ብዙ አይነት የጭንቀት በሽታም ተገኘባት

በ29 ዓመቷ በእርዳታ ትተዳደር ነበር

በ30 ዓመቷ ሞትን ተመኝታ ነበር -ራሷንም ለማጥፋት ወሰነች ይሁን እንጂ የህይወቷን በመቀየር ከሌላ ሰው የተሻለ ነገር ለመስራት መሰነች

በ31 ዓመቷ የመጀመሪያ መጽሀፏን አሳተመች

በ35 ዓመቷ 4 መጽሐፎችን በማሳተም የአመቱ ምርጥ ደራሲ ተባለች

በ42 ዓመቷ በአንድ ቀን ውስጥ 11 ሚሊዮን ኮፒ መጽሐፎቿን ሸጠች

ይህቺ ሴት J.K. Rowling ትባላለች! በ30 አመቷ ራሷን ልታጠፋ እንደነበረ አስበሃል?

ይህች ሴት የHarry Potter መጽሐፍ ደራሲ ከመጽሐፉ ብቻ በተገኘው ከ15 ቢሊዮን ዶላር በአለም አቀፍ ደረጃ በቱጃሮች ተርታ ተቀምጣለች!

ተስፋ አትቁረጥ! ተግተህ ሥራ! ጽኑ አላማ ይኑርህ! በፈጣሪሀሰ ታመን! ይሳካልሃል!

#ሼር_ማድረግ_አትርሱ

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
642 viewsBahiru Abas, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 18:44:06
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
830 viewsBahiru Abas, 15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 18:14:15 #ኮምፒውተራችሁ_እየተንቀራፈፈ_ተቸግራችኋል?

ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል ?

እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን ።

1. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

2.Disable unwanted start up programs

ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

4. Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

5. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

6. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

7. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

8. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ

#share_please

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
891 viewsBahiru Abas, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 20:02:36 #ሰላም_ጤና_ይስጥልኝ!!


ዩቲዩብ ቻነሌ ላይ በጣም ጠቃሚ ቪድዮዎች አሉ።
በቅርብ አፕሎድ ካደረኳቸው ቪድዮዎች መካከል ለምሳሌ፦

ነፃ ትምህርት የሚሰጡ ዌብሳይቶችን በተመለከተ፣
ላፕቶፕ ስንገዛ ለኛ የሚሆነውን ላፕቶፕ እንዴት መርጠን መግዛት እንደምንችል፣
መሬት ድንገት ብትጠፋ እንዴትና ለምን እንደጠፋች መዝግቦ የሚያስቀምጥ ብላክ ቦክስ(Black Box) መገንባቱን የሚገልፅ እና ሌሎችም እጅግ ጠቃሚ ቪድዮዎች ይገኛሉ።

ለማንኛውም የዩቲዩብ ቻነሌን ሰብስክራይብ በማድረግ እራሳችሁ ምስክር ሁኑ።

ይሄው ሊንኩ፦
https://youtube.com/@dotcomtvshow2729
490 viewsBahiru Abas, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 18:49:44 ላፕቶፕ ሲገዙ ማገናዘብ ያለብዎ አስፈላጊ ነገሮች
1. ምን ሊሰሩበት አስበዋል?
ብዙ ሚፅፉ ከሆነ ኪቦርዱን ማየት ይገባል
ጌም ሚያበዙ ከሆነ ግራፊክስ ካርዱንና ስፒከሩን
ይመልከቱ
ለቪዲዮ ቅንብር (editing or software Engineering) ከሆነ ከፍተኛ የፕሮሰሰር አቅም ፣ ትልቅ ሳይዝ ራም high definition (HD) ስክሪን
መኖሩን ያረጋግጡ
2 አዲስ ከካምፓኒው እንደመጣ ( brand new ) ነው
ወይም በብልሽት ምክንያት ተመልሶ ካምፓኒው
ገብቶ የተሰራ (Refurbished ) መሆኑን ያረጋግጡ
3. የስክሪን ወይም የዲስፕለይ መጠን: ለርሶ ትክክለኛዉን የስክሪን መጠን ይምረጡ
(13.3” ,15.6”,17.3”)
4. የላፕቶፑን ስፔሲፊኬሽን በጥልቀት ይመርምሩ
ፕሮሰሰር (intel core 2 dou, core i3, core i5,
core i7 or AMD and others)
ራም (ስንት እንደሆነ 1GB,2GB,3GB,4GB , 8G and above)
ሀርድ ዲስክ (160 GB, 250GB, 320GB,500GB, 750GB and above)
ዲቪዲ ወይም ብሉሬይ ድራይቭ ( re-writable )
5. ባትሪ ይህ በጣም ወሳኝ ነው ። ሊደራደሩበት
አይገባም! ቢያንስ 3 ሰአት እና ከዛ በላይ ቢሆን አሪፍ ነው
6. የሚፈልጉት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይምረጡ:
ማክሮሶት ዊንዶውስ (windows 7, windows
8,windows10, windows11) , mac, Ubuntu,Linux ወዘተ
ዊንዶውስ 10 ወይም windows 11 ቢመርጡ ይመከራል!

ምንጭ፦MuhammedComputerTechnology

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
666 viewsBahiru Abas, 15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 18:14:32 አንድ ትልቅ የኮምፒዩተር ድርጅት ውስጥ የሺንት ቤት የጽዳት ሰራተኛ ሆኖ ለመስራት የአመለከተ ሰውዬ ስራ አስኪያጁ ኢንተርቪው ሲያደርገው ከቆየ በኋላ ለስራው ተቀባይነት አግኝተሃል ስለዚህ የስራ ስምሪትና ውሉን እንድንልክልህ ኢሜልህን ስጠኝ ይለዋል። ሰውዬውም ኤሜልም ኮምፒውተርም እንደሌለው ይገልጻል። ከዚያም ማናጀሩ ኮንፒውተር የለህም ማለት አንተ የለህም ማለት ሲሆን ከሌለህ ደግሞ ለእኛ መስራት አትችልም በማለት በሩን እፊቱ ላይ ዘጋበት። ሰውዬውም እያዘነ ከዚያ እንደወጣ እኪሱ በነበረው 10$ ዶላር 10ኪግ እንጆሪ በመግዛት ቤት ለቤት እየዞረ በመሸጥ ቀኑ መጨረሻ ላይ 20$ አተረፈ። ከዚያም ነገሩ ቀላል እንደሆነ ሲረዳ መጠኑን በእጥፍ እየጨመረ እየሸጠ በሚያተርፈው አንድ ሳይክል ገዝቶ በዚያ እየተንቀሳቀሰ ስራውን ቀጠለ። ከዚያም ገቢው እ
የጨመረ ሲመጣ በመደብር መሸጥ ጀመረ። ጠንክሮ በመስራቱ ከአምስት አመታት በኋላ የትልቅ የምግብ መደብር ባለቤት ሆነ። እንዲህ እየሆነ ሲመጣ ስለ ድርጂቱ ስለ ወደፊቱ ማሰብ ሲጀምር ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር ውል መግባት እንዳለበት ወሰነ። ከኢንሹራንስ ኩባንያ ባለሙያው ጋር ማውራት እንደጀመሩ ተግባቡና ውሉን እንድልክልህ ኢሜልህን በማለት ይጠይቀዋል? ሰውዬውም ኢሜይልም ኮንፒውተርም የለኝም በማለት መለሰለት። የኢንሹራንስ ባለሙያውም በመደነቅ በአምስት አመት ውስጥ ትልቅ የምግብ መደብር አቋቁመህ ኢሜይል የለህም? ቢኖርህ ምን ትሆናለህ አለው። እሱም መለሰ ከአምስት አመት በፊት ኢሜይል ቢኖረኝ አሁን ድርጅት ውስጥ ሺንትቤት አጸዳ ነበር አለው።
አንዳንድ ነገሮች የማይሆኑት ለበጎ ነው ወይም በምክንያት ነው። ምንአልባት አንደኛው በር ሲዘጋ ሌላኛው እየተከፈተ ይሆናልና ሁሌም በፈጣሪህ ተስፋ አትቁረጥ!

ሼር_ማድረግ_አትርሱ

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
799 viewsBahiru Abas, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 19:37:59 #ሰላም_ጤና_ይስጥልኝ!!
በቅድሚያ እንኳን አደረሳችሁ!!

ዩቲዩብ ቻነሌ ላይ በጣም ጠቃሚ ቪድዮዎች አሉ።
በቅርብ አፕሎድ ካደረኳቸው ቪድዮዎች መካከል ለምሳሌ፦

ነፃ ትምህርት የሚሰጡ ዌብሳይቶችን በተመለከተ፣
ላፕቶፕ ስንገዛ ለኛ የሚሆነውን ላፕቶፕ እንዴት መርጠን መግዛት እንደምንችል፣
መሬት ድንገት ብትጠፋ እንዴትና ለምን እንደጠፋች መዝግቦ የሚያስቀምጥ ብላክ ቦክስ(Black Box) መገንባቱን የሚገልፅ እና ሌሎችም እጅግ ጠቃሚ ቪድዮዎች ይገኛሉ።

ለማንኛውም የዩቲዩብ ቻነሌን ሰብስክራይብ በማድረግ እራሳችሁ ምስክር ሁኑ።

ይሄው ሊንኩ፦
https://youtube.com/@dotcomtvshow2729
628 viewsBahiru Abas, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 18:53:50 ኮምፒውተርዎን ፈጣን የሚያደርጉ 10 ዘዴዎች

1. ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፎቶዎች ዎልፔፐር አይጠቀሙ፡፡
2. ሁሌም ኮምፒዩተሩ ከፍቶ ሳይጨርስ አፕሊኬሽን ለመክፈትም ሆነ ለመነካካት አይሞክሩ፡፡
3. አፕሊኬሽን ከዘጉ በሁዋላ ዴስክቶፑን ሪፍሬሽ ያድርጉ፤ ይህም ራም ሜሞሪን ነፃ ያደርጋል፡፡
4. የማይጠቀሙበት ሶፍትዌር ካለ ከኮምፒውተሩ ይሰርዙ (አን-ኢንስታል) ያድርጉት)፡፡
5. ዴስክቶፕ ላይ ፋይል አያስቀምጡ፤ ሾርትከትም መብዛት የለበትም፡፡
6. ኮምፒዩተሩ ሲከፈት በራሳቸው የሚከፈቱ ለምሳሌ: ስካይፕ አይነት አፕሊኬሽኖች ካሉ disable ያድርጉ
7. Recycle binን ሁሌም ባዶ ያድርጉ::
8. ሀርድ ዲስኩን ሁለት ፓርቲሽን ይፍጠሩለት፡፡
9. ብዙ ሶፍትዌሮችን ባንዴ አይክፈቱ::
10. ኮምፒውተርዎን update ያድርጉ!

በነገራችን ላይ በነፃ የኦንላይን ትምህርት የሚሰጡ አራት ዌብሳይቶችን እና እንዴት መመዝገብ እንደምትችሉ የሚያሳይ ቪድዮ ዩቲዩብ ቻነሌ ላይ አለ።አሁን ወቅቱ የምዝገባ ወቅት ስለሆነ አያምልጣችሁ።

ይሄው ሊንኩ፦













#ሼር_ይደረግ
750 viewsBahiru Abas, 15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ