Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ትልቅ የኮምፒዩተር ድርጅት ውስጥ የሺንት ቤት የጽዳት ሰራተኛ ሆኖ ለመስራት የአመለከተ ሰውዬ | Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

አንድ ትልቅ የኮምፒዩተር ድርጅት ውስጥ የሺንት ቤት የጽዳት ሰራተኛ ሆኖ ለመስራት የአመለከተ ሰውዬ ስራ አስኪያጁ ኢንተርቪው ሲያደርገው ከቆየ በኋላ ለስራው ተቀባይነት አግኝተሃል ስለዚህ የስራ ስምሪትና ውሉን እንድንልክልህ ኢሜልህን ስጠኝ ይለዋል። ሰውዬውም ኤሜልም ኮምፒውተርም እንደሌለው ይገልጻል። ከዚያም ማናጀሩ ኮንፒውተር የለህም ማለት አንተ የለህም ማለት ሲሆን ከሌለህ ደግሞ ለእኛ መስራት አትችልም በማለት በሩን እፊቱ ላይ ዘጋበት። ሰውዬውም እያዘነ ከዚያ እንደወጣ እኪሱ በነበረው 10$ ዶላር 10ኪግ እንጆሪ በመግዛት ቤት ለቤት እየዞረ በመሸጥ ቀኑ መጨረሻ ላይ 20$ አተረፈ። ከዚያም ነገሩ ቀላል እንደሆነ ሲረዳ መጠኑን በእጥፍ እየጨመረ እየሸጠ በሚያተርፈው አንድ ሳይክል ገዝቶ በዚያ እየተንቀሳቀሰ ስራውን ቀጠለ። ከዚያም ገቢው እ
የጨመረ ሲመጣ በመደብር መሸጥ ጀመረ። ጠንክሮ በመስራቱ ከአምስት አመታት በኋላ የትልቅ የምግብ መደብር ባለቤት ሆነ። እንዲህ እየሆነ ሲመጣ ስለ ድርጂቱ ስለ ወደፊቱ ማሰብ ሲጀምር ከኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጋር ውል መግባት እንዳለበት ወሰነ። ከኢንሹራንስ ኩባንያ ባለሙያው ጋር ማውራት እንደጀመሩ ተግባቡና ውሉን እንድልክልህ ኢሜልህን በማለት ይጠይቀዋል? ሰውዬውም ኢሜይልም ኮንፒውተርም የለኝም በማለት መለሰለት። የኢንሹራንስ ባለሙያውም በመደነቅ በአምስት አመት ውስጥ ትልቅ የምግብ መደብር አቋቁመህ ኢሜይል የለህም? ቢኖርህ ምን ትሆናለህ አለው። እሱም መለሰ ከአምስት አመት በፊት ኢሜይል ቢኖረኝ አሁን ድርጅት ውስጥ ሺንትቤት አጸዳ ነበር አለው።
አንዳንድ ነገሮች የማይሆኑት ለበጎ ነው ወይም በምክንያት ነው። ምንአልባት አንደኛው በር ሲዘጋ ሌላኛው እየተከፈተ ይሆናልና ሁሌም በፈጣሪህ ተስፋ አትቁረጥ!

ሼር_ማድረግ_አትርሱ

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ