Get Mystery Box with random crypto!

Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹 D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dotcomtvshow — Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dotcomtvshow
ምድቦች: ሽያጭ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.01K
የሰርጥ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሰረፀባት፣ያደገች ፣የበለፀገች እና የዓለም ህዝብ ሁሉ የሚመርጣት ምርጥ ሀገር እንድትሆን እመኛለሁ!!
t.me/dotcomtvshow

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-25 20:23:25 ሰላም ውድ ቤተሰቦች!!

ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ?

የንግድ ድርጅቶ ይሁን ማንኛውም የሚሰሯቸውን ስራዎች ማስተዋወቅ ከፈለጉ በጣም በቅናሽ ዋጋ እዚህ ቻነል ላይ እናስተዋውቅሎታለን!!

ይደውልሉኝ ወይም ቴክስት ያርጉልኝ
+251928959595
2.0K viewsBahiru Abas, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 18:06:18 ስለ ስልክ ቫይረስ ምንያህል ያቃሉ
What is Virus ??

#Virus ማለት የ Computer Code ወይም Program ሲሆን ብዙ ግዜ የሚሰራው ወይም
የሚፈጠረው የ Computer እውቀት ባላቸው ሰወች እና ስለ Computer ጠልቀው በ ተማሩ ሰወች ነው
ቫይረስ ስንል ብዙ አይነት ቫይረሶች አሉ
➲Spyware Virus
➲Malware Virus
➲Ransonware Virus
➲Adware Virus
➲Trojan Horse Virus ናቸው
እንደ ስማቸው ሁሉ ስራቸውም ይለያያል

የ#Virus ዋና አላማው እና ስራው ምን ምን ናቸው

1 ስልካችንን ማበላሸት (Damage) ማድረግ
የስልኩን Software ቫይረሱ በሚያጠቃበት ግዜ ስልኩ Dead ይሆናል ይህ ማለት ስልካችን Samsung ከሆነ ስንከፍተው Samsung ይልና ቀጥ ብሎ ይቆማል አይከፈትም ማለት ነው

2 በጣም ጠቃሚ ፋይል ማጥፋት እና መደበቅ

ስልካችን ላይ ሆነ MemoryCard ላይ ያሉትን ማንኛውም (File)
ለምሳሌ
Music Photo Video Application Document ያለ ምንም ምህረት ያጠፋል (Format) ያደረጋቸዋል ያለኛ ትዛዝ እና ፍቃድ

4 ስልካችንን በማናውቀው Password ወይም Pattern መቆለፍ እና መዝጋት
ይህ ማለት ስልካችንን የዘጋንበትን የሚስጥር Password ይቀይርና የራሱን Password
በማስገባት ይቆልፍብናል ማለትም ስልካችንን
ሙሉ በ ሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር ያደርገዋል እኛ ስልኩን ማዘዝ አንችልም ማለት ነው

5 ስልካችንን(OS)Operating System ስራ ማዛባት እና ስልኩ እንዲዘባርቅ ማድረግ
ይህ ማለት ስልካችን ስራውን በትክክል እንዳይሰራ እንቅፋት ይሆናል ይህ ማለት እኛ ስልኩን
ሳንነካው ሳናዘው በራሱ (File)መክፈት መዝጋት
ስልኩን Flight Mode ላይ ማድረግ
ስልኩን Switch Off ማድረግ ከዛ ስልኩን መልሶ መክፈት. ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን በራሱ ይሰራል

6 Software File ማጥፋት
የ ስልካችንን Software File Delete ማድረግ
=> Software File Delete ከሆነ ስልኩን ማስተካከል ከባድ ይሆናል

ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉ ያለ ባለቤቱ ፍቃድ በራሱ መብት ይሰራል.
ስለ #ቫይረስ አደገኛነት ጉዳት እና አላማ ይህን ካልን ስለ መከላከያው እና ስለ መፍትሄው ደግሞ እናውጋ

እንዴት አድርገን ስልካችንን ከአደገኛ ቫይረስ መጠበቅ እና መከላከል እንችላለን

1 ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ ዌብሳይት ማንኛውንም ነገር ከ ማውረድ መቆጠብ
ለምሳሌ ካልታወቀ እና #Fake ከሆነ
ዌብሳይት Application ወይም File (Download) በምናደርግበት time #ቫይረሱ Download ከምናረገው Application ወይም File ጋር አብሮ ወደ ስልካችን በቀላሉ ይገባል
ለምን ቢባል Fake የሆኑ #ድረገጾች ላይ #ቫይረሶች ብዙግዜ ስለሚለቀቁ ነው ሰለዚህ ከታወቀ እና ታማኝነት ካለው ዌብሳይት ብቻ የምንፈልገውን File ማውረድ ይጠበቅብናል

2 Bluetooth Email እና G-mail ክፍት አድርጎ አለመተው ተጠቅመን ከ ጨረስን ቦሀላ መዘጋቱን #Check Up ማድረግ

3 የስልካችንን #Software Update ማድረግ
በሰአቱ እና በግዜ
ስልካችን የSoftware Update ጥያቄ ሲጠይቀን #ችላ አለማለት ወድያውኑ ስልኩን Update መድረግ
የስልካችን Software Update ከተደረገ ስልካችን በ ቫይረስ የመጠቃት እድል በጣም ዝቅተኛ ነው
የ ስልካችንን Software Update ለማድረግ መጀመሪያ #Setting ውስጥ እንገባለን ከዛ መጨረሻ ላይ #About Phone
የሚል አለ እሱን እንዴ #Click እንላለን ከዛ
Software Update የሚለውን #Click ማለት

4 ትክክለኛ እና #Original Antivirus መጠቀም
ስልካችን ላይ ያለውን ሁሉኑም Application እና File #Scan ማድረግ Scan በምናደርግበት ግዜ Virus ያለበት Application ወይም File ከተገኘ ወዲያውኑ ማጥፋት #Remove ማድረግ
እነዚህን Original Antivirus
ከ PlayStore በ ማዉረድ ተጠቀሙ
➷➷➷➷➷➷
➊#Norton Antivirus
➋#KasperskyAntiVirus
➌#BT Virus Protect: Mobile Anti-Virus & Security App
እነዚህ Antivirusሶች የሚሰሩት በ Data እና በ Wifi Connection

5 ቫይረስ በዋናነት ከሚገባበት መንገድ አንዱ በ #Email እና በ #G-mail ነው
Email እና በ G-mail በምንጠቀምበት ግዜ ከማናውቃቸው ሰወች #Link ሲላክልን ቶሎ መክፈት የለብንም ምክንያቱም የተላከው ከ #Hackerሮች (Linkኩም) ቫይረስ ሊሆን ስለሚችል በፍፁም መክፍት የለብንም

6 ስልካችን ላይ ያሉትን ሁሉኑም Application #Update ማድረግ ለምን ቢባል አንዳንድ
Applicationኖች ከ ቆይታ ብዛት የተነሳ ወደ ቫይረስ ይቀየራሉ ስለዚህ ሁሉኑም Application በየጊዜው Update ማድረግ አለብን
ስልካችን ላይ ያሉ Applicationኖችን Update ለማድረግ መጀመሪያ ወደ PlayStore ላይ እንገባለን ከዛ (My APP) ዉስጥ እንገባለን ከዛ Update መሆን ያለበት Application ካለ እራሱ ይህን Application Update አድርግ ብሎ ይጠቁመናል ከዛ Update የሚለውን Click ማድረግ

7 Wifi በምንጠቀምበት ግዜ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ
Wifi ከፍተን በምንጠቀምበት ሰአት ብዙ
Notification ወደ ስልካችን ይገባሉ በዚህ ግዜ
ወድያውኑ Notificationኑ ፍቃድ ይጠይቀናል
(Allow or Decline) ብሎ ይጠይቀናል ?
Notificationኑ ቫይረስ ይሁን አይሁን እኛ
አናውቅም ነገርግን እኛ ችላ በማለት ወይም ትኩረት ባለመስጠት (Allow) ብለን እንፈቅዳለን በዛን ሰአት Notification መስሎ የመጣው #ቫረስ በፍጥነት ወደ ስልካችን በመግባት ስልካችንን ያበላሻል ስለዚህ ማንኛውንም Notification
ወደ ስልካችን ሲመጣ ዝምብለን ከመክፈት መታቀብ አለብን

8 ማንኛውንም Application ከሰው ስንቀበል
ስለ Applicationኑ ምንነት እና ስራ በደንብ መረዳት አለብን ይህ ማለት Applicationኑ ጎጂ ሆነ ጥሩ የሚለውን እንድናውቅ ይረዳናል
ስለዚህ ማንኛውንም Application ስልካችን
ላይ ከመጫናችን እና ከ መቀበላችን በፊት ስለ
Applicationኑ በደንብ መገንዘብ ያስፈልጋል
#ሼር_ይደረግ

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
2.0K viewsBahiru Abas, edited  15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 17:26:02 አዲስ Smart ስልክ ከመግዛታችን በፊት ማወቅ የሚገቡን 10 ወሳኝ ነገሮች!

~ መግዛት ያሰቡት Smart ሞባይል ስልክ iPhone ወይም Samsung ወይም ሌላ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም Smart ሞባይል ሲገዙ መመዘኛዎችን ማሟላቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል.... ➩ ለምሳሌ:-

1~ ፕሮሰሰር(Processor)
▣ ብዙ ግዜ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ፣ቪድዮ የሚያዩ ከሆነ ወይም የቪድዮ ኤዲቲንግ የሚሰሩ ከሆነ የስልኩ ፕሮሰሰር Qualcom Snapdragon(652/820/821/888) /ቢሆን ይመረጣል።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ ፕሮሰሰሩ MedaTek ከሆነ በቂ ነው።

2 ~ ካሜራ
▣ ፎቶ የማንሳት ልምድ ያለው ሰው የስልኩ ካሜራ 16MP (Megapixels) #በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ ግን 13MP በቂ ነው።

3 ~ ባትሪ
▣ ብዙ ሰዓት ቪድዮ ለሚያይ፣ጌም ለሚጫወት ሰው ባትሪው 4000mAh በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። - ለመካከለኛ ተጠቃሚ 3000mAh/3500mAh በቂ ነው።

4 ~ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS)
▣ የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተም(OS) ቨርዥኖች
አሉ።
- ለምሳሌ:- ኪትካት፣ሎሊፓፕ፣ማርሽሜሎ፣...ወዘተ የተባሉ ቨርዥኖች አሉ። ስለዚህ latest ቨርዥን መምረጥ ይመከራል።

5 ~ ስቶሬጅ
▣ ስልኩ በቂ የማጠራቀሚያ አቅም ቢኖረው ይመረጣል። 16GB/32GB/64GB..ከነዚህ ውስጥ መምረጥ ነው። ስልኩ ኤክስተርናል ሜሞሪ (microSD card) የሚቀበል መሆን አለበት።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ 32GB Storage በቂ ነው።

6 ~ RAM
▣ ከተቻለ ከ3/4GB Ram በላይ ቢሆን ጥሩ ነው የተለያዩ ነገሮችን በፍጥነት እንድንሰራ ይረዳናል ይህም ስልካችን ፈታ ብሎ ስራውን እንዲያከናውን ይረዳዋል።
- ለመካከለኛ ተጠቃሚ 2GB Ram በቂ ነው

7 ~ Headphone Jack
▣ HeadPhone 3.5mm audio jack ቢሆን ይመረጣል።

8 ~ USB File transfer USB 2.0
▣ በአሁኑ ጊዜ ያለ ስለሆነ ይህ ፖርት ያለው ቢሆን ይነረጣል , USB 3.0 ቢሆን ጥሩ ነው።

9 ~ Physical Size
▣ በኢንች ለናንተ የሚመቸውን መምረጥ አለባችሁ።
- አሪፍ የሚባለው Size ለምሳሌ:- 6.2inch/6.4inch/6.5inch አሪፍ የሚባል ነው።

10 የሚቀበለው የሲም ካርድ አይነት መለየት።
▣ ለምሳሌ:- Dual SIM (Nano-SIM, dual stand-by)

ለምሳሌ ከታች ያለውን Specification ተመልከቱ።

Technology : GSM / CDMA / HSPA / CDMA2000 / LTE / 5G EXPAND ▼
Dimensions: 75.8 x 164 x 8.9 mm
Weight : 205 g
SoC: MediaTek Helio P35 (MT6765)
CPU : 4x 2.3 GHz ARM Cortex-A53, 4x 1.8 GHz ARM Cortex-A53, Cores : 8
GPU : PowerVR GE8320, 680 MHz
RAM : 3 GB, 4 GB, 6 GB
Storage : 32 GB, 64 GB, 128 GB
Camera : 13MP, 16MP, 48MP, 64MP...
Selfie : 8MP, 13MP, 20MP, 32MP...
Memory cards : microSD, microSDHC, microSDXC
Display : 6.5 in, TFT, 720 x 1560 pixels, 24 bit
Battery : 5000 mAh, Li-Ion
OS: Android 10
SIMcard : Dual SIM (Nano-SIM, dual stand-by)
Wi-Fi : a, b, g, n, n 5GHz, ac, Dual band, Wi-Fi Hotspot, Wi-Fi Direct
USB: 2.0, Micro USB
Bluetooth: 5.0/5.1

አንድ ቀን ስልክ ለመግዛት ስትፈልጉ ይጠቅማችኋል #ሼር አድርጉት

ምንጭ ELA TECH

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
1.7K viewsBahiru Abas, edited  14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-25 17:25:34
1.5K viewsBahiru Abas, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 17:01:04 ስለ ሞባይል ስልክ ሃርድዌር እና ሶፍትዌር በጥቂቱ!!

ስልካችን ከመጠገናችን በፊት የሃርድዌር እና የሶፍትዌር ሃሳብ ምን እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ ። ሀርድዌር ማለት ልናየዉ ልንዳስሰዉ የምንችለዉ የስልካችን የዉስጥም ሆነ የዉጪ ክፍል ማለት ነዉ ።

ማንኛዉም የሀርድዌር ክፍል ትንሽም ሆነ ትልቅ የራሱ የሆነ ክብደትና ቀለም ይኖረዋል ። በሌላ አባባል የስልካችን የሃርድዌር ክፍል የሚዳሰስ ዕቃ ነዉ ማለት ነዉ ። ለምሳሌ ከቨር : የባትሪ ማስቀመጫ ክፍሉ : ስክሪን በተጨማሪ ስልካችን ተከፍቶ ወይም ከፈታነዉ በኋላ ልናያቸዉ የምንችል ማንኛዉም አይሲ: ሬዚስተር :ካፓሲተር :ኢንደክተር በሙሉ የስልካችን ሀርድዌር ክፍል ነዉ ።

ሶፍትዌር ማለት ስልካችን የሚሰራበት ፕሮግራም ማለት ነዉ ። ይህ ማለት በአይናችን የማናየዉ የማንዳስሰዉ ነገር ግን ስልካችን ስርአቱን ሳያዛባ እንዲሰራ የሚያደርግ መንገድ ማለት ነዉ ። የስልካችንን ሶፍትዌር እራሱን አንየዉ እንጅ ስራወቹን ማየት እንችላለን ለምሳሌ :- ስክሪናችን ላይ ስዓት : ምስል : የኔትወርክ ምልክት እንዲሁም ማንኛዉም ጥሁፍ እንዲመጣ እና እንዲሰራ የሚያደርገዉ ሶፍትዌሩ ነዉ ። እነኚህን ምስሎች ወይም ጽሑፎች በእጃችን መንካት አንችልም ።

እነኚህን ጽሑፎችና ምስሎችን ለመንካት ብንሞክር ለመንካት የምንችለዉ የሀርድዌር ክፍል የሆነዉን ስክሪኑን ነዉ ።

አንድ ስልክ በስርአቱ እንዲሰራልን ሁለቱም ክፍሎች ማለትም ሀርድዌር እና ሶፍትዌር በአግባቡ መስራት አለባቸዉ ። አንዳቸዉ እንኳ ቢበላሹ ስልካችን በስርአቱ ሊሰራ አይችልም ። የሶፍትዌሩን ችግር ለመፍታት ፍላሸር ቦክስ ያስፈልገናል /ከኮምፒውተር በተጨማሪ/። አንዳንድ ጊዜ ቀለል ያሉ የሶፍትዌር ችግሮች በኮድ ልናስተካክላቸዉ እንችላለን ። ይህ ማለት የተወሰኑ ቁጥሮችን በማስገባት ችግሩን መፍታት እንችላለን ማለት ነዉ ። ምሳሌ :-ሪስቶር ማድረግ ።

የሀርድዌር ችግር ሲገጥመን እንደችግሩ አይነትና መጠን መፍቻ : ካዉያ : ዲሲ :ቲነር: ብሎወርና የመሳሰሉትን መሣሪያዎች በመጠቀም እንጠግናለን የአንዳንድ የማይበራ ወይም ጸጥ ያለ ስልክ ችግር ሶፍትዌር ነው ወይም ሃርድዌር ነዉ ብሎ ለመለየት ስልኩ የሚያሳየንን ምልክት በማየት ወይም ዲሲ ፓወር ሰፕላይ በመጠቀም ማወቅ ይቻላል ። የስልካችንን ሶፍትዌር ወደ ተሻለ ፕሮግራም መቀየር /upgrade/ ማድረግ እንችላለን ።

አንዳንድ ጊዜ የሀርድዌርና ሶፍትዌር ሃሳብ በተሳሳተ መንገድ ሲገለጽ ይስተዋላል ።

ሃርድዌር ማለት የሚታይ ክፍል ሶፍትዌር ደግሞ የማይታይ ክፍል ብሎ ማስቀመጥ የተሳሳተ ነዉ ። ምክንቱም የስልኮችን የሶፍትዌር ስራ ማየት ይቻላል ። ለምሳሌ :- የስልኮች ስክሪን ላይ የምናየዉ የኔትወርክ ምልክት : ቀን : ስአትና ሜኑ: ስክሪንሴቨር: ጋለሪ: ፎቶግራፎች የመሳሰሉትን የሶፍትዌር ስራዎች ማየት ይቻላል ።

ሆኖም የአንድን ስልክ ሶፍትዌር ፕሮግራሙን ማየት ግን አይችልም ። ስለዚህ የሚታይ ክፍል እና የማይታይ ክፍል ብሎ ከመለየት ይልቅ ሃርድዌር የሚዳሰስ እና ሶፍትዌር የማይዳሰስ ክፍል ብሎ መለየት የተሻለነዉ ።

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
1.9K viewsBahiru Abas, edited  14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 15:13:59 በፍፁም ዳውንሎድ መደረግ የሌለባቸው አፕሊኬሽኖች ልጠቁማችሁ!!

መቼስ በዚህ ወቅት ጫኑኝ የማይል የስልክ መተግበሪያ የለም። ዓለም ራሷ የስልክ መተግበሪያዎች ውስጥ ተከናንባ እየገባች ይመስላል።
የደም ግፊት መጠንን ከሚለኩት ጀምሮ ቋንቋ መማሪያዎች፣ ቀን መቁጠሪያዎች፣ ቁርስ ምሳ ማዘዣዎች፣ ታክሲ መጥሪያዎች፣ ባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀሻዎች፤ ብቻ የሌለ ዓይነት የስልክ መተግበሪያ የለም።
ፈተናው ሐሰተኛውን ከእውነተኛው መለየት ነው። በዚህ በኩል እኛ እንርዳዎት! የሚከተሉት ሦስት የስልክ መተግበሪያዎችን ጫኑ ማለት መከራን ስልክዎ ላይ ጫኑ እንደማለት ነው።
ስልክዎን ለጤና መቃወስ የሚያጋልጡ ሐሰተኛ መተግበሪያዎች (Apps) የሚከተሉት ናቸው።
1.የባትሪ ዕድሜን እናራዝማለን የሚሉ
የሞባይል ባትሪ እንደ ቋንቋ ነው፤ ይወለዳል፣ ያድጋል ይሞታል። ልዩነቱ በምን ፍጥነት ይሞታል የሚለው ነው። በዚህ ረገድ የባትሪው ኦሪጅናልነትና የአገልግሎት ዘመን ቁልፍ ጉዳይ ነው።
አንዳንድ ጊዜ ባትሪ ቶሎ እየሞተ ሲያስቸግር ያነጫንጫል። በዚህ ጊዜ የባትሪዎን ዕድሜ ላራዝምልዎ የሚል መተግበሪያ ሲመጣ ያጓጓል። ጫኑኝ ጫኑኝ ይላል። አይቸኩሉ!
የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛ የሆነው ኤሪክ ሄርማን “የባትሪ ዕድሜን የሚያቆይ ምንም ዓይነት መተግበሪያ የለም” ይላል።
ይልቅ የባትሪ ዕድሜን ለማራዘም መፍትሄው ብዙ ዳታ የሚያሟጥጡ መተግበሪያዎችን ለጊዜው ዝም ማሰኘት ነው። እምብዛምም የማያስፈልጉ መተግበሪያዎች ከጀርባ ሆነው ባትሪን ይመዘምዛሉ።
የስልክዎ የብርሃን ድምቀት፣ የኢንተርኔት ዳታ፣ የዋይ ፋይ ማብሪያ ማጥፊያ ባትሪን ይመገባሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ስልክዎን “ናይት ሞድ” ወይም “ባትሪ ቆጥብ” የሚለው ማዘዣ ላይ ያድርጉት።
ሌላው መፍትሄ ባትሪ ኮንፊገሬሽን ላይ ገብቶ የባትሪን እድሜ እየበሉ ያሉትን ዝርዝሮች ማየትና ያንን ለይቶ ዝም ማሰኘት ነው።
2.ስልክዎን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች
ስልክዎትን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች በአመዛኙ ውሸት ናቸው። እንዲያውም ለቫይረስ ያጋልጣሉ። “ክሊን ማስትር” የሚባለው መተግበሪያ ዋንኛው ነው።
ስፔናዊው የቴክኖሎጂ አዋቂ ጆስ ጋርሺያ እንደሚለው “ክሊን ማስተር” የተባለው መተግበሪያ የስልክን ፍጥነት ይቀንሳል፣ የራሱን ገበያ ለማድመቅም ብዙ መተግበሪያዎችን እንድንጭን ያባብለናል።
ስልክዎ ትኩሳት ከተሰማው ችግር አለ ማለት ነው። የስልክ ትኩሳት በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
ለረዥም ሰዓት ለፀሐይ ብርሃን ከተጋለጠ፤ በቫይረስ ከተጠቃ፤ ወይም ደግሞ ጤናማ ያልሆነ ባትሪ ከተገጠመለት አልያም ደግሞ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት አገልግሎት ላይ ከዋለ ስልክ እንደ ብረት ምጣድ ይግላል።

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
2.0K viewsBahiru Abas, edited  12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 18:16:35
ሌላው የሚያስደንቀኝ ጥበበኛ Alex Girma Arts
ጥበብህ ይምጠቅ፤ይጥለቅ።#አሜን
እንደ እኔ አድናቂው ከሆናችሁ #ብራቮ ብንለው ደስ ይለኛል
751 viewsBahiru Abas, 15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 18:07:50
ይህ ልጅ #ጀግና ነው!! ወገኑን ለመርዳት የሚያደርገው ከልብ የመነጨ ጥረት ያስቀናል
#ብራቮ ብንለው ይገባዋል !!
1.5K viewsBahiru Abas, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 18:22:30
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ ወዳጆቼ!!
#መልካም_የዕረፍት_ቀን
በነገራችን ላይ ይህ ፔጅ እየጠቀማችሁ ነው?

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL
2.1K viewsBahiru Abas, edited  15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 17:43:36 https://www.facebook.com/100063773813503/posts/pfbid034FSQUbfo3rZtCD5PmN9KbK3tftG4VAYBuWs4hnefqw4a7nircu9RoT1PparJVQc8l/?sfnsn=mo
1.8K viewsBahiru Abas, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ