Get Mystery Box with random crypto!

Dubbo Our Lady's Catholic School ️

የቴሌግራም ቻናል አርማ dolcschool — Dubbo Our Lady's Catholic School ️ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dolcschool — Dubbo Our Lady's Catholic School ️
የሰርጥ አድራሻ: @dolcschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 780
የሰርጥ መግለጫ

This is the official telegram channel of DOLC school. You will get latest news, notices and informations of the school through this channel.
#WeMakeABetterFuture #Since1933
🌐 - http://www.dubboourladyscs.com
❓️ - @dolcschoolbot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-09 18:59:18 #ተራዝሟል

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ  ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ የካቲት 03/2013 ዓም. መራዘሙን አሳውቋል።

በ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንዲሁም በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስተካክሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደማህበራዊ ሳይንስ ቀይረው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች መቀየር የሚችሉት ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ገልጾ ይህም የሚሆነው ዩኒቨርስቲዎቹ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ስለዚህ ተማሪዎች የምርጫ ማስተካከያቸውን በጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ከዚህ ባለፈ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት የልህቀት ማዕከል ሆኖ መደራጀቱን ግንዛቤ አንዲወሰድ ብሏል።

tikvahethiopia
64 viewsSir Isaac Newton, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 20:20:10 Software የሚሰጡ ዩንቨርሲቲዎች ዝርዝር ይሄዉ !!

Mekelle Universitiy
Bahirdar Universitiy
Debre-Markos Universitiy
Wollo University
Haremaya Universitiy
Jimma Universitiy
Bulehora Universitiy
Jigjiga Universitiy
Debre-Birhan Universitiy
Arbamich Universitiy
Wachamo Universitiy
Wolkite Universitiy
Adis Ababa University
AASTU ,ASTU
INJIBARA UNIVERSITY

Muja
168 viewsSir Isaac Newton, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 20:14:04 ሜዲሲን የሚያስተምሩ ዩኒቨርስቲዎች ዝርዝር

Arbamich Universitiy
Jigjiga Universitiy
Adis Ababa University
Welikite University
Wolayta Sodo Universitiy
Wachamo Universitiy
Mizan Tepi Universitiy
Selale Universitiy
Arsi Universitiy
Wollega Universitiy
Jimma Universitiy
Hremaya Universitiy
Wollo University
Debre Tabor Universitiy
Bahirdar Universitiy
Gonder Universitiy
Adigrat Universitiy
Mekelle Universitiy
Ambo Universitiy
Debre-Birhan Universitiy
Debre-Markos Universitiy
Medda Wallabo Universitiy
Bulehora Universitiy
Hawassa Universitiy
Werabe University
Diredawa University



Highest intake capacity for medicine students -- AAU with total of 150 Human medicine students

Least Intake capacity -- Mizentepi University with total of 22 medical students
━━━━━━━━ ● ━━━━━━━━
𝑫𝒐𝒄𝒕𝒐𝒓𝒔 𝑭𝒐𝒖𝒏𝒕𝒂𝒊𝒏
177 viewsSir Isaac Newton, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 21:54:07 # ማስታወቂያ

በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ #ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-

በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ  መሆኑን እንገልጻለን።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ)  ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን  በቀጣዩ ሊንክ 

https://student.ethernet.edu.et

በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

MoE
279 viewsSir Isaac Newton, 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 04:11:04 የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስቴር ዴኤታው ዶክተር ሳምኡል ክፍሌ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ከተናገሩት የተወሰደ

፨ከ50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሙሉ በባቻቸው ፍሬሽማን ኮርስ ይጀምራል።

፨ከ50% በታች ያመጡ ተማሪዎች ሶስት አማራጭ አላቸው
1) *መንግስት የሚሰጠውን ሁለተኛ ዕድል በመጠቀም የማካካሻ ትምህርት መውሰድ እና አንድ ባች ዝቅ ብሎ ፍሬሽማን መጀመር።(መቁረጫ ነጥብ ለሚያሟሉ)
*ከመንግስት ዩንቨርሲቲ ውጭ በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርት ተምረው በድጋሚ የወደቁባቸውን ትምህርት በመከታተል ቀጣይ ዓመት በግል ፍሬሽማን ኮርስ መጀመር

2) ከቀጣይ ተፈታኞች ጋር በግል ድጋሚ መፈተን

3)ቴክኒክና ሙያ መሰልጠን

በመንግስት ስፖንሰርነት ማካካሻ የሚወስዱ የ#100ሺህ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ከ10-15 ቀን ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል።


━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
FBC
557 viewsSir Isaac Newton, 01:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 20:01:49 ALERT FOR Grade 12

ዘንድሮ ዩንቨርሲቲ ከሚገቡ ተማሪዎች ውስጥ Lazy ተማሪ የለም፣ እና የ ፈለጋችሁት ፊልድ ለመግባት ከ መቼውም በላይ መስራት ያለባችሁ ይህን የ አንደኛ ሴሚስተር ነጥብ ነው! እውነት ለመናገር አንዳንዴ over Confidence እና ጎበዝ እኔ ብቻ ነኝ ማለት ብቸኛ ጥቅሙ ከ ሌሎች አንሰህ መገኘት ነው።
የትምህርት ዓለም ውስጥ፣ ጎበዝ ማለት ጠንክሮ የሚያነብ ነው ። UEE 600 ወይስ 500 ስላመጣ አንተ/አንቺ ጎበዝ ነሽ፣ ነይ ፋርማሲ ግቢ or ሜድሲን ግቢ የሚልሽ የለም። ኢንትራንስ ነጥብ እንዳለ ሆኖ፣ በጣም ወሳኙ ነገር GPA ነው ። ስለዚህ አትሸወዱ plz.

So, ከ አሁኑ ተዘጋጁ፣ 12 ዓመት ለፍታችሁ ያመጣችሁትን ነጥብ፣ ፍሬሽማን ካልሰራችሁ ምንም ዋጋ አይኖረውም

የትም ፊልድ ለመግባት GPA በጣም አስፈላጊ ነው። Engineering, Medicine, pharmacy... እና ሌሎችም አሪፍ GPA ከሌለህ የማግኘት እድልህ ይጠባል።

ፍሬሽማን ደግሞ ካነበባችሁ በጣም ቀላል ነው ፣ ደግሞ A+ Academy እንዴት እንደምያስተምሩ ፣ ለ ብዙዎቻችን እነሱ ባለውለታችን ናቸው
እናንተም ግዜው ሲደርስ አትሸወዱ፣ ተመዝገቡ፣ ውጤት ስሩ ።
ለ ዲፓርትመንት ምርጫ እና CoC ፈተናዎች ደግሞ በየ ዩንቨርስቲዎች እዚህ ቻናል ላይ ያገኛሉ። ከዚህ ሁሉ በኋላ ደግሞ ፣ ወደ ፈለጋችሁ ፍልድ እንደምትገቡ እርግጠኛ ነኝ

First Generation University የገባችሁ ተማሪዎች በተለይ በጣም መስራት አለባችሁ። ምንም ማጋነን የሌለው፣ Competition ይበዛል። ሲቀጥል First Generation University የ ቅደመ-ምርቃ ተማሪዎችን ብዛት እየቀነሱ ነው ። ለምሳሌ በ አስር አመት ውስጥ አ.አ ዩኒቨርሲቲ undergraduate ተማሪ ላያስተምሩ ይችላሉ እንደ እቅድ ከሆነ። ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ Medicine ተማሪዎች 21 ብቻ ለመውሰድ እያቀዱ ነው። ይህ ግን ዘንድሮ ወይም ቀጣይ ዓመት ነው ማለት አይደለም ነገር ግን እቅድ ነው ።
ከሁለት ዓመት በፊት ጅማ ዩኒቨርሲቲ 150 የሰው ህክምና ተማሪዎች እየተቀበሉ ነበር። አሁን ግን ለ ሜዲስን 80 ተማሪ ብቻ ይቀበላሉ።
ስለዚህ ኢንትራንስ ያለፋችሁ ተማሪዎች፣ በደንብ ፍሬሽማን ለመስራት ተዘጋጁ። በፊት ብዙ ተማሪዎች ኢንትራንስ አጭበርብረው ስለሚገቡ፣ CoC ፈተና ላይ ይወድቃሉ ፣ ዘንድሮ ግን ታሪኩ አይደገምም በርትቶ የሰራ በልጦ ይገኛል

━━━━━━━━ ● ━━━━━━━━
𝑫𝒐𝒄𝒕𝒐𝒓𝒔 𝑭𝒐𝒖𝒏𝒕𝒂𝒊𝒏
@coctutorial
@coctutorial
Join           sharE
438 viewsSir Isaac Newton, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 20:01:49
#ASTU #AASTU

በ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ውጤት ያመጣችሁና ወደ ሁለቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ትምህርታችሁን መከታተል ለምትፈልጉ ተማሪዎች ስለ መግቢያ፣ምዝገባ እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ በቀጣይ የሚገለፅ በመሆኑን ተማሪዎች በትዕግስት ትጠብቁ ዘንድ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አሳውቋል።

━━━━━━━━ ● ━━━━━━━━
𝑫𝒐𝒄𝒕𝒐𝒓𝒔 𝑭𝒐𝒖𝒏𝒕𝒂𝒊𝒏
@coctutorial
@coctutorial
Join           sharE
346 viewsSir Isaac Newton, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 15:45:34 ማስተካከያ

ከትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ተነስቶ ለተማሪዎች ማብራሪያ በሰጠው ላይ ማስተካከያ አድርጓል።

29,909 ተማሪዎች መቼ ወደ ግቢ ይገባሉ የተባለው ገና አልተወሰነም። መግለጫው ላይ ከሰማችሁ በሚቀጥለው አመት ይባል እንጂ ገና ከውሳኔ እንዳልተደረሰ እና የነሱስ ምደባ መቼ ነው የሚለው ገና ነው።

ሌላው እነዚህ ከ 50 በላይ ያመጡ ተማሪዎች Freshman Course ይወስዳሉ ተብሏል። መቼ የሚለው ግን አልታወቀም። ስለዚህ Freshman አይኖርም የተባለው በስህተት ነው።

ለ 50% ቅርብ የሆኑት 100ሺ ተማሪዎች ገና አልተለዩም። ከተለዩ በኋላ በምን መልኩ ክለሳ ይወስዳሉ፣ የት ሆነው ይወስዳሉ፣ ለስንት ጊዜ ነው የሚወስዱት የሚሉ ጥያቄዎችም በዛው ጊዜ መልስ ያገኛሉ።

ስለ Astu, Aastu, Phawulos ውድድር ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ያስቀምጣል። አብዛኛው ተማሪ የጨነቀው ደግሞ College መግባት እችል ወይ? የሚለው ነው።

College'ን አስመልክቶ ምንም አልተባለም። መቼስ ባዶ ሆነው አይቀሩም። ስለዚህ በተስፋ መጠበቅ ነው።

በአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ቅሬታን መልስ ከሰጣ በኋላ ትንታኔ ይሰጣል። ውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ እስከ ጥር 26 ድረስ ቅሬታ ማቅረብ ትችላላችሁ።



የትምህርት ሚኒስቴር ትክክለኛ የተረጋገጡ ዜናዎችን ለ ጓደኛዎ ያጋሩ
ኢትዮ ዩኒቨርስቲ
619 viewsSir Isaac Newton, 12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 15:50:19
#Update

በ2014 የትምህርት ዘመን 899 ሺህ 520 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ወስደዋል።

ከነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡት 29 ሺህ 909 ወይም 3 ነጥብ 3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ ብለዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል።

ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ጠቁመዋል። ተማሪዎቹ “የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርሲቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል። #EI

@tikvahuniversity
560 views𝙺𝚊𝚕𝚎𝚋 ️, 12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 15:26:17
ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግባል።

@tikvahethiopia
446 views𝙺𝚊𝚕𝚎𝚋 ️, 12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ