Get Mystery Box with random crypto!

#ተራዝሟል ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ  ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ የካቲት 03/2013 | Dubbo Our Lady's Catholic School ️

#ተራዝሟል

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ  ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ የካቲት 03/2013 ዓም. መራዘሙን አሳውቋል።

በ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንዲሁም በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስተካክሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደማህበራዊ ሳይንስ ቀይረው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች መቀየር የሚችሉት ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ገልጾ ይህም የሚሆነው ዩኒቨርስቲዎቹ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ስለዚህ ተማሪዎች የምርጫ ማስተካከያቸውን በጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ከዚህ ባለፈ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት የልህቀት ማዕከል ሆኖ መደራጀቱን ግንዛቤ አንዲወሰድ ብሏል።

tikvahethiopia