Get Mystery Box with random crypto!

# ማስታወቂያ በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 | Dubbo Our Lady's Catholic School ️

# ማስታወቂያ

በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ #ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-

በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ  መሆኑን እንገልጻለን።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ)  ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን  በቀጣዩ ሊንክ 

https://student.ethernet.edu.et

በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

MoE