Get Mystery Box with random crypto!

Dire Soccer

የቴሌግራም ቻናል አርማ diresoccer — Dire Soccer D
የቴሌግራም ቻናል አርማ diresoccer — Dire Soccer
የሰርጥ አድራሻ: @diresoccer
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.40K
የሰርጥ መግለጫ

የኢትዮዽያ ኘሪምየር ሊግ አዳዲስ መረጃዎች
Join Us :- @DireSoccer
ሀሳብና አስተያየት:- @direDire
የሐሳብ መድረክ :- @Diresoccerfamily
የፌስቡክ ድረ ገፅ :-
https://m.facebook.com/diresoccer

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 19:32:22
ሊዲያ ታፈሰ ለዓለም ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ጥሪ ደርሷታል

ኢትዮጵያዊቷ ዳኛ በህንድ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የዓለም ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ግልጋሎት እንድትሰጥ በፊፋ ጥሪ ተደርጎላታል፡፡

የዓለም ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ ጨዋታ ውድድር ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 20 ድረስ በህንድ አስተናጋጅነት ይደረጋል፡፡ የውድድር የበላይ አካል የሆነው ፊፋ በዳኝነት የሚያገለግሉ ዳኞችን ከተለያዩ ሀገራት መምረጡንም ይፋ አድርጓል፡፡ አስራ አራት ዋና፣ ሀያ ስምንት ረዳት እና አስራ ስድስት የቪዲዮ ዳኞችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ከአፍሪካ ሁለት የቪዲዮ ዳኞች (VAR) ተካተዋል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰም ከአፍሪካ ከተመረጡ ሁለት የቪዲዮ ዳኞች መካከል አንዷ ሆናለች፡፡ ሌላኛዋ የኢሲዋቲኒ ዜግነት ያላት ቪያና ሊቺያ ሌላኛዋ የቪዲዮ ዳኝነት ግልጋሎትን የምትሰጥ ይሆናል፡፡

ፊፋ ለዚህ ውድድር ከአህጉረ አፍሪካ ሁለት ዋና እና አራት ረዳት ዳኞችንም ለውድድሩ ሲጠራቸው በህንድ በሚደረገው ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ ላይ ጥሩ ብቃት የሚሳዩ ዳኞች በቀጣዩ ዓመት በአውስትራሊያ ለሚደረገው የሴቶች አለም ዋንጫ ላይ በቀጥታ እንደሚመርጥ ታውቋል፡፡

soccer ethiopia

@diresoccer
276 viewsDire Soccer, 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:25:06
ሀዲያ ሆሳእና ሴኔጋላዊ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

ሀድያ ሆሳዕና ሦስተኛ የውጪ ዜጋ ተጫዋች በይፋ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ መሪነት በክለቡ መቀመጫ ከተማ ሆሳዕና የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን እየከናወነ የሚገኘው ሀድያ ሆሳዕና ከጋናዊዎቹ ሪችሞንድ ኦዶንጎ እና ስቴፈን ኒያርኮ ቀጥሎ ሶስተኛ የውጪ ዜጋ ተጫዋቹ የሆነውን ሴኔጋላዊ ግብ ጠባቂ ፓፔ ሰይዱ ኒዲያዬን በአንድ ዓመት ውል በዛሬው ዕለት የግሉ አድርጓል፡፡

soccer ethiopia

@diresoccer
232 viewsDire Soccer, 16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:18:54
አብዲ ቦሩ አለም ገና እግር ኳስ ፕሮጀክት ያዘጋጀው የ አሸናፊ ዎች አሸናፊ ውድድር በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ።

በ ዛሬው እለት ለ ሁለት ሳምንት ሲደረግ የቆየው ውድድር የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን በ ውድድሩ :-

     የፀባይ ዋንጫ : አምቦ ሴኒያስ ኮሌጅ
     ሀ 15 : ለቡ
     ሀ 17 : ጅማ ታዳጊ
      ክለብ : ዳለቲ  አሸናፊ
በመሆን የዋንጫ እና የ ማለያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን
በየ እድሜ እርከኑ ኮኮብ ለሆኑ ተጨዋቾች የኮኮብ ሸልማት ተበርክቷል !!

በተጨማሪ የውድድሩ ማማር አስተዋፀ ለደረጉ አካላት የምስጋና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።

@diresoccer
260 viewsDire Soccer, 16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:13:22
ማርቲን ዱብራቭካን ወደ ማንችስተር ዩናይትድ Here ሙሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፣ የውሰት ስምምነት ከ£5m የግዢ አማራጭ  ጋር የግዴታ አይደለም።

@diresoccer
342 viewsDire Soccer, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:36:20
#የእለቱ_የባህርማዶ #ዜናዎች

#ማንችስተር_ዩናይትድ ከ #አርሰናል !
በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ከምሽቱ 12:30  ጀምሮ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ሁለቱን ቡድኖች ሲያገናኝ ጨዋታውን የሚመሩት ዳኛ ይፋ ሆኗል  ።

የ 41 ዓመቱ የመሐል ዳኛ ፖል ቴርኒ ይህን ተጠባቂ ጨዋታ በበላይነት እንዲመሩ መመረጣቸው ተገልጿል ።


#ሉካስ_ፓክዌታ ከ ሊዮን ወደ ዌስታሀም የሚያደርገዉ ዝዉዉር ጨርሷል :: እስከ 2027 የ ሚያዉለዉን ኮንትራት ፈርሟል


#ሬናን_ሎዲ በውሰት ከ አትሌቲኮ ማድሪድ ኖቲንግሃም ፎረስትን ተቀላቅሏል በ€5m ክፍያ እና በ €30m የ ግዢ አማራጭ ክለቡን ተቀላቅሏል።
ሬናን ሎዲ የኖቲንግሀም ፎረስት 17ተኛ ፈራሚ ሆኗል።


#አርጀንቲና በ 2022 የአለም ዋንጫ የሚጠቀሙትን ሁለተኛ ማልይ ይፋ አድርገዋል

@diresoccer
337 viewsDire Soccer, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:30:46
የሳምንቱየተመረጡየባህርማዶ ዜናዎች

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ወደ ኦማን በማቅናት ለአል ሱዋይክ ፊርማውን ያኖረው ኡመድ ኡኩሪ በመጀመሪያው ጨዋታ ግብ ማስቆጠር ችሏል ።

ኡመድ ኡኩሪ ቡድኑ በዛሬው ዕለት አል ኢቲሀድን 2 ለ 0 ባሸነፈበት መርሐ ግብር በሰባ ስምንተኛው ደቂቃ ሁለተኛውን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳርፏል ።

የኡመድ ኡኩሪ ቡድን አል ሱዋይክ በሁለት ጨዋታዎች ስድስት ነጥቦችን በመሰብሰብ የአሸናፊነት ጉዟቸውን አስቀጥለዋል ።

      * ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ከአፍሪካ ክለቦች ብቸኛ በመሆን FIFA 23 ላይ ተካተዋል።


      * የ2022/23 የውድድር ዘመን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና የዩሮፓ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ።


   * ሮበርት ሌቫንዶውስኪ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የቀድሞ ክለቡን ባየርሙኒክን በባርሴሎና ማሊያ የሚገጥም ይሆናል ።


◉ በእያንዳንዱ የአውሮፓ ከፍተኛ አምስት ሊጎች የሊግ ዋንጫ ያነሳ የመጀመሪያው አሰልጣኝ
◉ አራት የቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታዎችን ያሸነፈ የመጀመሪያው አሰልጣኝ
◉ የመጀመርያው አሰልጣኝ አራት የUEFA ሱፐር ካፕ ዋንጫን ያሸነፈ
ካርሎ አንቸሎቲ የ UEFA የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን ሲመረጥ 
     * የ UEFA የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል የሪያል ማድሪዱ ተጫዋች ካሪም ቤንዜማ ተመርጧል።


  * ሳሪና ዊግማን የአመቱ ምርጥ የሴቶች የአውሮፓ እግር ኳስ አሰልጣኝ አሸናፊ ሆና ስትመረጥ
      * የባርሴሎናዋ ተጫዋች አሌክሲያ ፑቴያስ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የሴቶች የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብላ ተመርጣለች።


      * አንቶኒ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እየተጠበቀ የነበረው ዝውውር በስተመጨረሻ ተጠናቋል።

@diresoccer
375 viewsDire Soccer, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:53:03
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ተገባዷል

በኢ ሲ ኤ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የቀጠለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በባሕል እና ስፖርት ሚንስቴሩ ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የመክፈቻ ንግግር ከተከፈተ በኋላ የጉባኤው አጀንዳዎች ቀርበው ፀድቀው የፌዴሬሽኑ የጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ላይ የተሰሩ ሥራዎችን አብራርተዋል። በማስከተል የፋይናንስ ሀላፊው አቶ ነብዩ ደመሴ የፋይናንስ ሪፖርት አቅርበዋል። አቶ ነብዩ በገለፃቸው ፌዴሬሽኑ በበጀት ዓመቱ 235,783,534.50 ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ገቢ አድርጎ 252,805,711.33 ወጪ መደረጉን ይፋ አድርገዋል። የውጪ ኦዲት ሪፖርትም ቀርቧል።

በጉባኤው የአፋር እግርኳስ ፌዴሬሽን እንደ አጀንዳ ያቀረበውና ተወካዩ አቶ ዓሊሚራ መሐመድ በተወዳዳሪነት ይያዙልኝ ባለው መሠረት ግለሰቡ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። በተጨማሪም ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አዲሱ የጉባኤው አባል እንዲሆን የቀረበው ጥያቄ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

በመጨረሻም የወቅቱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ለጉባኤው አባላት እግርኳሱ እንዲያድግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሥራዎችን እንዲሰሩ አደራ ብለው የመዝጊያ ንግግራቸውን አድርገው የዛሬው ጉባኤ ተገባዷል።

በነገው ዕለት የፕሬዝዳንት እና የሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ የሚደረግ ይሆናል።

EFF

@diresoccer
251 viewsDire Soccer, 11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:21:39 #ትኩረት

በዛሬው የትኩረት ፕሮግራማችን ድሬዳዋን ወክሎ በአብዲ ቦሩ አለም ገና ፕሮጀክት አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ 2014 የክረምት የክልሎች ክለቦች የአሸናፊዎች አሸናፊ ሀገር አቀፍ የእግር ኳስ ውድድር እየተሳተፈ ያለውን ድሬ ከዚራ እግርኳስ ክለብን እንቃኛለን።

ካለማንም የፋይናንስ እገዛ በግል ተነሳሽነት በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ባለው በአብዲ ቦሩ አለም ገና ፕሮጀክት አዘጋጅነት የ 2014 የክረምት የክልሎች ክለቦች የአሸናፊዎች አሸናፊ ሀገር አቀፍ የእግር ኳስ ውድድር በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ከ15 አመት በታች የድሬ ከዚራ እግርኳስ ክለብ በውድድሩ ላይ አመርቂ ውጤትም እያስመዘገበ ሲገኝ በውድድሩ ጅማ ተስፋን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረስ ችሏል።

ክለቡ ባለፈውም አመት በዚሁ ውድድር ላይ ከ17 አመት ታዳጊዎችን ማወዳደሩ ይታወሳል።

ይህ ተግባር ለሌሎችም ታዳጊዎች መነሳሳትን ከመፍጠሩም ባሻገር የድሬዳዋን የቀድሞ ስሟንና ለመመለስም ይረዳታልተብሎ ይታሰባል ።

ታዲያ የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም እግርኳስ ፌደሬሽኑ እንዲህ አይነቱን በራሱ ተነሳስቶ ታዳጊዎችን ለማሳየት እና ለማሳደግ የሚጥሩ ክለቦችን ለምን መደገፍ አቃተው ብለኅ ጥያቄያችንን እንሰነዝራለን???

ድሬ ሶከር ክለቡ እንደዚህ አይነት ውድድር ላይ ለመሳተፍ ካሰበ ቀደም ብሎ የሚመለከተውን አካል የድጋፍ ጥያቄ ስለመጠየቃቸው የክለቡን ሀላፊ ጠይቆ ያገኘው ምላሽ ሁሉንም የሚመለከተውን አካል መጠያቃቸውንና ከከንቲባ ቢሮ እስከ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ድረስ ጥያቄውን ይዘው መሄዳቸውን ነገር ግን የተሰጣቸው ምላሽ የበጀት እጥረት ስላጋጠመን አሁን ላይ ምንም አይነት ድጋፍ መደገፍ አንችልም በማለት መልስ እንደሰጧቸው ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት ከማህበረሰቡ በሰበሰቡት ፋይናንስ ወደ ውድሩ ለመሄድ እንደተገደዱም ለማወቅ ችለናል።

በድሬዳዋ ከተማ እግርኳሱ ላይ የሚሰሩ አመራሮችና ባለሀብቶች በግል ተነሳሽነት ታዳጊዎችን ለማሳየትና የተሻለ እይታ እኅዲኖረው እንዲሁም ከቦታቦታ እያዘዋወረ ለሚያሳይ ክለብ ከማንም የተሻለ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል።

በክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከተማዋን ወክለዉ ከሚሄዱ ክለቦች ባልተናነሰ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል።

ድሬ ሶከር ታዳጊዎች  ትኩረት እንዲሰጣቸው በማንኛውም ሰአት ድምፅ ይሆናቸዋል!!!

የዚህ ሳምንት የትኩረት ፕሮግራማችንን በዚሁ እናበቃለን ሳምንት በሌላ ተመሳሳይ ፕሮግራም እስከምንገናኝ ባባይ

@diresoccer
246 viewsDire Soccer, 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:21:20
230 viewsDire Soccer, 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:15:59
#ድሬ_ስፖርት

አሰልጣኝ ቡዛየው ጀንበሩ

እግር ኳሱን በተግባር የሚያውቁት ተጫውተው አሰልጥነው የኢትዮጵያን እግር ኳስ ለመምራት ፍላጎቱና እውቀቱ ላላቸው በር የከፈተ ተግባር ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከወራት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በኡጋንዳ በተዘጋጀው በሴካፋ የ ሀ20 የሴቶች ውድድር ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ድል ከአሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል ጋር ያስመዘገበችው አሰልጣኝ ቡዛየው ጀንበሩ ቀደም ሲል በተጫዋችነት በአሰልጣኝነት በድሬደዋ ከነማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምናውቃት በ2014 ዓም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በስራ አስፈፃሚነት ለመወዳደር እጩ የቀረበች ብቸኛዋ እግር ኳሱን በተግባር የምታውቅ ብቸኛዋ ሴት ያሰኛታል።

ገና በእግር ኳስ አሰልጣኝነት ረጅም ርቀት የምንጠብቃት አሰልጣኝ ቡዛየው ጀንበሩ ለምን ወደ አመራርነት መጣች የብዙዎች ጥያቄ ሲሆን መልሱ ግን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ችግር ከተጫዋች ከአሰልጣኝ በተሻለ በተግባር የሚያውቀው ስለሌለ ወደ አመራርነት መምጣቷ መልስ ሲሆን ለብዙ ዋጋ ላልተሰጣቸው ተጫውተው እንዲሁም አሰልጥነው ላለፉ ወደ አመራርነት ለመምጣት ለሚፈልጉ በር የሚከፍት ነው።

በዛሬው የድሬ ስፖርት ፕሮግራማችን ድሬዳዋን ወክላ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስ ውስጥ እየተወዳደረች የምትገኘውን አሰልጣኝ ቡዛየሁ ጀንበሩ በጥቂቱ እንዲህ ቃኘናት ሳምንት በሌላ ተመሳሳይ ፕሮግራም ይዘን እንቀርባለን።

ሻሎም

@diresoccer
328 viewsDire Soccer, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ