Get Mystery Box with random crypto!

#ትኩረት በዛሬው የትኩረት ፕሮግራማችን ድሬዳዋን ወክሎ በአብዲ ቦሩ አለም ገና ፕሮጀክት አዘጋጅነ | Dire Soccer

#ትኩረት

በዛሬው የትኩረት ፕሮግራማችን ድሬዳዋን ወክሎ በአብዲ ቦሩ አለም ገና ፕሮጀክት አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ 2014 የክረምት የክልሎች ክለቦች የአሸናፊዎች አሸናፊ ሀገር አቀፍ የእግር ኳስ ውድድር እየተሳተፈ ያለውን ድሬ ከዚራ እግርኳስ ክለብን እንቃኛለን።

ካለማንም የፋይናንስ እገዛ በግል ተነሳሽነት በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ባለው በአብዲ ቦሩ አለም ገና ፕሮጀክት አዘጋጅነት የ 2014 የክረምት የክልሎች ክለቦች የአሸናፊዎች አሸናፊ ሀገር አቀፍ የእግር ኳስ ውድድር በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ከ15 አመት በታች የድሬ ከዚራ እግርኳስ ክለብ በውድድሩ ላይ አመርቂ ውጤትም እያስመዘገበ ሲገኝ በውድድሩ ጅማ ተስፋን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረስ ችሏል።

ክለቡ ባለፈውም አመት በዚሁ ውድድር ላይ ከ17 አመት ታዳጊዎችን ማወዳደሩ ይታወሳል።

ይህ ተግባር ለሌሎችም ታዳጊዎች መነሳሳትን ከመፍጠሩም ባሻገር የድሬዳዋን የቀድሞ ስሟንና ለመመለስም ይረዳታልተብሎ ይታሰባል ።

ታዲያ የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም እግርኳስ ፌደሬሽኑ እንዲህ አይነቱን በራሱ ተነሳስቶ ታዳጊዎችን ለማሳየት እና ለማሳደግ የሚጥሩ ክለቦችን ለምን መደገፍ አቃተው ብለኅ ጥያቄያችንን እንሰነዝራለን???

ድሬ ሶከር ክለቡ እንደዚህ አይነት ውድድር ላይ ለመሳተፍ ካሰበ ቀደም ብሎ የሚመለከተውን አካል የድጋፍ ጥያቄ ስለመጠየቃቸው የክለቡን ሀላፊ ጠይቆ ያገኘው ምላሽ ሁሉንም የሚመለከተውን አካል መጠያቃቸውንና ከከንቲባ ቢሮ እስከ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ድረስ ጥያቄውን ይዘው መሄዳቸውን ነገር ግን የተሰጣቸው ምላሽ የበጀት እጥረት ስላጋጠመን አሁን ላይ ምንም አይነት ድጋፍ መደገፍ አንችልም በማለት መልስ እንደሰጧቸው ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት ከማህበረሰቡ በሰበሰቡት ፋይናንስ ወደ ውድሩ ለመሄድ እንደተገደዱም ለማወቅ ችለናል።

በድሬዳዋ ከተማ እግርኳሱ ላይ የሚሰሩ አመራሮችና ባለሀብቶች በግል ተነሳሽነት ታዳጊዎችን ለማሳየትና የተሻለ እይታ እኅዲኖረው እንዲሁም ከቦታቦታ እያዘዋወረ ለሚያሳይ ክለብ ከማንም የተሻለ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል።

በክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከተማዋን ወክለዉ ከሚሄዱ ክለቦች ባልተናነሰ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል።

ድሬ ሶከር ታዳጊዎች  ትኩረት እንዲሰጣቸው በማንኛውም ሰአት ድምፅ ይሆናቸዋል!!!

የዚህ ሳምንት የትኩረት ፕሮግራማችንን በዚሁ እናበቃለን ሳምንት በሌላ ተመሳሳይ ፕሮግራም እስከምንገናኝ ባባይ

@diresoccer