Get Mystery Box with random crypto!

#ድሬ_ስፖርት አሰልጣኝ ቡዛየው ጀንበሩ እግር ኳሱን በተግባር የሚያውቁት ተጫውተው አሰልጥነ | Dire Soccer

#ድሬ_ስፖርት

አሰልጣኝ ቡዛየው ጀንበሩ

እግር ኳሱን በተግባር የሚያውቁት ተጫውተው አሰልጥነው የኢትዮጵያን እግር ኳስ ለመምራት ፍላጎቱና እውቀቱ ላላቸው በር የከፈተ ተግባር ።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ከወራት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በኡጋንዳ በተዘጋጀው በሴካፋ የ ሀ20 የሴቶች ውድድር ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ድል ከአሰልጣኝ ፍሬው ሀይለገብርኤል ጋር ያስመዘገበችው አሰልጣኝ ቡዛየው ጀንበሩ ቀደም ሲል በተጫዋችነት በአሰልጣኝነት በድሬደዋ ከነማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምናውቃት በ2014 ዓም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በስራ አስፈፃሚነት ለመወዳደር እጩ የቀረበች ብቸኛዋ እግር ኳሱን በተግባር የምታውቅ ብቸኛዋ ሴት ያሰኛታል።

ገና በእግር ኳስ አሰልጣኝነት ረጅም ርቀት የምንጠብቃት አሰልጣኝ ቡዛየው ጀንበሩ ለምን ወደ አመራርነት መጣች የብዙዎች ጥያቄ ሲሆን መልሱ ግን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ችግር ከተጫዋች ከአሰልጣኝ በተሻለ በተግባር የሚያውቀው ስለሌለ ወደ አመራርነት መምጣቷ መልስ ሲሆን ለብዙ ዋጋ ላልተሰጣቸው ተጫውተው እንዲሁም አሰልጥነው ላለፉ ወደ አመራርነት ለመምጣት ለሚፈልጉ በር የሚከፍት ነው።

በዛሬው የድሬ ስፖርት ፕሮግራማችን ድሬዳዋን ወክላ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስ ውስጥ እየተወዳደረች የምትገኘውን አሰልጣኝ ቡዛየሁ ጀንበሩ በጥቂቱ እንዲህ ቃኘናት ሳምንት በሌላ ተመሳሳይ ፕሮግራም ይዘን እንቀርባለን።

ሻሎም

@diresoccer