2022-06-15 15:45:20
የ2014 ዓ/ም ሁለተኛው መንፈቀ ዓመት የ10 ክፍል አማርኛ መለማመጃ ጥያቄዎች
፩.ልዩ የሆነው የቱ ነው?
1.ሀ/አቆማዳ ለ/ ቀልቀሎ ሐ/ጎተራ መ/ስልቻ
2 .ሀ/ ስንፍና ለ/ ውንብድና ሐ/ሀኬት መ/ልግም
3.ሀ/ ጠለቀ ለ/ ቀዳ ሐ/ጠጣ መ/ ደነበቀ
4.ሀ/አሽሙር ለ/አግቦ ሐ/ሽሙጥ መ/ሙገሳ
፪.በ "ሀ" ረድፍ የቀረቡትን ፈሊጣዊ ንግግሮች ከ"ለ" ረድፍ ፍቻቸው ጋር አዛምዱ፡፡
ሀ ለ
5. የብረት ልጥ ሀ/ልፍስፍስ
6. መሬት አሟሸ ለ/አሽሙር
7.አረቂ ወገብ ሐ/ሰው ባልተቀበረበት ቦታ ተቀበረ
8.አግቦ መ/ወገበ ቀጭን
ሠ/ቀዝቃዛ
፫.የሚከተሉትን ቅኔዎች ህብረቃል፣ሰምና ወርቅ ለዩ፡፡
9.ቁማር ጨዋታ ተጫውቼ፣
አጨብጭቤ ቀረሁ ተረትቼ፣
ምነው እድሌ በሰመረ ፣
ዘውዱን ገልብጨው በነበረ፡፡
10.አንገት የለሽም ወይ አዙሮ የሚያይ፣
ሲመሽ ብር ብለሽ ትሔጃለሽ ወይ?
11.ድሮም ምኒልክን ድመት አይወዳቸው፣
ዘንድሮም ጣይቱን አነር ገደላቸው፡፡
፬.የሚከተሉትን ሀረጋት በየምድባቸው ለይታችሁ አስቀምጡ፡፡
12.ወሬኛ አሮጊት 13.ከክፍለ ሀገር
14.ጎበዝ ተመራማሪ 15.እንደ ወንድሙ ቶሎ
16.ከማንኩሳ መጣ 17.ቀላል ጥያቄ
፭.የሚከተሉትን ጥገኛ ምዕላዶች የእርባታና የምስረታ በማለት ለዩ፡፡
18.-ህ 19.-ነት 20.-ኣት 21.-አዊ 22.ኣቸው 23.-ኦሽ 24.-ኧኛ
፮.እንደ አጠያየቃቸው መልሱ፡፡
25.የድርሰት አይነቶችን በመዘርዘር ምንነታቸውን ግለፅ/ጪ፡፡
26.ግለሰብ ለመስሪያ ቤት በሚፅፈው ማመልከቻና መ/ቤት ለመ/ቤት ወይም
ለግለሰብ በሚፅፈው ደብዳቤ መካከል ምን ምን ልዩነቶች አሉ?
27.ድሮ የኛ ቤት ሰው ቀንዳም ቀንዳም ሙገር ሙገር ነበር
ጎዳው ጎዳው ቀረ ቀንድ ቀንዱ ቢሰበር፡፡የሚለው ቃላዊ ግጥም ድምፀት ምንድነው?
28.የቃላት ፍካሬያዊ ፍች ሲባል ምን ማለት ነው?
29.የአረፍተ ነገር ስልቶችና አይነቶችን ዘርዝሩ፡
2.0K views12:45