Get Mystery Box with random crypto!

Dejen Times

የቴሌግራም ቻናል አርማ dejentimes — Dejen Times D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dejentimes — Dejen Times
የሰርጥ አድራሻ: @dejentimes
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.97K
የሰርጥ መግለጫ

ተመራጭ የመረጃ ምንጭዎ

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-08 20:04:33
ደጀን ኆኽተ ምስራቅ አበ ብዙኃን አብርሃም ወ መድኃኔዓለም ካቴድራል ቤተክርስቲያን
1.9K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 19:29:32
አዲስ አበባ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም
2.0K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 15:08:30
"ሰብዓዊ መብታችንን ማክበር የተሳነው መንግሥት ፤ የልብሳችንን ቀለም ሊመርጥልን አይችልም!"
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ
2.5K views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 13:48:37
የአሐዱ ባንክ ሰራተኞች
2.6K views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 12:46:59
2.7K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 12:46:53 ኑ ለቅሶ እንድረስ
በገጣሚ ምስራቅ ተፈራ

ያሳደግችኝ ደብር ተቀመጠች አሉኝ ለቅሶ
ውለታዋ ተዘንግቶ ክብር ማዕረጓ ተድሶ
በትዕቢት ተረማመደ ቅጥር ግቢዋን ጥሶ
ማር ይዘንባል ማር (×3) ነበር ዜማ ቅኝቷ
ስጋጃው በደም ራሰ ጥይት ዘነበ ከቤቷ

ሰንደቅ አላማ ነበር የዘለ ዕለት ውበቷ
ኑ እንድረሳት ለቅሶ ማቅ ለብሷል ጉልላቷ
እንዳትካስ ለብድሯ ወርቀዘቦ ተንቆጥቁጣ
በምን ቃል ይገለፃል በምን ቃል ይገለፃል
በውን ቆሞ እንደማየት ባዳፋ ጫማ ተረግጣ

ቅጥሯን ለተዳፈረ ለናቃት ይስጠው መጥኔ
የአለምን ሀይል ተመክቶ የታበየ ለኩነኔ
አለም በቃኝ ብለው ምለው ያፀኗት በምናኔ
ኑ እንላቀስ ምዕመን ያልሰማ ይስማ መርዶ
ደብራችን አንብታለች መጋረጃዋ ተቀዶ
ደብረ ሀይል ቅዱስ ራጉኤል የልጅነቴ
በመልዐክ ሀይል ምልጃ የፀናችልኝ ህይወቴ
የአባ መሸ ኪላራይሶ የገብረ ኪዳን ሰንበቴ
የአዝኖና መጠጊያ የነብስ ስጋ ቋቴ
የሀይማኖት መሰረቴ
አፍ መፍቻ ትምህርት ቤቴ
እስኪ ተጠየቁ እስኪ ልጠይቃችሁ
እስኪ ተጠየቁ

መስቀልና እስኬማ ካባ ደርባችሁ
በቀን በአደባባይ ነብስ የቀጠፋችሁ
እንደምን ይቀደሳል የምዕመን ደም ተራምዶ
እንዴትስ ይታረቃል መንፈስ በግፍ ላይ ወርዶ
በምድር የፈታችሁት በሰማይ እንዲፈታ
ግብራችሁን ስታችሁ በማስተስረይ ፈንታ
ባረካችሁን በወኔ ተሳለምን በቃታ

ፊደል ቀራጭ ስንዱዬ እኔን ልጅሽ ፊደል ጠፋኝ
ሀ ብለሽ ያስቆጠርሽው ሆ ብሎ ፊትሽ ደፋኝ
በፀአዳ ግምጃሽ ፈንታ ክልሽን ሳየው ከፋኝ
ህዝቤ በገዛ ሀገሩ ቢገፋ ቢያጎብጠው የኑሮ ቀንበር
የፀለየላት ኢትዮጵያ እንዳትፈርስበት ሀገር
ወዝ የራቀው ገፁን በውሀ እየወለወለ
ረሀብ ጥማቱን ችሎ በደጇ የተጠለለ
መስዋዕቱን ሊሰዋ በገናውን የደረደረ
ከጌታው ጋር ተቃጥሮ ተመስገን ሊለው ነበረ
ደረቱን ተቀረደደ በድኑ ተሽቀነጠረ
ይፅናናበት ማልቀሻችን ምናለን ከደብሩ ሌላ
እንፅናናበት ማልቀሻችን ምን አለ ከደብሩ ሌላ
ድርሳን አላቃጠ መንገድ አልዘጋ ኬላ
ጥበብ እየመገበች ኮትኩታው ነበር ከልላ
ለምጣዱ ሲባል ትለፍ ብለናል አይጧ
ሰስተንላት ነገር ፈርተን ይሄ ቀን እንዳይመጣ

ይልቅ ይልቅ ግፍህን ታጠብ በደልህን ተለቃለቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
የተማመንከው ቢደድር አስተምሮትህ ብረቅም
ከሺህ አመታት ዶሴ ከአባቶቻችን አይልቅም
ብንጠፋ ብናጠፋ ከደጀ ሰላሟ ብንርቅም
የተስፋ ርስታችን ናት ደብራችንን አንለቅም
እኔም አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ
ከአንዲት ቤተስኪያን ወድያ
አቻ ክብር አላውቅም ልጄም በካህን እንጂ በአቶ አይጠመቅም ይኸው ነው !!!
2.8K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 10:56:31
የአማራ ፖሊስ ባንድ አባላት
1.1K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 19:31:27
ደብረማርቆስ ባጃጅ ማሕበራት
1.1K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 13:36:36
አዋሽ ባንክ ጥቁር የለበሱ ሰራተኞችን አባርራለሁ ማለቱን ትናንተ መዘገባችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ በርካታ የገፃችን ተከታዮች መረጃው ስህተት መሆኑን በውስጥ መስመር መልዕክት እያስቀመጡ ነው፡፡
2.3K viewsedited  10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 12:44:22
የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መርቃዮስ ለአቶ ሙስጠፌ በይፋ ምስጋናቸውን አቀረቡ!

ብጹዕ አቡነ መርቃዮስ የምስራቅ ሃህርጌና የሶማሌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለእውነት የቆሙ የተዋህዶ ጠባቂ ናቸው ሲሉ በይፋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሊቀጳጳሱ ምስጋናቸውን የሰጡት በሶማሌ ክልል ትላንት ከማለዳው አንስቶ ጥቁር ለብሳችሁ ወደ ቤተክርስቲያን አትገቡም የተባሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናንን የጸጥታ አካል ነን በሚል ከፌደራል ፖሊስን ያቀፈ ሃይል እስከ እስር የደረሰ እንግልት ከማለዳው አንስቶ ማድረጉን ተከትሎ ቀትር ላይ አፋጣኝ ውይይት ከቤተክርስትያን ሃላፊዎች ጋር በማድረግ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡና አስፈላጊውም ጥበቃ እንደረግላቸው ማድረጋቸው ተከትሎ መሆኑን ሊቀጳጳሱን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቴሌቭዥን ዘግቧል።
2.4K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ