Get Mystery Box with random crypto!

ኑ ለቅሶ እንድረስ በገጣሚ ምስራቅ ተፈራ ያሳደግችኝ ደብር ተቀመጠች | Dejen Times

ኑ ለቅሶ እንድረስ
በገጣሚ ምስራቅ ተፈራ

ያሳደግችኝ ደብር ተቀመጠች አሉኝ ለቅሶ
ውለታዋ ተዘንግቶ ክብር ማዕረጓ ተድሶ
በትዕቢት ተረማመደ ቅጥር ግቢዋን ጥሶ
ማር ይዘንባል ማር (×3) ነበር ዜማ ቅኝቷ
ስጋጃው በደም ራሰ ጥይት ዘነበ ከቤቷ

ሰንደቅ አላማ ነበር የዘለ ዕለት ውበቷ
ኑ እንድረሳት ለቅሶ ማቅ ለብሷል ጉልላቷ
እንዳትካስ ለብድሯ ወርቀዘቦ ተንቆጥቁጣ
በምን ቃል ይገለፃል በምን ቃል ይገለፃል
በውን ቆሞ እንደማየት ባዳፋ ጫማ ተረግጣ

ቅጥሯን ለተዳፈረ ለናቃት ይስጠው መጥኔ
የአለምን ሀይል ተመክቶ የታበየ ለኩነኔ
አለም በቃኝ ብለው ምለው ያፀኗት በምናኔ
ኑ እንላቀስ ምዕመን ያልሰማ ይስማ መርዶ
ደብራችን አንብታለች መጋረጃዋ ተቀዶ
ደብረ ሀይል ቅዱስ ራጉኤል የልጅነቴ
በመልዐክ ሀይል ምልጃ የፀናችልኝ ህይወቴ
የአባ መሸ ኪላራይሶ የገብረ ኪዳን ሰንበቴ
የአዝኖና መጠጊያ የነብስ ስጋ ቋቴ
የሀይማኖት መሰረቴ
አፍ መፍቻ ትምህርት ቤቴ
እስኪ ተጠየቁ እስኪ ልጠይቃችሁ
እስኪ ተጠየቁ

መስቀልና እስኬማ ካባ ደርባችሁ
በቀን በአደባባይ ነብስ የቀጠፋችሁ
እንደምን ይቀደሳል የምዕመን ደም ተራምዶ
እንዴትስ ይታረቃል መንፈስ በግፍ ላይ ወርዶ
በምድር የፈታችሁት በሰማይ እንዲፈታ
ግብራችሁን ስታችሁ በማስተስረይ ፈንታ
ባረካችሁን በወኔ ተሳለምን በቃታ

ፊደል ቀራጭ ስንዱዬ እኔን ልጅሽ ፊደል ጠፋኝ
ሀ ብለሽ ያስቆጠርሽው ሆ ብሎ ፊትሽ ደፋኝ
በፀአዳ ግምጃሽ ፈንታ ክልሽን ሳየው ከፋኝ
ህዝቤ በገዛ ሀገሩ ቢገፋ ቢያጎብጠው የኑሮ ቀንበር
የፀለየላት ኢትዮጵያ እንዳትፈርስበት ሀገር
ወዝ የራቀው ገፁን በውሀ እየወለወለ
ረሀብ ጥማቱን ችሎ በደጇ የተጠለለ
መስዋዕቱን ሊሰዋ በገናውን የደረደረ
ከጌታው ጋር ተቃጥሮ ተመስገን ሊለው ነበረ
ደረቱን ተቀረደደ በድኑ ተሽቀነጠረ
ይፅናናበት ማልቀሻችን ምናለን ከደብሩ ሌላ
እንፅናናበት ማልቀሻችን ምን አለ ከደብሩ ሌላ
ድርሳን አላቃጠ መንገድ አልዘጋ ኬላ
ጥበብ እየመገበች ኮትኩታው ነበር ከልላ
ለምጣዱ ሲባል ትለፍ ብለናል አይጧ
ሰስተንላት ነገር ፈርተን ይሄ ቀን እንዳይመጣ

ይልቅ ይልቅ ግፍህን ታጠብ በደልህን ተለቃለቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
የተማመንከው ቢደድር አስተምሮትህ ብረቅም
ከሺህ አመታት ዶሴ ከአባቶቻችን አይልቅም
ብንጠፋ ብናጠፋ ከደጀ ሰላሟ ብንርቅም
የተስፋ ርስታችን ናት ደብራችንን አንለቅም
እኔም አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ
ከአንዲት ቤተስኪያን ወድያ
አቻ ክብር አላውቅም ልጄም በካህን እንጂ በአቶ አይጠመቅም ይኸው ነው !!!