Get Mystery Box with random crypto!

Addis Merkato

የቴሌግራም ቻናል አርማ corona_virus_updates — Addis Merkato A
የቴሌግራም ቻናል አርማ corona_virus_updates — Addis Merkato
የሰርጥ አድራሻ: @corona_virus_updates
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

Our Online Store in Addis Ababa Offers a Great Variety of Products. If You're Looking for Quality Grocery, Apparel and Other Products, You Should Visit Us!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2021-01-25 18:58:36 መቐለን ጨምሮ በትግራይ ክልል የብር ኖት ቅያሬን ከጀመሩ 14 ቀናት ባለፋቸው የክልሉ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው ቅያሬ እንዲቋረጥ ተወሰነ

ብሔራዊ ባንክ ለአሐዱ ቴሌቪዥን በላከው መግለጫ በክልሉ በነበረው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ተቋርጦ የነበረው የብር ኖት ቅያሬ ከታኅሣሥ 21 ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲከወን ከዚህ ቀደም መወሰኑን አስታውሷል፡፡
ሆኖም በአተገባበሩ ላይ ብዥታ ተፈሯል ያለው ብሔራዊ ባንኩ 14 ቀኑ የሚሰላው በአንድ ከተማ ላይ አንድ ባንክ ቀድሞ ሥራ ከሚጀምርበት ቀን አንስቶ ነው ብሏል፡፡

ለምሳሌ በክልሉ አንድ ከተማ ላይ ቀድሞ ሥራ የጀመረው ባንክ ጥር 17 ከሆነ 14 ቀናቱ መሰላት የሚጀምሩት ከጥር 17 ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህም ዘግይተው ሥራ በሚጀምሩት የባንክ ቅርንጫፎች ላይ ተጨማሪ ቀን መስጠት ሳያስፈልግ ቅድሚያ በጀመረው ቅርንጫፍ የጊዜ ገደብ ብቻ እንዲያጠናቅቁ ይገደዳሉ ማለት ነው፡፡
1.7K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-25 18:12:44
የሞደርና ክትባት አዲስ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ እንደሚከላከል ተመራማሪዎች አረጋገጡ

የሞደርና ክትባት በብሪታንያና በደቡብ አፍሪካ የተከሰተውን አዲሱን የኮሮና ቫይረስ እንደሚከላከል የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ተመራማሪዎች አረጋገጡ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራዎች እንዳሳዩት ከሆነ ክትባቱ አዲሱ ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ የሰውነት የመከላከል አቅምን ማዳበር መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡ ተመራማሪዎቹ በዚህ ጥናት የሞደርናን ክትባት የወሰዱ የስምንት ሰዎችን የደም ናሙና መውሰዳቸውን ነው የተናገሩ።
1.5K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-25 18:12:09 ቼልሲ ፍራንክ ላምፓርድን አሰናበተ፡፡

ቼልሲ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድን ከ18 ወራት ቆይታ በኃላ አሰናብቷል፡፡

የቀድሞ የክለቡ የመሀል ሜዳ አቀጣጣይ እንደዚሁም ያሁኑ የክለቡ አሰልጣኝ ሆኖ በመስራት ላይ የነበረው ፍራንክ ላምፓርድ ከአሰልጣኝነቱ መነሳቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የ42 አመቱ ፍራንክ ላምፓርድ በሶስት አመት ኮንትራት ነበር በ2019 የቀድሞ የክለቡ አሰልጣኝ የነበሩትን ማውሪዚዮ ሳሪን በመተካት ክለቡን ተቀላቅሎ የነበረው፡፡ ባለፈው ሳምንት በሌስተር ሲቲ የ2 ለዜሮ ሽንፈት ለአሰልጣኙ መባረር ምክንያት እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

ያለፈው አመት ክለቡ ቼልሲ አራተኛ ሆኖ የውድድር አመቱን ቢጨርስም ጥሩ ተስፋ በቡድኑ ውስጥ ማስቀመጥ ችሎ ነበር፡፡ ቼልሲ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ያሸነፈ ሲሆን የአሰልጣኙ መሰናበት በርካታ የስፖርት ሚዲያዎች በፊት ገጻቸው አውጥተውታል።
1.3K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-25 18:11:34 የኢትዮጵያ ወታደሮች በኢትዮ-ሱዳን ድንበር በኩል የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍተው ነበር ተባለ።

ሱዳን ትሪቡን ወታደራዊ ምንጮቼ ያላቸውን ጠቅሶ እሁድ ከኢትዮጵያ ወታደሮች በኩል በድንበር ላይ ቅኝት እያደረገ በነበረ የሱዳን ጦር ላይ ከባድ መሳሪያ መተኮሱን ዘግቧል። ሆኖም የተጎዳ አለመኖሩንም ነግረውኛል ብሏል።የዘገባው ባለቤት ሁለቱም አገራት ወደ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ እየገለፁ ነው ካለ በኋላ፤ ሆኖም ሱዳን በድንበሩ ጉዳይ ከኢትዮጵያ በኩል እየቀረበ ያለን የድርድር ጥያቄ አልተቀበለችም ሲል ጽፏል።ምክንያቱ ደግሞ የካርቱም መንግሥት በቅርቡ የተቆጣጠረውን መሬት የእኔ ሉኣላዊ ግዛት ነው የሚል እምነት ያሳደረ በመሆኑ ነው ብሏል።

የሱዳን መንግሥት ከኅዳር ጀምሮ በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በድንበር አቅራቢያ ማስፈሩንም ሱዳን ትሪቡን አክሏል።ዘገባው ጨምሮም የሱዳን ወታደሮች ድንበር ጥሰው ወደ አትዮጵያ በመግባት በኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ሰብል የተሸፈንን መሬት መያዛቸውን ነው የገለፀው።የአገሪቱ ባለሥልጣናት የቀድሞው የሱዳን መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ሰጥቷቸው እንጂ መሬቱ የሱዳን ነው የሚል እምነት ማሳደራቸውም ይሰማል።አሐዱ ቴሌቪዥን እሁድ ተፈጽሟል ስለተባለው ተኩስና ወቅታዊ የድንበሩ ጉዳይ ለመጠየቅ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ሬድዋን ሁሴን እና ቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ የስልክ ጥሪን ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]
1.3K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ