Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ወታደሮች በኢትዮ-ሱዳን ድንበር በኩል የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍተው ነበር ተባለ። ሱዳ | Addis Merkato

የኢትዮጵያ ወታደሮች በኢትዮ-ሱዳን ድንበር በኩል የከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍተው ነበር ተባለ።

ሱዳን ትሪቡን ወታደራዊ ምንጮቼ ያላቸውን ጠቅሶ እሁድ ከኢትዮጵያ ወታደሮች በኩል በድንበር ላይ ቅኝት እያደረገ በነበረ የሱዳን ጦር ላይ ከባድ መሳሪያ መተኮሱን ዘግቧል። ሆኖም የተጎዳ አለመኖሩንም ነግረውኛል ብሏል።የዘገባው ባለቤት ሁለቱም አገራት ወደ ጦርነት መግባት እንደማይፈልጉ እየገለፁ ነው ካለ በኋላ፤ ሆኖም ሱዳን በድንበሩ ጉዳይ ከኢትዮጵያ በኩል እየቀረበ ያለን የድርድር ጥያቄ አልተቀበለችም ሲል ጽፏል።ምክንያቱ ደግሞ የካርቱም መንግሥት በቅርቡ የተቆጣጠረውን መሬት የእኔ ሉኣላዊ ግዛት ነው የሚል እምነት ያሳደረ በመሆኑ ነው ብሏል።

የሱዳን መንግሥት ከኅዳር ጀምሮ በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን በድንበር አቅራቢያ ማስፈሩንም ሱዳን ትሪቡን አክሏል።ዘገባው ጨምሮም የሱዳን ወታደሮች ድንበር ጥሰው ወደ አትዮጵያ በመግባት በኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ሰብል የተሸፈንን መሬት መያዛቸውን ነው የገለፀው።የአገሪቱ ባለሥልጣናት የቀድሞው የሱዳን መንግሥት ለኢትዮጵያዊያን አርሶ አደሮች ሰጥቷቸው እንጂ መሬቱ የሱዳን ነው የሚል እምነት ማሳደራቸውም ይሰማል።አሐዱ ቴሌቪዥን እሁድ ተፈጽሟል ስለተባለው ተኩስና ወቅታዊ የድንበሩ ጉዳይ ለመጠየቅ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ሬድዋን ሁሴን እና ቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ የስልክ ጥሪን ቢያደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል።

[አሐዱ ቴሌቪዥን]