መቐለን ጨምሮ በትግራይ ክልል የብር ኖት ቅያሬን ከጀመሩ 14 ቀናት ባለፋቸው የክልሉ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው ቅያሬ እንዲቋረጥ ተወሰነ ብሔራዊ ባንክ ለአሐዱ ቴሌቪዥን በላከው መግለጫ በክልሉ በነበረው ሕግ የማስከበር ዘመቻ ተቋርጦ የነበረው የብር ኖት ቅያሬ ከታኅሣሥ 21 ጀምሮ ለ14 ቀናት እንዲከወን ከዚህ ቀደም መወሰኑን አስታውሷል፡፡ ሆኖም በአተገባበሩ ላይ ብዥታ ተፈሯል ያለው ብሔራዊ ባንኩ 14 ቀኑ የሚሰላው በአንድ ከተማ ላይ አንድ ባንክ ቀድሞ ሥራ ከሚጀምርበት ቀን አንስቶ ነው ብሏል፡፡ ለምሳሌ በክልሉ አንድ ከተማ ላይ ቀድሞ ሥራ የጀመረው ባንክ ጥር 17 ከሆነ 14 ቀናቱ መሰላት የሚጀምሩት ከጥር 17 ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህም ዘግይተው ሥራ በሚጀምሩት የባንክ ቅርንጫፎች ላይ ተጨማሪ ቀን መስጠት ሳያስፈልግ ቅድሚያ በጀመረው ቅርንጫፍ የጊዜ ገደብ ብቻ እንዲያጠናቅቁ ይገደዳሉ ማለት ነው፡፡ 1.7K views15:58