Get Mystery Box with random crypto!

ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ሀሰተኛ ደረሰኝ ተገኘ! የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባደረገ | Addis Merkato

ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ሀሰተኛ ደረሰኝ ተገኘ!

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ባደረገው የኦዲት ምርመራ ግምታቸው ከ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ ሀሰተኛ ደረሰኞች ማግኘቱን ለአዲስ ዘይቤ ገልጿል፡፡“የተጭበረበሩ ደረሰኞችን በማዘጋጀት፣የታክስ እዳውን ለመቀነስ ወይም ተመላሽ ለመጠየቅ ሆን ተብሎ እንደተደረገ በኦዲት ስራ ተጋልጧል።

እንዲህ አይነት ህገወጥ ተግባር ደግሞ የ100 ሺህ ብር የገንዘብ እና ከሰባት እስከ አስር አመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት እንደሚያደርሰ ህጉ ላይ በግልፅ ተቀምጧል።” በማለት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተናግሯል።በመጨረሻም አሁን ላይ መስሪያቤቱ የህግ ማስከበር ስራን በስፋት አጠንክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቅሶ የኦዲት ስራን የሚሰሩ ባለሞያዎች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብሏል፡፡