Get Mystery Box with random crypto!

ጠ/ሚ ዐብይ በይፋ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት መቼ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሳምንታት በይ | Addis Merkato

ጠ/ሚ ዐብይ በይፋ ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት መቼ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሳምንታት በይፋ አለመታየታቸው በበርካቶች ዘንድ አነጋጋሪነቱን እየጨመረ የመጣ ክስተት ሆኖ ቀጥሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የታዩት መቼ ነው የሚለው በራሱ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎችን እያነጋገሩ ካሉ ጉዳዮች አንዱ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የታዩት እና ንግግር ያደረጉት ወይም ደግሞ ንግግር ሲያደርጉ የታዩት ማክሰኞ ታሕሳስ 13፣ 2013 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከነዋሪዎች ጋር በተወያዩበት ጊዜ ነበር።

በተመሳሳይ ቀን በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የተካሄደውን የሚኒስትሮች ስብሰባ መምራታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና በትዊትር ገጽ ላይ ሰፍሮ ይታያል።

ነገር ግን ጥር 4 2013 ዓ.ም የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ደቡብ ክለል ተጉዘው የኮይሻን ፕሮጀክት ጎብኝተዋል የሚል በምስል የተደገፈ ዜና አቅርበዋል።

በዚህ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩ በአደባባይ አለመታየት መነጋገሪያ መሆኑን ጨምሮ ስለነበር፣ መንግሥትን የሚደግፉ አክቲቪስቶች ይህንን እንደማስረጃ በመጥቀስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቢሯቸው ስራ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ጽፈዋል።

ይኹን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተንቀሳቃሽ ምስል በመገናኛ ብዙኀን ላይ ቀርበው የታዩት በመተከል ዞን ከነዋሪዎች ጋር ሲወያዩ ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ማለትም፤ በትዊትር እና ፌስቡክ፣ በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።