Get Mystery Box with random crypto!

አስተምህሮተ 🔱ክርስትና

የቴሌግራም ቻናል አርማ christiandoctrine — አስተምህሮተ 🔱ክርስትና
የቴሌግራም ቻናል አርማ christiandoctrine — አስተምህሮተ 🔱ክርስትና
የሰርጥ አድራሻ: @christiandoctrine
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.11K
የሰርጥ መግለጫ

በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ መሰረት= የቅዱሳት መጽሀፍት "ትምህርት "ነው ።
👌አላማችን
✔ ክርስቶስን የሚመስል፣ቅዱሳት መጸሀፍትን እና እምነቱን የሚያውቅ ክርስቲያን ማፍራት
👌የምንሰጠው አገልግሎት
✔በድምፅ ዶክትሪናል የሆኑ ትምህርቶች
✔በፅሁፍ ዶክትሪናል የሆኑ ትምህርቶች
✔በአማርኛ እንዲሁም በEnglish የተፃፉ መጽሀፍትን መቅረብ እና የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-04 20:45:02 ፩. ውድ በኾነው በልጅህ ደም ዋጅተህ
ከወርቅ ከዕንቁ የሚበልጥ ዋጋ ከፍለህ
ማደርያህ እንዲሆን በቀደስከው ሕዝብህ ላይ
አቤት ስያስፈራ ግርማህ ደምቆ ሲታይ
በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
በወደድከው ሕዝብህ ላይ
ባከበርከው ሕዝብህ ላይ
የእኔ ባልከው ሕዝብህ ላይ

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል

፪. ከምሥራቅ ምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ
ትልቅ ትንሹን ከሩቅ እና ከቅርብ
እርስት አድርገህ ለራስህ መርጠሃል
ለእርሱም ርስቱ አንተው ሆነኸዋል
የዘላለም መኖርያ አምባና መታመኛው
ሞገሱና ውበቱ ብርታቱ ነህ ጉልበቱ

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል

፫. ከዓለም እርኩሰት ከዕድፈት አንጽተኸው
የንጉሥ ካህን እንዲሆን በሾምከው
የክብርህ ጸዳል በላዩ በርቶበት
ድል ነሺ ሆኗል በጠላቶቹ ፊት
ለራስህ የለየኸው
ለርስትህ የቀደስከው
በፍቅርህ የማረከው
በስራህ ያጸደከው

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል

፬. ድቅድቅ ጨለማ ወርሶት በነበረው
በአንተ ቸርነት ምህረትን ባገኘው
በዚህ ምርጥ ሕዝብ ትመሰገናለህ
በምሥጋናውም ሁሌ ትከብራለህ
ልጅ አርገህ ባቀረብከው
በስምህ በጠራኸው
ክብርህን ባካፈልከው
በቀኝህ ባስቀመጥከው

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል
107 viewsበምህረት ተሻገር, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 13:46:10 የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፤
ምሳሌ 9:10

The fear of the LORD is the beginning of wisdom: and the knowledge of the holy is understanding.
Proverbs 9 10
133 viewsበምህረት ተሻገር, 10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:26:02
190 viewsNarrow, 07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 21:40:47 God speaks to us today all the time through the Scriptures. God that speaks apart from the Scripture is not a God.

@Christisallsufficient
169 viewsበምህረት ተሻገር, 18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 12:21:24 .  በብዙ መልኩ፣ የክርስቶስን ክብር አበላሽቷል” (T.H.L. Parker , Portrait of Calvin Paperback, Desiring God, 2009, 113)። በወቅቱ የፓፓው ሥልጣን ከቃሉ በላይ እንደሆነ ተድርጎ ቤተ ክርስቲያን በታወረችበት ወቅት፣ ካልቪን በነፍሱ በመወራረድ፣ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ቃሉ የበላይነት ሥልጣን ሥር መሆኗን አጥብቆ ሞግቷል፦

“የቅዱሳት መጻሕፍት ሥልጣን ምንጭ የእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ ሰው አይደለም . . .  ሰው ሁሉ (ፓፓውንና ካህናቱን ጨምሮ) ለእግዚአብሔር ቃል ሥልጣን ተገዢ ናቸው . . . ቅዱሱ ቃሉ በሰው ሥልጣ ሥር አይደለም፤ ይልቁንም የቤተ ክርስቲያን ሕልውና መሠረቱ ቃሉ ነው፤ ። (Institutes, 1.7.2)።

ይህም ጽኑ አቋም፣ 25 ዓመት በአገልግሎት የሚቀደመው የሉተርም ነበር። ሉተር ቅዱስ አውጐስጢኖስን በመጠቀስ፣ "ቅዱሳት መጻሕፍት፣ ሕጸጽም ሆነ ግድፈት የሌለባቸው የእግዚአብሔር እስትንፋሳዊ ቃል መሆናቸውን አጥብቄ በማመን ይዤአለሁ" ሲል መስክሯል፤ ዋጋም ከፍሏል። (What Luther Says: An Anthology, ed. Ewald M. Plass [St. Louis: Concordia, 1959], 1:87)

የካልቪን 28 ዓመታት የአገልግሎት ሕይወት ቀላል አልነበረም። በብዙ መከራ የታሸ ነበር። መዝሙር 124፣ በተለይም፣ "ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው" የሚለው የልቡ ጥቅስ ነበረ። ባለቤቱ ኢደሌት (Idelette)፣ ባሏን በወረርሽኝ ሳቢያ ያጣች የሁለት ልጆች ባልቴት ነበረች። ከካልቪን ጋር ወደ አስር ዓመታት ያህል አብረው የኖሩ ሲሆን፣ በዙ መከራም አሳልፈዋል። የመጀመሪያ ልጃቸው የሁለት ሳምንት ሕፃን ሳለ ሞቶባቸዋል። ስለ ልብ ስብራቱም እንዲህ በሎ ጽፏል፦

“ጌታ በሐዘን ጅራፍ ልቤን ያቈሰለው አስኪመስለኝ ድረስ የልጄ ሞት አጥንቴ ውስጥ ዘልቈ ገብቷል። ይሁን እንጂ እርሱ ራሱ ሰማያዊ አባት ስለሆነ ልጅ ማጣት ምን ማለት እንደሆነ ይገባዋል፤ የእርሱም ፈቃድ ፍጹም፣ ለልጃችንም የተሻለውን ያውቃል በማለት በፍጹም ሉዓላዊነቱ ተጽናናሁ።” (T. H. L. Parker, Portrait of Calvin,  [SCM Press; 1st Edition, January 1, 1954, reprinted by Desiring God, 2009], 79)።

በተከታታይ የወለዷቸው ሁለት ልጆች በጨቅላ ዕድሜያቸው፣ በመጨረሻም ኢደሌት ራሷ በወረርሽኝ ወይንም በሳንባ ነቀርሳ ምክንያት ሞታበታለች። ባለቤቱን በማጣቱ ስላለፈበትና ከድባቴ ጋር ስላታገለው የልብ ሐዝን እንዲሁ ብሏል፦

“መሞቷ [በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ፈቃድ] የተወሰነ ቢሆንም፣ ድኽነትን ብቻ ሳይሆን ሞቴን ለመጋራት ፈቃደኛ የሆነችውን የሕይወት አጋሬን በማጣቴ ጥልቅ ሐዘን ክፉኛ አስቆዝሞኛል።” (Parker, Portrait of Calvin, 80)

በዚህ ሁሉ የልብ ስብራት ውስጥ፣ ልቡን በእግዚአብሔር አምላኩ ያበረታ የተሐድሶ መሪ ነበር፤ ትጉህና መስቀል-ተኮር። በሁለት ሳምንት ውስጥ 10 ጊዜ (እሁድ ቀን ብቻ ሁለት ጊዜ) እንዲሁም በሳምንት ሦስት ቀን ነገረ-መለኮት ያስተምር ነበር። ከዮሐንስ ራእይ በስተቀር በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት፤ በአምስቱም ኦሪቶች፣ በመጽሐፈ ኢያሱ፣ በመዝሙረ ዳዊትና በኢሳይያስ ላይ ማብራሪያ ጽፏል።

ይህን ሁሉ ይባትል የነበረው፣ በጄኔቭ የቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን መጋቢነቱ በተጨማሪ ነበር። በየቤቱ የታመሙትን፣ የተቸገሩትን፣ የተጨነቁትን፣ ወላጅ አልባዎችንና ችግረኛ ባልቴቶችን በታማኝነት ይጐበኝ ነበር። በቂ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፤ በኩላሊት፣ በጨጓራ ቁስል፣ በሆድ ድርቀትና ተመሳሳይ ጤና መታወክና እንቅልፍ በማጣት ይሰቃይ ነበር። ይኽን ሁሉ መከራ በትዕግሥት ይቀበል የነበረው፣ በተገኘበት ማንም ሰው እንዲገድለው ቀዳማዊ ፍራንሲስ ያወጀበትን የሞት ዐዋጀ እያወቀ ነበር።

እንደ ጳውሎስ “በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር። በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤” (2ቆር 1፡ 8-9) ያለባቸው ብዙ ሞትን የተመኘባቸው የጨለማ ወቅቶች አሳልፏል። ይሁን እንጂ፣  ብድራቱን ትኩር አድርጐ ዘላለምን በማሰብና በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ላይ በመደገፍ በታማኘነት የክርስቶስን ወንጌል አገልግሏል።  - “የራሴ ጌታ እንዳልሆንሁ አውቃለሁ፤ ልቤን እውነተኛ መስዋዕት በማድረግ ለጌታዬ አሳልፌ ሰጥቻለሁ . . . ፈቃዴንና መከራዎቼን በሙሉ ለእግዚአብሔር አስገዝቼአለሁ።” በማለት!  (Portrait of Calvin, 74-75)። ሲሞትም፣ መቃብሩ ስም የለሽ እንዲሆን በትሕትና ተማጥኗል - ክርስቶስ በእርሱ ካደረገው ሥራ በስተቀር ስሙ እንዲዘከር አልፈለገምና።

“ጌታ ሆይ፤ በእውነት ለወንጌልህ እንድንኖርና ታማኝ ባለዐደራዎች እንድንሆን ጸጋህን አብዛልን።” አሜን!

ግርማ በቀለ (ዶ/ር)

ከ ነገረ ወንጌላውያን
https://t.me/negere_evangelical
503 viewsበምህረት ተሻገር, edited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 12:19:16 “በባዝል (ስዊዘርላንድ) በተደበቅሁበት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ፣ እንደ እኔ ከስደት የማምለጥ ዕድል ያላገኙ የወንጌል አማኝ ወዳጆቼ፣ በሕይወት እያሉ በማገዶ እሳት ጋይተው ስለ ክርስቶስና ስለበራላቸው እውነት ሰማዕት ሆነዋል። ታዲያ ይኽን እያወቅሁ ዝም ብል ከዳተኛ፤ ሰማዕትነታቸውንም አቅላይ ያደርገኛል። የሞቱለትን ጌታና የወንጌሉን መልእክት በፍጹም ንጽሕና ለትውልድ ማትረፍ ትንሹ ዕዳዬ ነው።” ( John Dillenberger, Ed., John Calvin: Selections from His Writings, The American Academy of Religion, 1975), 35-36.

ይህን ያለን ወንድማችን የፈረንሳዪ ጆን ካልቪን (10 July 1509 – 27 May 1564) ነው። የ24 ዓመት ወጣት በነበረበት ወቅት የፈርንሳይ ንጉሥ፣ ቀዳማዊ ፍራንሲስ፣ በወንጌል አማኞች ላይ ያስነሣው ስደት ትውልድ አገሩን ጥሎ ወደ ጄኔቭ እንዲሰደድ አድርጎታል። ቀሪው ዘመኑንም የጨረሰው እዚያው ጄኔቭ የቤተ ክርስቲያን ታማኝ መጋቢ በመሆን ነበር። አራት መድብሎች ያሉት የካልቪን ኢንስቲቲዩት “Institutes of the Christian Religion” ያለፉት አምስት መቶ ዐመታት የቤተ ክርስቲያን ሐብትና የነገረ መልኮት አስተምህሮ ቅርስ ናቸው። (http://www.reformed.org/master/index.html?mainframe=/books/institutes/) 

ካልቪን፣ በዓለምና በቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካላቸው ታላላቅ መሪዎች መካከል፣ ከቀዳማይ ተጠቃሾች መካከል ነው። የሕግ፣ ነገረ-መለኮት፣ ፍልስፍና፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ በተለይም ጥንታዊ ግሪክ-ሮማ ሥልጣኔና ቋንቋዎች ጥናት ሊቅ ነበር። በታሪክ ውስጥ፣ በነገረ አስተምህሮ፣ በተለይም በድነት ዙሪያ፣ በቤተ ክርስቲያን ማንነትና ተልእኮ፣ በትምህርት፣ በዲሞክራሲ፣ በመንግሥትና ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መርሕ ዙሪያ መሠረታዊ የሆነ አስተዋጽኦ አድርጓል።  

የዚህ ሁሉ ምንጩ፣ ለሰማው ወንጌል የነበረው ቀናዒነትና ታማኝነት ነበር። ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሔር ግርማዊ ክብር ነጸብራቅ እንዲሆን ነው። እግዚአብሔርን ማምለክና ለክብሩ መኖር፣ የሰው ሕይወት ዓላማና ግብ ነው። የሰው ልጅ ዋነኛ ችግር በኀጢአት ምክንያ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት መሰበር ነው። በተሰነጣጠቀ መስታወት ውስጥ የሚታይ ምስል ጥፉ (disfigured) እንደሚሆን ሁሉ፣ አምሳለ እግዚአብሔር (Imago Dei) የሆነው ሰውም ጥፉ ሆኗል። ኀጢአት የእግዚአብሔርን ክብር ከሰው ላይ ገፏል። ኀጢአት ሰውን ከእግዚአብሔር፣ ሰውን ከራሱ ጋር፣ ሰውን ከሰው ጋር፣ ሰውን ከፍጥረት ጋር አጋጭቶ ለያይቷል፤ በእርሱ ፍርድ ሥር አስቀምጦታል (ሮሜ 6፥11፡ 23፤ ኤፌ 2፥1)። ከውደቀት በኋላ፣ እግዚአብሔር አዳምን “የት ነህ?” ብሎ ሲጠይቀው የቦታ ወይም የአድራሻ ጥያቄ አልነበረም። ይልቁንም፣ በኀጢአት ምክንያት በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ክብር ማጣትና ራሱን ያገኘበትን የውርደት ቦታ እንዲያስብ ነው። ስለዚህ ኀጢአት አነስተኛ የሞራል ቀውስ አይደለም፤ ሥር-ነቀል የሆነ የውስጥ ማንነት ብልሽት ነው። ሆኖም፣ ካልቪን እንዳሰቀመጠው፣ በክርስቶስ ብቸኛ የመስቀል ላይ ቤዝዎት ሥራ ድነት ሆኗል፤ የእግዚአብሔር ክብር ተመልሷል። ወንጌል የዚህ የምሥራች ዐዋጅ ነው።

በልቡ ስለበራለት የወንጌል ብርሃን ሲመሰክር እንዲህ ብሎ ጸፏል፦

“እግዚአብሔር ልቤን በድንገት ለወጠው፤ ለእውነተኛውም የወንጌል ቃል አንበርከከው። በየዕለቱ እየጨመረ በሚሄድና የእግዚአብሔርን ቅድስና በሚጠማ መንፈሳዊ የውስጥ ግለት ነፍሴ ታሠረች።” (John Calvin: Selections from His Writings, 35)።

ስለዚህ ወንጌል፦

“የንግግር ችሎታ፣ ወይም ከአፍ የማያልፍ ሕይወት የለሽ ደረቅ ታሪካዊ ዶክትሪን ሳይሆን ሥር-ነቀል የሆነ የሕይወት መልእክት ነው። በአእምሮ የግል ጥረት፣ በረቀቀ አመንክዮና ሙት በሆነ ሃይማኖታዊ ግልብ የፊደል ሽምደዳ ሊረዱት አይችሉም። የወንጌልን ጉልበት መረዳት የሚቻለው፣ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ነፍስንና የውስጥ ልብን ሰርስሮ ሲገባ ብቻ ነው።" በማለት የወንጌልን ከሰው፣ በሰው ያልሆነ ፈጹም መለኮታዊነት በሕይወት ምስክርነትና በአስተምህሮ ብቃት ሞግቷል። (Calvin, Golden Booklet of a True Christian Life, 20-21)። ይህም መረዳት ሐዋርያው ጳውሎስን ግንዛቤ ያንጸባርቃል። ለገላትያ አማኞች እንዳስታወቀው “ወንጌል ሰው ሠራሽ” አይደለም (ገላትያ 1:11)፤ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ የክርስቶስ ነው። “ከሙታን የተነሣውን፣ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤ የእኔም ወንጌል ይኸው ነው፤”(2 ጢሞቴዎስ 2:8)።

ወንጌልን እንዴት እንደሰማን፣ እንዴት እደተረዳንና እንዴት እንደምንኖር፣ ለትውልዱ ያለንን ተምሳሌነት ይወስናል። የመልእክታችንም ተአማኒነትና ቅቡልነት መሠረት ያረፈው በዚህ እውነት ላይ ነው። ምንም እንኳን በጽኑ መከራና በስደት መካከል ቢሆኑም፣ የተሰሎንቄ ቅዱሳን ይህንን ወንጌል “በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ተቀብለዋል”። ለውጣቸውም ሥር ነቀል በሆነ መልኩ የሚታይ ነበር። በጳውሎስ ሕይወት ውስጥ ክርስቶስን አይተዋል። እነርሱም ጳውሎስንና የጳውሎስን ክርስቶስ መስለዋል። “እናንተ  እኛንና ጌታን መስላችኋል” (1:6። ) በብርቱ መገፋትና መገለል ውስጥ “ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ኅይል ደስታ ተቀብለዋል።” (1:7) በሕይወታቸው ለውጥ፣ ባለመኑትም ዘንድ ሆነ በቅርብና በሩቅ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ምሳሌ ሆነዋል። “ከዚህም የተነሣ በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ ምእመናን መልካም ምሳሌ ሆናችኋል” (1:7)። በዚህ ትውልድ መካከል፣ የእኛስ ሕይወት ምን ይመስክራል?

ልክ በዚሁ መልኩ፣ የመጋቢ ካልቪን ሕይወት እና የሚያገለግላቸው ምእመናን ሕይወት ለውጥ ትወልድ ተሻጋሪ ሆኖ እስከአሁን ለእኛም በረከትና ምሳሌ ሆነዋል። ካልቪን ለክርስቶስ ወንጌል መኖርንና ማገልገለን የየዕለት የሕይወት ግቡ ባደረገ መሰጠት ነበር የኖረው። ይህንንም “ትንሹ የፍቅር ዕዳዬ” ይለዋል። እኛስ፣ ምን ሠርተን ይሆን የምናልፈው?

የካልቪን ጥማት የእግዚአብሔር ክብር ነበር። ይኸው በግል ሕይወቱ ሞልቶ የፈሰሰው የእግዚአብሔር ክብር ነበር፣ የቤተ ክርስቲያንና የዓለምን ዐቅጣጫ ያሰቀየረው። እንደጻፈው፣ “[ክርስቶስን በመምስል] ለማደግ ብርቱ በሆነ የውስጥ መሻት ውስጤ ነደደ” ( . . . inflamed with [an] intense desire to make progress” (John Calvin: Selections from His Writings, 35)። በአደባባይና በግል ሕይወቱ መካካል ምንም የግብዝነት ክፍተት አልነበረም። እሁድ ማለዳ በምስባኩ ላይ የሚታየው ያው ካልቪንን፣ በዚያው የወንጌል መልእክት ግለት በባዝል መንገዶችም ላይ ይታይ ነበር። 

የካልቪን የውስጥ ጩኸት በሙት ሃይማኖትኝነት፣ ከቃሉ ጋር በሚጋጭ ትውፊትና ገደብ በሌለው ፍጹማዊ የፓፓው የሥልጣን ቀውስ የተሰወረውን የክርስቶስን ልቀትና ክብር  ለትውልዱ መገለጥ ነበር። የክርስቶስ የማይቀነስበት፣ የማይጨመርበት፤ እንዲሁም አቻ የሌለው፣ ብቸኛና ብቁ የሆነ የድነት ሙሉ ሥራ የካልቪን መካከለኛ አስተምህሮ ነበር። ለካልቪን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ሊሸፍነው የማይገባ የእግዚአብሔር መካከለኛ ግርማ ነው። ለካልቪን የሮም  (የካቶሊክ እምብርት)፣ “. .
376 viewsበምህረት ተሻገር, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 22:24:00 ኢየሱስ ሰዎችን አትከተሉኝ ብሎ ያውቃል!?
የቱጋ?

ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፱: ፶፯- ፷ ላይ ነዋ። ክፍሉ ኢየሱስ ከሶስት ሰዎችጋ ተራ በተራ ያወራበት ታሪክን ያስነብበናል!

የመጀመሪያው ሰው " ጌታ ሆይ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ " አለው!

ኢየሱስም " ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይ ወፎችም መሣፈሪያ አላቸው ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" ብሎ መለሰለት። በሌላ አነጋገር ፥ ኢየሱስ ሰውየውን "እኔን ልትከተለኝ ካሰብክ ቤት አልባ ልትኾን እንደምትችል አስበኽ ተከተለኝ" እያለው ነው!እንደዛ ከኾነ ተከታዮቹ መጠለያ የማግኘት መሠረታዊ ፍላጎታቸው ላይረጋገጥ ይችላል ማለት ነው። "Followers of Christ are not guareented that even their basic need of shelter will be met."

ኹለተኛውን ደሞ ተከተለኝ ሲለው " ጌታ ሆይ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ " አለው፤ ኢየሱስም " ሙታን ሙታናቸውን ይቅበሩ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግስት ስበክ አለው።"

ይኼ ደ'ሞ በፍፁም ያልተጠበቀ መልስ ነው፤ "አባቴ ሞተብኝ " ያለውን ሰው አብሮት ሊያስተዛዝነውና ወደ ቀብር ቦታ ሊሄድ ሲገባው "ሙታኖችን ሙታን ይቅበሯቸው" የሚል ኩም የሚያደርግ ንግግር ተናገረው ። የሚወደው አባቱ የሞተበትን ሰው "ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው" መባል በራሱ አስደንጋጭ እኮ ነው!

ሦስተኛውም "ጌታ ሆይ እከተልሃለሁ አስቀድሜ ከቤተሰቦቼ እንድሰናበት ፍቀድልኝ" አለው። ኢየሱስም "ማንም እርፍ ይዞ ወደኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግስት የተገባ አይደለም " ብሎ መለሰለት።

አኹንም ተመሳሳይ የኾነ ሰብዓዊ ጥያቄ ያስነሳል!ቤተሰቦቹን እንዳይሰናበት?? አብረውት ረጅም ዘመን የኖሩትን የቅርቦቹን?? ከማንም በላይ አብልጠው የሚወዱትንና የሚወዳቸውን??

በጣም ሚያስገርመው ግን

"from all we can tell in Luke 9, Jesus was successful in persuading these men not to follow him?" ነገርየው ፡ ክፍሉ ኢየሱስ ሶስቱንም ሰዎች እንዳይከቱሉት በማሳመን ተሳክቶለታል የሚል ነው ።

[ይሰቀል ሳልባል ልንገራቹ ]

ይሄን ኹሉ ያለው David Platt ነው፤ "Radical; taking back your faith from the American dream "በሚለው መፅሀፉ ውስጥ።

ነገሩ እንዲያ ከኾነ ታዲያ የኛን "ወንጌል" ማነው የወጋው??

እምነት አየለ
449 viewsበምህረት ተሻገር, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 11:11:40 " እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:6)
670 viewsበምህረት ተሻገር, 08:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 20:47:09 " ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:5)
691 viewsHop Um Geb, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 09:49:06 "እኔ እስክመጣ ድረስ ለማንበብ [ልታነብላቸው]፣ ለመምከርና ለማስተማር ትጋ" (1 ጢሞ 4፡13)

ከወደቅንባቸው ታላላቅ ነገሮች መካከል ብዬ ከማስባቸው አንዱ፣ የቅዱሳት መጻሕፍትን ንባብ «የግል መንፈሳዊ ልምምድ» ብቻ ማድረጋችን ነው። እንደ ክርስቲያናዊ ማኅበረብ፣ የኅብረት ጾም፣ የኅብረት ጸሎትና አምልኮ እናደርጋለን። እንደ ክርስቲያናዊ ማኅበረሰብ ግን በጉባኤ ወይም በቡድን በጋራ ቁጭ ብሎ ረጃጅም የቅዱሳት መጻሕፍትን ንባባት የማንበብ ልማድ ግን አላዳበርንም። ይህ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ያስከተለው አያሌ ጉዳት ያለ ይመስለኛል። ዕዝራ "ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ፣ ዕዝራ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ያነብ" ነበር። ጳውሎስም ለሌሎች ያስነብብ ነበር። ኢየሱስ በሙኹራቦቻቸው መጻሕፍትን ያነብ ነበር። አቡቀለምሲሱ ዮሐንስ ጠቅላላ የራዕዩን መጽሐፍ ለታዳሚው "የሚያነብ ብፁዕ ነው" ይላል፤ "የሚሰሙትም የሚያደርጉትም ብፁዓን" ናቸውም ብሎናል።

እውነት ነው፣ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሞላ ጎደል በግል ማንበብ እድል ስላልነበራቸው (በዋነኝነት የግል ቅጂ መያዝ እጅግ ውድ በመሆኑ፣ አንዳንዱም ማንበብ ስለማይችሉ) በጉባኤ እንዲነበብ መታዘዙ የግድ ነው። ግን ይህ ብቻ ነው ብሎ ለመስውሰድ ያዳግተኛል። ሲጀመር፣ ብዙዎቻችን በግል ዲሲፕሊን ኖሮን ለማንበብ የምንቸገር ስንት ነን? የቃሉስ ንባብ "በግልህ ብቻህን የምትጋፈጠው እንጂ የጉባኤ ልማድ አይደለም" ብሎስ ማን አዘዘን? ይህን ስል በግል ቅዱሳት መጻሕፍት ማንበብና ማሰላሰል «ጣል፡ ጣል እናድርግ» እያልኩ አይደለም። ተቃራኒውን እንጂ። እንደ ሕዝብ አንድን ንባብ አንብበን፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ አንድ ሕዝብ ቢመክረን፣ ቢገስጸን፣ ቢናገረን...አንዳንዴ በሳቅና በእንባ...አንዳንዴም ተንበርክከን ቃሉ እንደ ወንዝ ቢፈስ፣ ምን አለበት ግን? ሁለት ሰዓት ቁጭ ብለን ፊልም እያየን? አራት ሰአት "ቢንዥ ተከታታይ ፊልም" እያየን? ሦስት ሰአት አምልኮ በፉጨት እየዘመረን? ምን አለበት? ግን ደግሞ ወደ እግዚአብሔር «ኧረ ጠፋን መልሰን!» ብለን እንጮኻለን አይደል? መጮኹስ አይቅር። አብዝተን እንጩኽ። ግን ሠይፍ የሆነውንና ኀያል-ቃሉ እየተደመጠ ብንጮህ እንደቃሉ ቃሉ ይሠራል። በምስባኮቻችን «አንድም ቀን ተነበው የማያውቁ የቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት አሉ» ብላችሁ ታምናላችሁ? አታምኑም! ስንት ዓመት ነበር ያገልገልኩት...ስንት አመት ነበር በአንድ አጥቢያ ያመለኩት...የትዬ ለሌ! ነገር ግን በጉባኤ ተነበው ያልተመከርንባቸው፣ የልተገሰጽንባቸውና ያልተጽናናንባቸው አያሌ ምንባባ አሉ ብላችሁስ! አታምኑኝም። ይህ የኔ ብቻ ልምምድ ነውና። እግዚአብሔርም ያድርገው። ይህ የኔ ብቻ ገጠመኝና ቅዠት ሆኖ እኔ በጠፋሁ። እኔ ውሸተኛ በሆንኩ። ግን ከዚህ ቅዠት አልነቃ አልኩ።

የሮሜ ደብዳቤ እኮ፣ በአንድ ቁጭታ ነበር ለጉባኤው የተነበበው። እውነት ነው ምናልባት አገልጋይቱ ፌበን አሊያም የቤተ ክርስቲያኑ መሪዎች ለረጅም ሰዓታት፣ በተከታታይ ሰንበት ለሕዝቡ እየተነተኑ ማብራሪያ እንደሰጡ ጥርጥር የለውም። ግን የ16ቱ ምዕራፍ ንባቡ አላጠረም:: እናም፣ የቃሉ ንባብ ጋር ስንመጣ ረጅም ንባብ አይደብረን። ለምን በስቅለቱ ሰሞን ወንጌላት አይነበቡም? ቢያንስ ኢየሩሳሌም ከገባበት ቀናት ጀምሮ እስከ ስቅለቱ የወንጌል ትራኬ በጉባኤ ቢተረክልን ምናለበት? ቁጭ ብለን። ተንበርክከን። ቆመን። ደግሞ እሁድ የትንሳኤውን ንባባት፣ እያጨበጨብን!

ማን ነው የቃሉ አገልግሎት በ30-40 ደቂቃ ስብከት ብቻ ይወሰን ያለን? ማለቴ፣ እንዴት በሳምንት በ30 ደቂቃ ሕዝብ እንዲለወጥ፣ የአስተሳሰብ ተሓድሶ እንዲመጣ እንጠብቃለን? ምንስ እንደዚያ ይመጣል? ሕዝብ እንዲያ ተለውጦ ያውቃል? አድማሳዊ የሆነ (የፓራዳይም) ለውጥ በቅጽበት መጥቶ ያውቃል? ግን ደግሞ "ጸጋው" ጎደለብን አይደል? ለመቆም ጉልበት አጣን፣ ኀጢአት በላይና በታች አወከን አይደል? የስህተት ትምህርት በግራና በቀኝ አጣፋን አይደል? ላዩም ጆሯችን ጭው እስኪል ድረስ። ልጆቻችን እንግዳ ልምምድ ውስጥ ገቡ አይደል? ግራ ተጋባን! ይህ ሁሉ በጉባኤ ንባብ አይፈታም። መች በቀላል። ግን ወደ መሠረታዊውና ወደ ዋነኛው መመለስ፣ የት እንደወደቅን አውቀን ወደ ሚበጀን መመለስ ጥበብ ይመስለኛል። ደግሞስ "ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ" ሰጣቸው (ሐዋ 20፡32) ሲል፣ ቃሉ ጉልበት እንዳለው ታሳቢ ያደረገ ነው አይደል? እንደ ጉባኤ አንድን ነገር ሰምተን፣ ተመሳሳይ ምላሽ ለቃሉ ስንሰጥ እድገታችንም እንዲሁ ብስለታችንም እንዲሁ እያደገ የሚመጣ ይመስለኛል።

ጳውሎስ በአንድ ከተማ ለጥቂት ሳምንታት ቢበዛ ለጥቂት ወራት ነበር ሰብኮ፣ ቤተ ክርስቲያን ተክሎና መሪዎችን ሾሞ የሚሔደው። ለምሳሌ በተሰሎንቄን የነበረው ቆይታ ቢያንስ ለሦስት ሰንበታት ወይም ቢያልፍ ጥቂት ሳምንታት ነበር (ሐዋ 17፡2-10)። ከኤፌሶንና ከቆሮንቶስ በስተቀር ይህ ልማዱ ነበር። ግን ምን ያህል በየዕለቱ የትየሌለ የሚያህል የብሉይ መጻሕፍትን (ከሰብዓ-ሊቃናቱ? ወይም መሰል የግሪክ ትርጉም?) ቢያነብላቸው ይሆን፣ በመልእክቱ ሁሉ ከልጅነታቸው ጀምሮ ብሉይን እንዳነበቡ ሰዎች የሚጽፈው። የገላትያን መልእክት ተመልከቱ። እነዚህ ሰዎች ብሉይ ንባባትን ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቁ እንጂ ለአፍታ ከጥቂት ጊዜ በፊት አብርሃም የሚባል ሰውና የድነቱን ትራኬ፣ ኢሳያስ የተባለ ትንቢትና የትድግናውን ተስፋ (ከነትንታኔው) የማያውቁ እንደነበሩ የሚጠቁም የለም። በተጨማሪም፣ ለከፍ አድርጎ የሚያልፋቸው፣ ብሉይን ንባባት አስደምመው (allusions) የሚያልፉ ጽሑፎቹ፣ ከአንባቢያኑ ምን ያህል የብሉይ ንባባትን እውቀት እንደሚጠብቅ ያስረዳል። እነዚህ ሰዎች በአጭር ጊዜ በቅዱሳት መጻሕፍት ባህር ውስጥ እንደሚዋኙ ሰዎች ነበር የሞገታቸው። ምን እያልኩ ነው? የቅዱሳት መጻሕፍት ንባባት የመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ልማድ ነበር።

በጉባኤ ማንበብ ግን ብቸኛ አማራጭ አይደለም። ዛሬ ዙም አለ። ስልክ አለ። በአካል የሚገኝ በአካል፣ ካልሆነም በርቀት ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ጉባኤ ማንበብ ይቻላል። የግድ በሰንበት ስብስባችን መሆን የለበትም። ዋናው ቁም እንደ ጉባኤ በአንድነት መነበባቸው ላይ ነው። የዚያን ጊዜ አንድ ነገር ይሆናል። በስብከት እንዲተጋ የእግዚአብሔር ጸጋ የበዛለት "በዚህ ቃል እስኪ አበረታታንና ምከርን" ሕዝብ ይላል። በማስተማር የሚተጋውን "እዚህ ጋር ጥያቄ አለን፦ በዚህ ንባብ ጸሐፊው 'ምን ለማለት ፈልጎነው' ተንትነህ አስረዳን" ጉባኤው ይጠይቃል። የጸሎት ኮረንቲ የሚያቀጣጥለውም፣ "ኧረ በዚህ ቃል ላይ እንጸልይ" ይላል። የቅኔው ሰውም፣ ቃሉን በዜማ ቅኔ አድርጎ ይዘርፈዋል። ተሓድሶ ዝም ብሎ አይመጣም። ለመታደስ ማደስ ያሉብንም ነገሮች አሉ። ከእነዚህ መካከል፣ በዋነኛነት፣ የቃሉ ንባብ ወደ ሕዝበ ክርስቲያኑ መመለሱ ነው።

ጌታ ሆይ ከቃልህን ረሃብ፣ ቃልህን ወደ መራብ አምጣን!

"ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣
ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣
በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።" (ኢሳያስ 66:2)

ሳምሶን ጥላሁን
841 viewsበምህረት ተሻገር, 06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ