Get Mystery Box with random crypto!

ኢየሱስ ሰዎችን አትከተሉኝ ብሎ ያውቃል!? የቱጋ? ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፱: ፶፯- ፷ ላይ ነዋ | አስተምህሮተ 🔱ክርስትና

ኢየሱስ ሰዎችን አትከተሉኝ ብሎ ያውቃል!?
የቱጋ?

ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፱: ፶፯- ፷ ላይ ነዋ። ክፍሉ ኢየሱስ ከሶስት ሰዎችጋ ተራ በተራ ያወራበት ታሪክን ያስነብበናል!

የመጀመሪያው ሰው " ጌታ ሆይ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ " አለው!

ኢየሱስም " ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይ ወፎችም መሣፈሪያ አላቸው ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም" ብሎ መለሰለት። በሌላ አነጋገር ፥ ኢየሱስ ሰውየውን "እኔን ልትከተለኝ ካሰብክ ቤት አልባ ልትኾን እንደምትችል አስበኽ ተከተለኝ" እያለው ነው!እንደዛ ከኾነ ተከታዮቹ መጠለያ የማግኘት መሠረታዊ ፍላጎታቸው ላይረጋገጥ ይችላል ማለት ነው። "Followers of Christ are not guareented that even their basic need of shelter will be met."

ኹለተኛውን ደሞ ተከተለኝ ሲለው " ጌታ ሆይ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ " አለው፤ ኢየሱስም " ሙታን ሙታናቸውን ይቅበሩ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግስት ስበክ አለው።"

ይኼ ደ'ሞ በፍፁም ያልተጠበቀ መልስ ነው፤ "አባቴ ሞተብኝ " ያለውን ሰው አብሮት ሊያስተዛዝነውና ወደ ቀብር ቦታ ሊሄድ ሲገባው "ሙታኖችን ሙታን ይቅበሯቸው" የሚል ኩም የሚያደርግ ንግግር ተናገረው ። የሚወደው አባቱ የሞተበትን ሰው "ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው" መባል በራሱ አስደንጋጭ እኮ ነው!

ሦስተኛውም "ጌታ ሆይ እከተልሃለሁ አስቀድሜ ከቤተሰቦቼ እንድሰናበት ፍቀድልኝ" አለው። ኢየሱስም "ማንም እርፍ ይዞ ወደኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግስት የተገባ አይደለም " ብሎ መለሰለት።

አኹንም ተመሳሳይ የኾነ ሰብዓዊ ጥያቄ ያስነሳል!ቤተሰቦቹን እንዳይሰናበት?? አብረውት ረጅም ዘመን የኖሩትን የቅርቦቹን?? ከማንም በላይ አብልጠው የሚወዱትንና የሚወዳቸውን??

በጣም ሚያስገርመው ግን

"from all we can tell in Luke 9, Jesus was successful in persuading these men not to follow him?" ነገርየው ፡ ክፍሉ ኢየሱስ ሶስቱንም ሰዎች እንዳይከቱሉት በማሳመን ተሳክቶለታል የሚል ነው ።

[ይሰቀል ሳልባል ልንገራቹ ]

ይሄን ኹሉ ያለው David Platt ነው፤ "Radical; taking back your faith from the American dream "በሚለው መፅሀፉ ውስጥ።

ነገሩ እንዲያ ከኾነ ታዲያ የኛን "ወንጌል" ማነው የወጋው??

እምነት አየለ