Get Mystery Box with random crypto!

“በባዝል (ስዊዘርላንድ) በተደበቅሁበት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ፣ እንደ እኔ ከስደት የማምለጥ ዕድ | አስተምህሮተ 🔱ክርስትና

“በባዝል (ስዊዘርላንድ) በተደበቅሁበት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ፣ እንደ እኔ ከስደት የማምለጥ ዕድል ያላገኙ የወንጌል አማኝ ወዳጆቼ፣ በሕይወት እያሉ በማገዶ እሳት ጋይተው ስለ ክርስቶስና ስለበራላቸው እውነት ሰማዕት ሆነዋል። ታዲያ ይኽን እያወቅሁ ዝም ብል ከዳተኛ፤ ሰማዕትነታቸውንም አቅላይ ያደርገኛል። የሞቱለትን ጌታና የወንጌሉን መልእክት በፍጹም ንጽሕና ለትውልድ ማትረፍ ትንሹ ዕዳዬ ነው።” ( John Dillenberger, Ed., John Calvin: Selections from His Writings, The American Academy of Religion, 1975), 35-36.

ይህን ያለን ወንድማችን የፈረንሳዪ ጆን ካልቪን (10 July 1509 – 27 May 1564) ነው። የ24 ዓመት ወጣት በነበረበት ወቅት የፈርንሳይ ንጉሥ፣ ቀዳማዊ ፍራንሲስ፣ በወንጌል አማኞች ላይ ያስነሣው ስደት ትውልድ አገሩን ጥሎ ወደ ጄኔቭ እንዲሰደድ አድርጎታል። ቀሪው ዘመኑንም የጨረሰው እዚያው ጄኔቭ የቤተ ክርስቲያን ታማኝ መጋቢ በመሆን ነበር። አራት መድብሎች ያሉት የካልቪን ኢንስቲቲዩት “Institutes of the Christian Religion” ያለፉት አምስት መቶ ዐመታት የቤተ ክርስቲያን ሐብትና የነገረ መልኮት አስተምህሮ ቅርስ ናቸው። (http://www.reformed.org/master/index.html?mainframe=/books/institutes/) 

ካልቪን፣ በዓለምና በቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካላቸው ታላላቅ መሪዎች መካከል፣ ከቀዳማይ ተጠቃሾች መካከል ነው። የሕግ፣ ነገረ-መለኮት፣ ፍልስፍና፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ በተለይም ጥንታዊ ግሪክ-ሮማ ሥልጣኔና ቋንቋዎች ጥናት ሊቅ ነበር። በታሪክ ውስጥ፣ በነገረ አስተምህሮ፣ በተለይም በድነት ዙሪያ፣ በቤተ ክርስቲያን ማንነትና ተልእኮ፣ በትምህርት፣ በዲሞክራሲ፣ በመንግሥትና ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መርሕ ዙሪያ መሠረታዊ የሆነ አስተዋጽኦ አድርጓል።  

የዚህ ሁሉ ምንጩ፣ ለሰማው ወንጌል የነበረው ቀናዒነትና ታማኝነት ነበር። ሰው የተፈጠረው የእግዚአብሔር ግርማዊ ክብር ነጸብራቅ እንዲሆን ነው። እግዚአብሔርን ማምለክና ለክብሩ መኖር፣ የሰው ሕይወት ዓላማና ግብ ነው። የሰው ልጅ ዋነኛ ችግር በኀጢአት ምክንያ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት መሰበር ነው። በተሰነጣጠቀ መስታወት ውስጥ የሚታይ ምስል ጥፉ (disfigured) እንደሚሆን ሁሉ፣ አምሳለ እግዚአብሔር (Imago Dei) የሆነው ሰውም ጥፉ ሆኗል። ኀጢአት የእግዚአብሔርን ክብር ከሰው ላይ ገፏል። ኀጢአት ሰውን ከእግዚአብሔር፣ ሰውን ከራሱ ጋር፣ ሰውን ከሰው ጋር፣ ሰውን ከፍጥረት ጋር አጋጭቶ ለያይቷል፤ በእርሱ ፍርድ ሥር አስቀምጦታል (ሮሜ 6፥11፡ 23፤ ኤፌ 2፥1)። ከውደቀት በኋላ፣ እግዚአብሔር አዳምን “የት ነህ?” ብሎ ሲጠይቀው የቦታ ወይም የአድራሻ ጥያቄ አልነበረም። ይልቁንም፣ በኀጢአት ምክንያት በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ክብር ማጣትና ራሱን ያገኘበትን የውርደት ቦታ እንዲያስብ ነው። ስለዚህ ኀጢአት አነስተኛ የሞራል ቀውስ አይደለም፤ ሥር-ነቀል የሆነ የውስጥ ማንነት ብልሽት ነው። ሆኖም፣ ካልቪን እንዳሰቀመጠው፣ በክርስቶስ ብቸኛ የመስቀል ላይ ቤዝዎት ሥራ ድነት ሆኗል፤ የእግዚአብሔር ክብር ተመልሷል። ወንጌል የዚህ የምሥራች ዐዋጅ ነው።

በልቡ ስለበራለት የወንጌል ብርሃን ሲመሰክር እንዲህ ብሎ ጸፏል፦

“እግዚአብሔር ልቤን በድንገት ለወጠው፤ ለእውነተኛውም የወንጌል ቃል አንበርከከው። በየዕለቱ እየጨመረ በሚሄድና የእግዚአብሔርን ቅድስና በሚጠማ መንፈሳዊ የውስጥ ግለት ነፍሴ ታሠረች።” (John Calvin: Selections from His Writings, 35)።

ስለዚህ ወንጌል፦

“የንግግር ችሎታ፣ ወይም ከአፍ የማያልፍ ሕይወት የለሽ ደረቅ ታሪካዊ ዶክትሪን ሳይሆን ሥር-ነቀል የሆነ የሕይወት መልእክት ነው። በአእምሮ የግል ጥረት፣ በረቀቀ አመንክዮና ሙት በሆነ ሃይማኖታዊ ግልብ የፊደል ሽምደዳ ሊረዱት አይችሉም። የወንጌልን ጉልበት መረዳት የሚቻለው፣ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ነፍስንና የውስጥ ልብን ሰርስሮ ሲገባ ብቻ ነው።" በማለት የወንጌልን ከሰው፣ በሰው ያልሆነ ፈጹም መለኮታዊነት በሕይወት ምስክርነትና በአስተምህሮ ብቃት ሞግቷል። (Calvin, Golden Booklet of a True Christian Life, 20-21)። ይህም መረዳት ሐዋርያው ጳውሎስን ግንዛቤ ያንጸባርቃል። ለገላትያ አማኞች እንዳስታወቀው “ወንጌል ሰው ሠራሽ” አይደለም (ገላትያ 1:11)፤ ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ የክርስቶስ ነው። “ከሙታን የተነሣውን፣ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤ የእኔም ወንጌል ይኸው ነው፤”(2 ጢሞቴዎስ 2:8)።

ወንጌልን እንዴት እንደሰማን፣ እንዴት እደተረዳንና እንዴት እንደምንኖር፣ ለትውልዱ ያለንን ተምሳሌነት ይወስናል። የመልእክታችንም ተአማኒነትና ቅቡልነት መሠረት ያረፈው በዚህ እውነት ላይ ነው። ምንም እንኳን በጽኑ መከራና በስደት መካከል ቢሆኑም፣ የተሰሎንቄ ቅዱሳን ይህንን ወንጌል “በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ተቀብለዋል”። ለውጣቸውም ሥር ነቀል በሆነ መልኩ የሚታይ ነበር። በጳውሎስ ሕይወት ውስጥ ክርስቶስን አይተዋል። እነርሱም ጳውሎስንና የጳውሎስን ክርስቶስ መስለዋል። “እናንተ  እኛንና ጌታን መስላችኋል” (1:6። ) በብርቱ መገፋትና መገለል ውስጥ “ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ኅይል ደስታ ተቀብለዋል።” (1:7) በሕይወታቸው ለውጥ፣ ባለመኑትም ዘንድ ሆነ በቅርብና በሩቅ ላሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ምሳሌ ሆነዋል። “ከዚህም የተነሣ በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ ምእመናን መልካም ምሳሌ ሆናችኋል” (1:7)። በዚህ ትውልድ መካከል፣ የእኛስ ሕይወት ምን ይመስክራል?

ልክ በዚሁ መልኩ፣ የመጋቢ ካልቪን ሕይወት እና የሚያገለግላቸው ምእመናን ሕይወት ለውጥ ትወልድ ተሻጋሪ ሆኖ እስከአሁን ለእኛም በረከትና ምሳሌ ሆነዋል። ካልቪን ለክርስቶስ ወንጌል መኖርንና ማገልገለን የየዕለት የሕይወት ግቡ ባደረገ መሰጠት ነበር የኖረው። ይህንንም “ትንሹ የፍቅር ዕዳዬ” ይለዋል። እኛስ፣ ምን ሠርተን ይሆን የምናልፈው?

የካልቪን ጥማት የእግዚአብሔር ክብር ነበር። ይኸው በግል ሕይወቱ ሞልቶ የፈሰሰው የእግዚአብሔር ክብር ነበር፣ የቤተ ክርስቲያንና የዓለምን ዐቅጣጫ ያሰቀየረው። እንደጻፈው፣ “[ክርስቶስን በመምስል] ለማደግ ብርቱ በሆነ የውስጥ መሻት ውስጤ ነደደ” ( . . . inflamed with [an] intense desire to make progress” (John Calvin: Selections from His Writings, 35)። በአደባባይና በግል ሕይወቱ መካካል ምንም የግብዝነት ክፍተት አልነበረም። እሁድ ማለዳ በምስባኩ ላይ የሚታየው ያው ካልቪንን፣ በዚያው የወንጌል መልእክት ግለት በባዝል መንገዶችም ላይ ይታይ ነበር። 

የካልቪን የውስጥ ጩኸት በሙት ሃይማኖትኝነት፣ ከቃሉ ጋር በሚጋጭ ትውፊትና ገደብ በሌለው ፍጹማዊ የፓፓው የሥልጣን ቀውስ የተሰወረውን የክርስቶስን ልቀትና ክብር  ለትውልዱ መገለጥ ነበር። የክርስቶስ የማይቀነስበት፣ የማይጨመርበት፤ እንዲሁም አቻ የሌለው፣ ብቸኛና ብቁ የሆነ የድነት ሙሉ ሥራ የካልቪን መካከለኛ አስተምህሮ ነበር። ለካልቪን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንም ሊሸፍነው የማይገባ የእግዚአብሔር መካከለኛ ግርማ ነው። ለካልቪን የሮም  (የካቶሊክ እምብርት)፣ “. .