Get Mystery Box with random crypto!

፩. ውድ በኾነው በልጅህ ደም ዋጅተህ ከወርቅ ከዕንቁ የሚበልጥ ዋጋ ከፍለህ ማደርያህ እንዲሆን በቀ | አስተምህሮተ 🔱ክርስትና

፩. ውድ በኾነው በልጅህ ደም ዋጅተህ
ከወርቅ ከዕንቁ የሚበልጥ ዋጋ ከፍለህ
ማደርያህ እንዲሆን በቀደስከው ሕዝብህ ላይ
አቤት ስያስፈራ ግርማህ ደምቆ ሲታይ
በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
በወደድከው ሕዝብህ ላይ
ባከበርከው ሕዝብህ ላይ
የእኔ ባልከው ሕዝብህ ላይ

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል

፪. ከምሥራቅ ምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ
ትልቅ ትንሹን ከሩቅ እና ከቅርብ
እርስት አድርገህ ለራስህ መርጠሃል
ለእርሱም ርስቱ አንተው ሆነኸዋል
የዘላለም መኖርያ አምባና መታመኛው
ሞገሱና ውበቱ ብርታቱ ነህ ጉልበቱ

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል

፫. ከዓለም እርኩሰት ከዕድፈት አንጽተኸው
የንጉሥ ካህን እንዲሆን በሾምከው
የክብርህ ጸዳል በላዩ በርቶበት
ድል ነሺ ሆኗል በጠላቶቹ ፊት
ለራስህ የለየኸው
ለርስትህ የቀደስከው
በፍቅርህ የማረከው
በስራህ ያጸደከው

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል

፬. ድቅድቅ ጨለማ ወርሶት በነበረው
በአንተ ቸርነት ምህረትን ባገኘው
በዚህ ምርጥ ሕዝብ ትመሰገናለህ
በምሥጋናውም ሁሌ ትከብራለህ
ልጅ አርገህ ባቀረብከው
በስምህ በጠራኸው
ክብርህን ባካፈልከው
በቀኝህ ባስቀመጥከው

አዝማች፤
የክብርህ ጸዳል ያበራል
አንተ በመረጥከው ሕዝብህ ላይ
የራስህ ባረከው ገንዘብህ በኾነው
ርስቴ ነህ ባልከው ሕዝብህ ላይ
የክብርህ ጸዳል ያበራል