Get Mystery Box with random crypto!

አስተምህሮተ 🔱ክርስትና

የቴሌግራም ቻናል አርማ christiandoctrine — አስተምህሮተ 🔱ክርስትና
የቴሌግራም ቻናል አርማ christiandoctrine — አስተምህሮተ 🔱ክርስትና
የሰርጥ አድራሻ: @christiandoctrine
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.11K
የሰርጥ መግለጫ

በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ መሰረት= የቅዱሳት መጽሀፍት "ትምህርት "ነው ።
👌አላማችን
✔ ክርስቶስን የሚመስል፣ቅዱሳት መጸሀፍትን እና እምነቱን የሚያውቅ ክርስቲያን ማፍራት
👌የምንሰጠው አገልግሎት
✔በድምፅ ዶክትሪናል የሆኑ ትምህርቶች
✔በፅሁፍ ዶክትሪናል የሆኑ ትምህርቶች
✔በአማርኛ እንዲሁም በEnglish የተፃፉ መጽሀፍትን መቅረብ እና የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-02 09:50:48 ከዚህ በተረፈ ወንድሞቼ ሆይ፤ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ያንኑ ደግሜ ብጽፍላችሁ እኔ አይሰለቸኝም፤ ለእናንተም ይጠቅማችኋል።
ፊልጵስዩስ 3:1
621 viewsበምህረት ተሻገር, 06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 06:57:11 #በክርስቶስ #ሕያው #መሆን

1 እናንተ በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ 2 በዚህም፣ የዓለምን ክፉ መንገድ ተከትላችሁ፣ በአየር ላይ ላሉት መንፈሳውያን ኀይላት ገዥ ለሆነውና አሁንም ለእግዚአብሔር በማይታዘዙት ሰዎች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር። 3 እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንን ምኞትa እያረካን፣ መንገዱንም እየተከተልን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም የቍጣ ልጆች ነበርን። 4 ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለእኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ፣ 5 በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፣ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤ የዳናችሁት በጸጋ ነው። 6 እግዚአብሔርም ከክርስቶስ ጋር አስነሣን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፤ 7 ይኸውም በሚመጣው ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠልንን ወደር የሌለውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ነው፤ 8 በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ 9 ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም፤ 10 ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀልንን መልካም ሥራ እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።
ኤፌ 2:1-10

@christiandoctrine
614 viewsበምህረት ተሻገር, edited  03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 16:31:27 #እግዚአብሄር(አብ) ስለ #ልጁ(ኢየሱስ)

በአለም ላይ የተለያዩ ሀይማኖቶች የተለያዩ ሀሳቦች እና አመለካከቶች #በጌታችን ኢየሱስ ዙሪያ እንዳላቸው የታወቃል። አንዳዶቹ
#ነቢይ ብቻ ነበር ሲሉ ሌሎኞቹ ደግሞ #ፍጥረታትን ለመፍጠር የተፈጠረ #ፍጡር ሲሉ አንዳዶቹም መልካም #የስነ ምግባር ወይም የሞራል #አስተማሪ ብቻ ነበር ሲሉ ይደመጣሉ።

#እግዚአብሄር አብ

ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤ “አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል፤ ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣ የደስታንም ዘይት ቀባህ።” ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ በመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤ እንደ ልብስም ይለወጣሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”
ዕብራውያን 1:8-12
#ኢየሱስእርሱ #እግዚአብሄር #ነው።

@christiandoctrine
900 viewsበምህረት ተሻገር, edited  13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 09:09:49 #መናፍስትን #መርምሩ

41 ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ #አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን #መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ #ሐሰተኞች #ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና። 2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ 3 ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ግን ከእግዚአብሔር አይደለም፤ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ይህ ነው፤ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።
4 ልጆች ሆይ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤ እነርሱንም አሸንፋችኋቸዋል፤ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል። 5 እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ የሚናገሩት እንደ ዓለም ነው፤ ዓለምም ይሰማቸዋል። 6 እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን #የሚያውቅ #ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም፤ በዚህም የእውነትን መንፈስና የሐሰትን መንፈስ እናውቃለን።

1 ዮሐ 4:1-6

@christiandoctrine
535 viewsበምህረት ተሻገር, 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 09:34:34 #አሁን እኔ ድኛለሁ? ብዙዉን ጊዜ የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች ሲነሳ እና ስናነሳ ቆይተናል ። ለዚህም ጥያቄ መልስ ሐዋርያው ዮሐንስ አእንዲህ ይለናል “ትእዛዛቱን ብንፈጽም እርሱን ማወቃችንን በዚህ ርግጠኞች እንሆናለን። “እርሱን ዐውቃለሁ” እያለ ትእዛዙን የማይፈጽም ግን ሐሰተኛ ነው፤ እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም። ነገር ግን ማንም ቃሉን ቢጠብቅ፣ በእውነት የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ ፍጹም…
511 viewsበምህረት ተሻገር, 06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 09:39:12 #ልናየው እና #ልንመስለው እንናፍቃለን!

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀንም እርሱን ስላ ላወቀው ነው። ወዳጆች ሆይ፤ እኛ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደ ፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። እርሱ በሚገለጥበት ጊዜ እናየዋለንና፣ እርሱን እንደ ምንመስል እናውቃለን። በእርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ፣ እርሱ ንጹሕ እንደሆነ ራሱን ያነጻል።
1 ዮሐንስ 3:1-3

@christiandoctrine
513 viewsበምህረት ተሻገር, 06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 09:44:53 #አሁን እኔ ድኛለሁ?
ብዙዉን ጊዜ የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች ሲነሳ እና ስናነሳ ቆይተናል ።
ለዚህም ጥያቄ መልስ ሐዋርያው ዮሐንስ አእንዲህ ይለናል


“ትእዛዛቱን ብንፈጽም እርሱን ማወቃችንን በዚህ ርግጠኞች እንሆናለን። “እርሱን ዐውቃለሁ” እያለ ትእዛዙን የማይፈጽም ግን ሐሰተኛ ነው፤ እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም። ነገር ግን ማንም ቃሉን ቢጠብቅ፣ በእውነት የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ ፍጹም ሆኖአል። በእርሱ መሆናችንን የምናውቀው በዚህ ነው፤ ማንም በእርሱ እኖራለሁ የሚል፣ ኢየሱስ እንደ ተመላለሰ ሊመላለስ ይገባዋል።”
1 ዮሐንስ 2:3-6

ለእግዚያብሄር ቃል መታዘዝ የመዳናችን #አንደኛው እና #ዋነኛው #ምልክት ነው።

@christiandoctrine
468 viewsበምህረት ተሻገር, 06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 08:16:02 እንደ ብርሃን ልጆች መኖር

17 ስለዚህ ይህን እነግራችኋለሁ፤ በጌታም ዐደራ እላለሁ፤ በአስተሳሰባቸው ከንቱነት እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ልትመላለሱ አይገባም። 18 እነርሱ ከልባቸው መደንደን የተነሣ ስለማያስተውሉ ልቦናቸው ጨልሞአል፤ #ከእግዚአብሔርም #ሕይወት ተለይተዋል። 19 ኅሊናቸው ስለ ደነዘዘ በማይረካ ምኞት፣ በርኵሰት ሁሉ እንዳሻቸው ለመኖር ቅጥ ለሌለው ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።
20 እናንተ ግን ክርስቶስን ያወቃችሁት እንደዚህ ባለ መንገድ አይደለም፤ 21 በርግጥ ስለ እርሱ ሰምታችኋል፤ በኢየሱስም እንዳለው እውነት በእርሱ ተምራችኋል። 22 ቀድሞ ስለ ነበራችሁበት ሕይወትም፣ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውን አሮጌ ሰውነታችሁን አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤ 23 ደግሞም #በአእምሮአችሁ #መንፈስ #እንድትታደሱ፣ 24 እውነተኛ በሆነው ጽድቅ እንዲሁም ቅድስና እግዚአብሔርን እንዲመስል የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።
25 ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ነንና። 26 ተቈጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ፤ በቍጣችሁ ላይ ፀሓይ አይግባ፤ 27 ለዲያብሎስም ስፍራ አትስጡት። 28 ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም።
29 እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎችን የሚጠቅም ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከአፋችሁ አይውጣ። 30 ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ። 31 መራርነትን ሁሉ፣ ቍጣና ንዴትን፣ ጭቅጭቅና ስድብን ከማንኛውም ክፋት ጋር ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ። 32 እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ፣ እናንተም ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ።
ኤፌ4:17-32

@christiandoctrine
1.5K viewsበምህረት ተሻገር, 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 09:22:21 “የእግዚአብሔርን ጸጋ አላቃልልም፤ ጽድቅ በሕግ በኩል የሚገኝ ከሆነማ፣ ክርስቶስ እንዲያው በከንቱ ሞተ ማለት ነዋ!”
ገላትያ 2:21
ጽድቅ በስራ(ህግን በመጠበቅ) ወይንም በስራ + በእምነት ስንል እንዲህ እያልን ነው - "የእግዚአብሔርን የማዳን ስራ እቅድ አልተሳካም "

እኛ ክርስቲያኖች ግን የምናምነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ስለ እግዚአብሔር የደህንነት እቅድ የተናገረውን ነው ።
ዮሐ 19 :30 #ተፈጸመ!

@christiandoctrine
422 viewsበምህረት ተሻገር, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 12:20:52 አንድ ክርስቲያን አገልጋይ የአገልግሎት ጥቅሙ(ተጠቃሚያን) ቅዱሳን ቢሆኑም #ተጠያቂነቱ ለአገልግሎቱ ባለቤት ለክርስቶስ ነው ።

አሁን እኔ ጐሽ ለመባል የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሰኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንሁ ነበር።
ገላትያ 1:10

@christiandoctrine
434 viewsበምህረት ተሻገር, 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ