2022-02-26 21:10:44
: መስሎሽ ነው
ገረመሽ አይደለ፣
እስካሁኗ ሰዓት ነብስያየ ስላለ።
በሁለት እግሮቼ ቀና ብዬ ስሄድ፣
የኋላዬን ትቼ ወደፊት ስራመድ።
ሃዘን ሚባል ረስቶ ፊቴ ወገግ ሲል፣
አልጠበቅሽም አይደል?
ውስጥሽ ምን ተሰማው ልብሽ ምን ኃለየ፣
ያ ወድቋል ያልሽው ሰው ተነስቶ ስላየ።
እኮ ምን ተሰማሽ?
ያ ላ'ንቺ የሚሞተው ኖሮ በማየትሽ።
አውቃለው ገርሞሻል፣
ያለአንቺ እጎዳለው ያልኩሽን አምነሻል።
ግን ደሞ አልዋሽም፣
በገፋሺኝ ማግስት
ልቤን አቁስሎታል ናፍቆት ሆኖ ህመም
ደርሶ አዳነኝ እንጂ መርሳት ሚሉት ሀኪም
እናማ ውድዬ ምስጋና ለገፋር፣
ትላንትን አባሮ ዛሬን ለሚቀይር።
መስሎሽ ነው የኔ አለም፣
ይሀው አለው ዛሬም፣
እንደውም እንደውም።
ሳይደግስ አይጣላም አይደል የሚባለው፣
እንኳንም ጨልመሽ ጨረቃዋን አየው።
እሙ ሠላም
981 viewsƏmų şəląm, edited 18:10