Get Mystery Box with random crypto!

ጨረቅረቃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ cherekreka — ጨረቅረቃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ cherekreka — ጨረቅረቃ
የሰርጥ አድራሻ: @cherekreka
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 189

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-02-09 22:04:24 እንቆቅልሽ?
ምን አውቅልሽ?
ምንም፣
ጥያቄ ነው ያለኝ መልሱን ግን አላውቅም
ትፈቺልኛለሽ?
በውስጤ ያለውን ሁሉን ልጠይቅሽ።
በያ ቃል ግቢልኝ፣
ሆዴ ያባውን ያውጣ እኔምደሞ ይቅለለኝ።
ግን ደሞ ካቃተሽ መልሱ ካልተፈታ፣
ሀገርሽን ልትሰቺኝ በስተትሽ ፋንታ።
እንዳልመታሽ እህቴ ነሽ፣
ብዬ ፍፁም አላዝንልሽ።
እንዳልተውሽም ጠላቴ
ብዬ ብዙም አላጋነው፣
ሃገርና ሀገር ብቻ እኔ ካንቺ ምፈልገው።
ታድያ ከተስማማን በጠየኩሽ ምንዳ፣
መናገር ልጀምር ያበጠው ይፈንዳ።
ግን ደሞ ማይልኝ ይሁነን ምስክር፣
ወይ መልሴን ልሰጪኝ ወይምደሞ ሀገር።
እሙ ሠላም
694 viewsƏmų şəląm, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 21:55:08 ያቺ ሴት
ለወንድሟ አዛኝ ለልጇ ምርጥ እናት፣
አባቷን አቃፊ ለባሏ ደግ ሚስት፣
ያቺ እናት
ኢሳን ያለ አባት ብቻዋን ያመጣች፣
የአለሙን እዝነት ነቢን የወለደች።
ዘጠኝ ወር አርግዛ ለአመታት አዝላ፣
ልጇን የምትመግብ ለራሷ ሳትበላ።
ደግ እናት፣
ጀሊል ያስቀመጠው በእግሮቿ ስር ጀነት።
ያቺ ሚስት
ከአደም ከአካሉ ከጎኑ የተሠራች፣
ብቸኝነት አለም ሚስት ሆና ያስቀረች።
እመቤት ኸዲጃ ያቺ የረሡል አጋር፣
አይኖችዋ ያነቡ በእውነተኛ ፍቅር።
ለሀቅ ዘብ ቆማ ባሏን ያበረታች፣
የፋጢማ እናት ነቢን የታደለች።
ትዳሯን ጠባቂ ለባሏ ከለላ፣
ጎጆዋን አድማቂ ኢማን የምትሞላ።
ያቺ ልጅ፣
ጭንቀት ምታስረሳ ሳቅን የምትፈርጅ።
ለእናቷ እፎይታ ለአባቷ ጠባቂ፣
ደስታን የምትቸር ጎጆውን አድማቂ።
ያቺ የረሡል ስስት ውቢቷ ፋጢማ፣
ዘመንዋን የኖረች ነቢን ተሸልማ።
ያቺ እህት፣
ገመናን ደባቂ ለታናሿ እናት።
ለእህቷ ጓደኛ ለወንድሟ አዛኝ፣
ሁሌ ደግ አሳቢ ቀናን የምትመኝ።
ያቺ ሴት፣
ከፍጥረታት መሃል ጀሊል የመረጣት፣
እናት እህት አድርጎ ለአለም የሸለማት።
እኔ ነኝ አንቺ ነሽ እሷ ናት እኛ ነን፣
የልቅናን ካባ ሴትነት ያደለን።
አንቺ ነሽ አው አንቺ፣
ፍፁም ሞልቶ አይሞላም ይህአለም ያለአንቺ።
እኔ ነኝ አው እኔ፣
ለራሴ የምቆም አጃቢ ለምኔ።
እሷ ናት አው እሷ፣
ድጋፍ የማትሻ የምትቆም በራሷ።
እኛ ነን አው እኛ፣
አደራ የተሠጠን ከአላህ መልክተኛ!!
እሙ ሠላም
448 viewsƏmų şəląm, edited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 21:01:17 . አትናፍቂኝም
ጥፊ አትመለሽ፣
ከሀገር ተሰደጂ ከቀዬው ርቀሽ።
በይ ወስኚ ሂጂ፣
ሳትሰናበቺ በጊዜ ንጎጂ።
አው አትናፍቂኝም፣
በናፍቆትሽ ህመም ዘለላ አላነባም።
ሀገር ብትቀይሪ ውቅያኖስ ተሻግረሽ፣
ከማዶ ብትኖሪ ከዚ ርቀሽ ሄደሽ፣
አትናፍቂኝም እውነቴን ነው ምልሽ።
እንደውም እንደውም
ሰው ከማይኖርበት ተራራ ብትወጪ፣
ከጥልቅ ውቅያኖስ ከባህር ብትሰምጪ።
ከስምጥ ሸለቆ ገደል ገባሽ ቢባል፣
ዝር ከማይልበት አንድም ፍጡር ሚባል።
አ ት ና ፍ ቂ ኝ ም፣
ምክንያቱም፣
ስንጠፋ አብረን ነው እጅሽን አለቅም።
እሙ ሠላም
1.2K viewsƏmų şəląm, edited  18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-29 21:23:15 በሽምያ ዓለም በቅምያ ምድር፣
መተዛዘን በ'ኖ
መተሳሰብ ተ'ኖ ፍጡር ለፍጡር።
በተፈጥሮ ኩርፍያ ምድርን እየሳልኩት፣
የመኖሬ ተስፋ ጥርስሽ ላይ አየሁት።
እማ
1.1K viewsƏmų şəląm, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 22:28:45 . አትጥለቅ
እንደምን ነሽ ዓለም፣
ዛሬስ ከትላንቱ አዲስ ነገር የለም?
ዛሬ'ም እንደ ከርሞ፣
በይነጋል ተስፋ
በያልፋል መድሃኒት እራስን አስታሞ።
ዛሬም እንደ ትላንት??
የውሸት እየኖሩ የእውነት ሞት መሞት።
በሳቅ ተደብቆ የቦረቁ መምሰል፣
ለራስ እየዋሹ ህሊናን ማታለል፣
የምር ይሰለቻል።
እንደዚ ከሆነ ተይ አትንጊ ይቅር፣
ለሞት አልጠጋ እድሜዬም አይጨምር። አው አትንጊ በቃ፣
ፀሐይሽ ትደበቅ አትጥለቅ ጨረቃ፣
አንቺም ደህና ሰንብች አኛም ደሞ አንንቃ
ባለችበት ትቁም ምድር አትሽከርከር፣
እኔም በማያልቀው በህልም ዓለም ልኑር።
እሙ ሠላም
1.2K viewsƏmų şəląm, 19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 22:22:22
ዛሬ ደብዝዘሻል፣
የተኳለው ፊትሽ ደመና ጋርዶታል፣
ፈገግታሽ ቀንሷል፣
አንቺም ልክ እንደኔ የከፋሽ ይመስላል።
1.1K viewsƏmų şəląm, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 21:46:10 መች ይሆን፣
ሁሉም እንዳሰቡት እንዳለሙት ሚሆን።
ግን ይሆናል አይደል?
የጎደለው ሁሉ በጊዜው ይሞላል።
በሉዋ፣
ብላቹ ተስፋ ስጧት ለዛች ለሚስኪኑዋ።
ከዛሬ ነገ ያምራል ከነገም በስትያ፣
ችግርን አታዪም ፍፁም ካሁን ወድያ።
ተስፋ አትቁረጪ፣
ነገ ይዞ ይመጣል ብዙ አማራጪ።
ብላችሁ ንገሯት፣
እሷ ከህልሟ ውጭ ሌላ ማንም የላት፣
ያላት ትንሽ ተስፋ ከመቁረጧ በፊት።
እሙ ሰላም
1.1K viewsƏmų şəląm, edited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 20:44:01 ፡ ኢላሂ
ስምህን ጠርቼ
መቼ ሳይሆን ያውቃል፣
ተስፋዬ ባንተ ነው
ይህም ቀን ባንተ ያልፋል።
433 viewsƏmų şəląm, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-31 11:30:07
አንቺ እናት ሀገሬ፣
ብሶብሻል አሉ ከትላንቱ ዛሬ፡፡
ዋይታሽ ሩቅ ይሰማል፣
ቃቤሎችሽ በዝተው አቤልሽ ተጨንቅዋል፡፡
ሃዘንሽ በረታ ለቅሶሽ አልበርድ አለ፣
ምን ብታደርጊ ነው?
ፈጣሪ ላይረዳሽ ባንቺ ላይ የማለ፡፡
ማን ነው የረገመሽ፣
ያ ባ'ንዲት ጀንበር
ልጅና አጋሩን በቅጽበት ያጣብሽ።
ወይስ ያቺ እናት፣
አንድ የስለት ልጇ ወቶ የቀረባት፣
ከደጅ የወደቀው ያ ምስኪኑ ወጣት፡፡
ማነው በልጆችሽ ልጁን የተቀማ፣
ከላይ ቀድሞ ደርሶ ብሶቱን ያሰማ፡፡
በይ አንቺም በተራሽ
ፈጣሪን ለምኚው ብለሽ ባንተ መጀን፣
እንባሽ እሳት ሆኖ ሗላ እንዳይፈጀን፡፡
እሙ ሠላም
1.2K viewsƏmų şəląm, edited  08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 22:11:26 ፡ አላየሁም
አበባ አየሽ ወይ አደይ አበባ፣
የሚያበስረው አሮጌው አልፎ አዲስ እንደገባ፡፡
ለምን ዝም አልሺኝ ለምለም በይጂ፣
አብረን እንዘምር ጥለሽ አቲጂ፡፡
አበባ አየሽ ወይ ስልሽ በተራ፣
ለምለም እያልሽኝ ጨዋታው ይድራ፡፡
ለምን ልዋሽሽ ያላየሁትን አየሁኝ ብዬ፣
ከበራፍ በቅሎ አደይ አበባ አይኔ ካላዬ፡፡
ካላየሁትስ ከቤቴ ደጃፍ ካልተተከለ፣
አዲስ ካልገባ ካልተቀየረ አሮጌው እዳለ፡፡
ለምለም እያልኩኝ ለምን ልዋሽሽ፣
ባይሆን በቶሎ
እንክዋን ቤትና ሚለው ጋር ደርሰሽ፣
ዘንድሮም እንደ አምናው
እደጅ አዳሪ መሆኔን ልንገርሽ፡፡፡
እሙ ሠላም
1.2K viewsƏmų şəląm, edited  19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ