Get Mystery Box with random crypto!

ጨረቅረቃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ cherekreka — ጨረቅረቃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ cherekreka — ጨረቅረቃ
የሰርጥ አድራሻ: @cherekreka
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 189

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-16 20:59:08 እንዴ ልረሳሽ ባልሆነ
ልቤ ያ'ላመሉ ስምሽን ሲሰማ እንዲ የደነደነ
እንዲሁ እንደዘበት?
በሰራ አካላቴ እንዳልነገሽበት
ስሙን እረስቼ በስምሽ እንዳልማልኩ
እንዳላጣሽ ብዬ ስለት እንዳልተሳልኩ
እንዲሁ እንደቀላል?
አሁን ረሳሁሽ ብል ማንስ እኔን ያምናል
አይ አይ ቃልኮ ነበረ
በስሙ ተማምለን ከቤቱ የታሰረ
ልቤ ላይ ላኖርሽ ዘላለም ልትነግሺ
እራሴን ልሰጥሽ አካሌን ልትወርሺ
እና ምን ተገኘ
ልቤ ያለወትሮው መርሳት የተመኘ
ግን አትፍረጂበት
መናፈቅን ትቶ መርሳት ካወቀበት
ረስቶኛል አትበይኝ
አንቺ ነሽ እርቀሽ ካለን ያስበላሺኝ
አየሽ መጠበቅ ሲታክት መተው ይፀነሳል
መናፈቅ ሲያረጅ መርሳት ይወለዳል
ለካ መጠበቅ ነውጂ መርሳት ይለመዳል
እሙ ሠላም
495 viewsedited  17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 21:11:14 ምን ጉድ ነሽ
እያረሩ መሳቅ ማነው ያስተማረሽ
እስቲ በይ ንገሪኝ በተራዬ ልሳቅ
ጥርሶቼን ከፍቼ ህመሜን ልደብቅ
እኔም ልወቅበት ፈገታን ልላበስ
በሳቅ አሳብቤ ክትክት እያልኩ ላልቅስ
እሙ ሠላም
468 viewsedited  18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 19:38:24 ታምሜልሻለው በጽኑ በጠና
አበረታኝ'ጂ ያንቺ መሆን ደ'ና
ታምሜብሻለው
ምናለ ላ'ንዴኳ ህመሜን ባየሽው
33 views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 22:36:26 እኔና ዕድል ፊት'ና ጀርባ፣
እኔ ፊት ሳለው
እሱ ከጓሮ ዞሮ 'ሚገባ።
እኔና ስኬት የማንጣጣም፣
በመንደሩ ላይ እኔ ካለሁኝ
ፈጽሞ አይመጣም።
ከዕድል ጋራ የማንዋደድ፣
እኔ በዚ ስል
እሱ የሚጓዝ በሌላ መንገድ።
እሱም ረስቶኛል
ጸሎተን እንኳ' ከሰማ ቆየ፣
ከደጁ ቆሜ
እንባ ሳነባ አይቶ እንዳላየ።
ትቶ አልፎኛል፣
እሱ ረስቶኛል።
እያልኩ ከፍጡር አንተን አላማም
ሸንጎ ፊት ቆሜ አንተን አልከስም።
ግን እጠብቃለው
ከጠየኩህ በላይ የሚሻለኝን
ከእድል ይልቅ አንተ ያልከውን
ተስፋም ባንተ ነው
ስኬትም ያንተው፣
ፍጹም አልሰንፍም እጠብቃለዉ
ደሞም አምናለው።
እሙ ሰላም
15 views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 21:32:22 ማሪኝ እናት አለም፣
አ'ደለም ሳቅሽን
ኩርፊያሽ 'ሚደርስ የለም።
180 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 21:51:41 እመኚኝ ይሳካል
እኛ እንመኛለን ጀሊሉ ይሞላዋል
89 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 20:56:12 ፡ አላየሁም
አበባ አየሽ ወይ አደይ አበባ፣
የሚያበስረው አሮጌው አልፎ አዲስ እንደገባ፡፡
ለምን ዝም አልሺኝ ለምለም በይጂ፣
አብረን እንዘምር ጥለሽ አቲጂ፡፡
አበባ አየሽ ወይ ስልሽ በተራ፣
ለምለም እያልሽኝ ጨዋታው ይድራ፡፡
ለምን ልዋሽሽ ያላየሁትን አየሁኝ ብዬ፣
ከበራፍ በቅሎ አደይ አበባ አይኔ ካላዬ፡፡
ካላየሁትስ ከቤቴ ደጃፍ ካልተተከለ፣
አዲስ ካልገባ ካልተቀየረ አሮጌው እዳለ፡፡
ለምለም እያልኩኝ ለምን ልዋሽሽ፣
ባይሆን በቶሎ
እንክዋን ቤትና ሚለው ጋር ደርሰሽ፣
ዘንድሮም እንደ አምናው
እደጅ አዳሪ መሆኔን ልንገርሽ፡፡፡
እሙ ሠላም
369 views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 21:39:55 ባልጠፋ ህመም
በሞላ ስቃይ፣
ኖሮ ለሞተ
ይለቀሳል ወይ?
572 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 21:06:17 አይንጋ ግድ የለም፣
ጨረቃ እስካለች
ፀሀይ አትናፍቅም።
157 views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:32:12 መብትህን ንገረኝ ጮክ ብሎ የማውራት፣
ብለው ቢጠይቁት፣
እልል የማለት ነው ሲመጣልን መብራት፣
ብሎ ሀገሬን አሳቃት፣
መፃፍ ላይ የጻፉት መብቷን ሁሉ ነፍጓት፡፡
ግንኮ አሏሸም፣
በኛ ሀገር መጮህ ለውሻም አልበጀም፣
ታሪክ ተቀይሮ ውሻም ከቤት ውሏል፣
ባለመታየት ውስጥ ህይወቱን ቀጥሏል፡፡
ታድያ እዩኝ ብሎ ከተወረጫጨ፣
አብዷል በሚል ሰበብ ህይወቱ ተቋጨ፡፡
ታድያ ማን ሞኝ አለ፣
ሰሚ ለማያገኝ ድረሱልኝ ያለ፡፡
ዝም፣
በኛ ሀገር አሱ ብቻ አያሳስርም፡፡
ፀጥ፣
ወይ ጮሆ መሞት ነው
ወይ ሕይወትን መምረጥ፡፡
እሙ ሠላም
55 views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ