Get Mystery Box with random crypto!

. እሷ ናት እምነት ተስፋ ፅናት ፣ ትጋት እልህ ስኬት። ካንቺ ፊት ማን አየው፣ ቀድሞ | ጨረቅረቃ

. እሷ ናት
እምነት ተስፋ ፅናት ፣
ትጋት እልህ ስኬት።
ካንቺ ፊት ማን አየው፣
ቀድሞሽ ማን ጎበኘው።
ማንስ የደፈረ፣
ማን ቀድሞሽ የኖረ።
ማነው ካንቺ በፊት፣
በፅናት ሀ ብሎ
ተስፋን አስከትሎ
ስኬትን የኖራት።
ማነው እስኪ ጥሪ፣
ለፍቅር ዋስ ሚሆን ለመውደድ ተጠሪ።
እኮ ማን ተገኘ፣
ከስቃይሽ ወርሶ ላፍታ የጎበኘ፣
እናት ሆኖ ኖሮ ህመምሽን የቃኘ።
ማነው እስኪ ወንዱ፣
ፈተና የበዛበት እንዳንቺ በመንገዱ።
ማነው ያንቺን ያክል፣
ስለሌላው ሞቶ ፍቅርን የሚወክል።
ማንም፣
ካንቺ ወድያ ሌላ ከቶ አይታለም።
አንቺ ብቻ እናት፣
ሕይወትሽን ገብረሽ
የምትሰጭ ሌላ ሕይወት፣
አዎ እሷ ናት፣
እናት እህት ሕይወት፣
ደስታ ብልሃት እዝነት።
በልቧ ያጨቀች፣
ለፍቅር የኖረች፣
ለመውደድ ዋስ ሸምጋይ
በዕዝነት የታጠረች፣
እሷ ነች፣
እናት እህት ሆና ምድርን ያደመቀች።
እሙ ሠላም