Get Mystery Box with random crypto!

ግን ምን ይሆን? ቃቤል በወንድሙ እንዲ የሚያስጨክን እውነት እሷ ብቻ ወዳጁን ለማገግኘት የትዳሩን | ጨረቅረቃ

ግን
ምን ይሆን?
ቃቤል በወንድሙ እንዲ የሚያስጨክን
እውነት እሷ ብቻ
ወዳጁን ለማገግኘት የትዳሩን አቻ?
እራስ ወዳድነት ህሊናውን ወርሶት
ወይ ሴጣን አሳስቶት?
እሺ ማን እንውቀስ ለአቤል ሞት ቃቤል?
ወይስ ያቺ እንስት ቆንጅየዋ ጉብል
ማነው ፍርድ ሰጪ ማነው የእውነት ዳኛ
ለዚያ ወንድሙን ገዳይ ላ'ባቱ ደመኛ
ከቶ ማን ይፍረደው እሺ ማን ይጠራ
እኩል የሚፈርደው ሳይከፋፍል ጎራ
እሺ ማን ይለመን ማን ከችሎት ይድረስ
ሐዋን የሚያስቃት እንባዋን የሚያብስ??
በቃት!
እንባ ደርቆባታል ሳቅ ይቀየርላት።
እሙ ሠላም