Get Mystery Box with random crypto!

Campus Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ campus_group_ethiopia — Campus Students C
የቴሌግራም ቻናል አርማ campus_group_ethiopia — Campus Students
የሰርጥ አድራሻ: @campus_group_ethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.47K
የሰርጥ መግለጫ

Campus Students news.

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-08 20:50:18
በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 09 እና 10/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው የገለፀ ሲሆን ...

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ በስም አልፋቤታችሁ መሠረት

* Natural science /alphabet / A - R ፣ በዋናው ግቢ (ሆሳዕና)

* Natural science /alphabet/ S -Z ፣ ዱራሜ ካምፓስ ግቢ (ዱራሜ)

*Social science /alphabet / A - P ፣ በዋናው ግቢ (ሆሳዕና)

*Social Science /alphabet / R - Z ፣ ዱራሜ ካምፓስ ግቢ (ዱራሜ)

የተመደባችሁ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት አሳውቋል።

ምንጭ፡ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia
2.9K viewsedited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 20:50:18
ማስታወቂያ
-----------------
በ2014 ዓ.ም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባች መደበኛ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08-09/2014 ዓ.ም ሲሆን
1.በ Natural Science and Teacher Education in Natural Science የተመደባችሁ በዋናው ግቢ
2.በ Social Sciences Teacher Education in Social Science የተመደባችሁ በቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት(IOT)
መሆኑን እናሳውቃለን።
2.7K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:39:44
#WachemoUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 09 እና 10/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው
• ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት
• 3×4 ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

በ Re-admission እና Withdrawal ወጥታችሁ የነበራችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ዳግም ቅበላ ግንቦት 11 እና 12/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia
3.8K viewsedited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 20:39:44
#ASTU

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን መግለጹ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው ከአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች የሚነሱ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ለተማሪዎች ማዘጋጀቱን አሳውቋል።

የትራንስፖርት አገልግሎት ከተከታዮቹ መነሻዎች ማግኘት እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፦

• ከአዲስ አበባ መርካቶ መናኸሪያ
• ከአዲስ አበባ ቃሊቲ መናኸሪያ
• ከአዳማ ፒኮክ መናኸሪያ
• ከአዳማ ሚጊራ መናኸሪያ
• ከአዳማ ፍራንክ ሆቴል አካባቢ

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia
3.2K viewsedited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 22:51:37
#ጅማ_ዩኒቨርሲቲ

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ቀን ግንቦት 4 እና 5 ነው።

#ደብረማርቆስ_ዩኒቨርሲቲ

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ቅበላ ግንቦት 4 እና 5 /2014 ዓ/ም ይካሄዳል።

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia
3.3K viewsedited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 22:51:37
#InjibaraUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከግንቦት 09 እስከ 11/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፊኬት
ዋናውንና የማይመለስ ኮፒው
• ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና
የማይመለስ ኮፒው
• 3×4 ፎቶግራፍ (8)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia
2.9K viewsedited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 22:51:37
#BahirDarUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከሚያዚያ 28 እስከ 30/2014 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የሚገቡባቸውን ሦሥት ካምፓሶች፦ ዘንዘልማ፣ ይባብ (ግሽ አባይ) እና ሰላም ካምፓሶች ዝርዝር አሳውቋል።

( ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።)

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia
2.5K viewsedited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 22:51:37
#MettuUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ መቱ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ግንቦት 03 እና 04/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ተቋሙ ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

• ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች
ዋናውንና ኮፒው
• የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው
• የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

የስማችሁ ቀዳሚ ፊደል ከ'A-D' የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች እና የስማችሁ ቀዳሚ ፊደል 'A' የሆነ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብቻ ምዝገባችሁ የሚከናወነው በበደሌ ካምፓስ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

@campus_group_ethiopia
@campus_group_ethiopia
2.5K viewsedited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ