Get Mystery Box with random crypto!

Bank of Abyssinia

የሰርጥ አድራሻ: @boaeth
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 161.39K
የሰርጥ መግለጫ

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-01-17 15:00:46
የአቢሲንያን የሞባይል ባንክ አገልግሎት ወደ *815# በመደወል ብቻ ያለ ኢንተርኔት ወይም በስማርት ፎን መገልገል ይቻላል።


#BoAmobile #mobilebanking #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
26.7K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-13 12:27:50
ባንካችን አቢሲንያ በቢሾፍቱ ከተማ ቢሾፍቱ መናኸሪያ ቅርንጫፉ በሚገኝበት ሕንጻ ላይ ለከተማው የመጀመሪያ የሆነውን እንዲሁም አዲስ አበባ 5ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዝየም ቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከል አስመርቆ ሥራ አስጀመረ!
/
ባንካችን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች መሰል ቨርቿል ባንኪንግ አገልግሎት በማስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ የገነባውን ማዕከል አስመርቆ አገልግሎት አስጀምሯል።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የባንካችን የሥራ ሃላፊዎች እና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን ማዕከሉ 24/7 አገልግሎት የሚሠጥ ማዕከል በመሆኑ አጠቃላይ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው ማኅበረሠብ የተሻለ እና የተመረጠ ተደራሽ የባንክ አገልግሎት ማዕከል እንደሚሆን ታምኖበታል።
እንዲሁም በ5ኪሎ ብሔራዊ ሙዝየም መግቢያ በር አካባቢ በገነባው የቨርቿል ባንኪንግ ማዕከል ምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሠር አበባው አያሌው እና ሌሎች የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች፣ የባንካችን ዲፒዩቲ ቺፍ ሬቴል ቢዝነስ የሆኑት አቶ ወሰንየለህ አበራን ጨምሮ የባንካችን የሥራ ሃላፊዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።
ማዕከሉ በዋናነት የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱን ሠራተኞች በአካባቢው የሚመጡትን ቱሪስቶች፤ እና በአካባቢው ያሉ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን እና ማኅበረሰብን ከግምት በማስገባት የተከፈተ ቢሆንም 24/7 አገልግሎት የሚሠጥ ማዕከል በመሆኑ አጠቃላይ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው ማኅበረሠብ የተሸለ እና የተመረጠ ተደራሽ የባንክ አገልግሎት አማራጭ ይሆናል።
18.2K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-13 10:02:02
የ6ኛ ዙር የቴሌግራም ጥያቄና መልስ ውድድር ለተሳተፋችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ 7ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ሐሙስ ጥር 9 ከቀኑ 6:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አምስት አምስት አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!

https://t.me/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
19.2K views07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-12 15:53:51
ከታች በተጠቀሱት ቦታዎች በአለም አቀፍ ቪዛና በአቢሲንያ ቪዛ ካርድዎ የአቢሲንያ ፖስ ማሽን ላይ በመክፈል የ5% ተመላሽ እና ልዩ ሽልማቶችን ይቀበሉ። አፕ ስኬል ባር እና ሬስቶራንት- ጥር 3 እና ጥር 17 ቪላ ቨርዴ - ጥር 4 እና ጥር 18 ዘከለብ አዲስ - ጥር 5 እና ጥር 19።
ደንብ እና መመሪያዎች ይጠበቃሉ።

#PaywithVisa #Visa #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
25.2K viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-11 12:30:31
ለዝምድናችሁ ሽልማት አላችሁ!

ፈጥነው የመለሱ 10 ሰዎች ይሸለማሉ!

ጥያቄ፡- የአቢሲንያ ባንክ የቨርቹዋል ባንክ ማዕከሎች ከሚገኙባቸው ቦታዎች ውስጥ አምስቱን ጥቀሱ።

ማሳሰቢያ፡ መልስ ማስተካከል አይቻልም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከአንድ ጊዜ በላይ በተለያየ የቴሌግራም አካውንት መመለስ አይቻልም፡፡


#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
29.8K views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-10 15:02:02
በፍቅር የተላከ ገንዘብ በፍጥነት በአቢሲንያ ባንክ እናንተ ጋር ይደርሳል!
ለመጪው የጥምቀት በዓል ከውጭ አገራት በአቢሲንያ ባንክ በኩል የሚላክልዎትን ገንዘብ ሲቀበሉና ሲመነዝሩ የሞባይል አየር ሰዓት ያገኛሉ።
እስከ ጥር 19 ቀን 2016 የሚቆይ።

#holiday #newyear #Gena #BoA #chirstmas #finance #transfer #Visa #Mastercard #BankofAbyssinia #BankingService #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
21.3K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-09 15:22:08
የ5ኛ ዙር የቴሌግራም ጥያቄና መልስ ውድድር ለተሳተፋችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፣ 6ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ሐሙስ ጥር 2 ከቀኑ 6:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ በየሳምንቱ አስር አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!

https://t.me/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
27.5K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-06 09:01:09
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የደስታ እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን::
መልካም የገና በዓል!
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#Gena #Christmas #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
19.8K views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-05 11:42:43 ባንካችን አቢሲንያ 7 ቨርቹዋል የባንክ ማዕከሎችን በዛሬው እለት በተከናወነ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ሥራ አስጀመረ።

መስከረም 2013 ዓ/ም ባንካችን አቢሲንያ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ቨርቹዋል የባንክ ማዕከል አስመርቆ ሥራ ሲያስጀምር፣ ቴክኖሎጂው ለሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ ለባንክ ኢንዱስትሪው ቀዳሚ ከመሆኑ አኳያ ባንካችንን ፋና ወጊ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
ቨርቹዋል የባንክ አገልግሎት ቴክኖሎጂ ደንበኞች የባንክ ቅርንጫፍ የተገደበ የጊዜ ሰሌዳ ሳያሳስባቸው በቅርንጫፍ የሚያገኙትን አገልግሎት በቀን ለ24 ሰዓት በሳምንት ለ7 ቀናት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ ደንበኞች ከሚያገኟቸው አገልግሎቶች መካከል ሒሳብ መክፈት ፣ ገንዘብ ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ ፣ ቼክ መመንዘርና ተቀማጭ ማድረግ ፣፤ የሃገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ ሓዋላ አገልግሎት ፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፤ እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ካርድ ባንኪንግና ሞባይል መኒ ያሉ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት ምዝገባ ማከናወን ይገኙበታል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት ባንካችን ቴክኖሎጂውን በመላው ሀገራችን ለማስፋፋት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ዛሬ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ከተከናወነላቸው 7 ማዕከላት መካከል ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ በሚገኙ የክልል ከተሞች የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በደሴ፤ በመቀሌ፤ በሆሳዕና፤ በአርባምንጭ ከተሞች ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ማዕከላቱን 15 አድርሷል። በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሶስት ማእከላት የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል። ባንካችን በቀጣይ ሳምንታት የሚመረቁ አምስት የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ማእከላትን ጨምሮ በመላው ሀገራችን የሚገኙ የቨርቹዋል ባንኪንግ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትን 29 በማድረስ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ይህ ለሀገራችን የባንክ ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ የሆነው አይ.ቲ.ኤም. (Interactive Teller Machine) ቴክኖሎጂ ለባንካችን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችም በተለየ ተግባራዊ በማድረግም ባንካችን ቀዳሚ የንግድ ባንክ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
ባንካችን አቢሲንያ በሚቀጥሉት ሳምንታት የሙከራ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ተጨማሪ 5 የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከላትን አስመርቆ ስራ ለማስጀመር በሂደት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ከተመረቁት ማዕከላት መካከል በቃሊቲ፤ በጎፋ እንዲሁም በጀሞ አካባቢ ይገኙበታል።
19.2K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-05 11:42:41
18.3K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ