Get Mystery Box with random crypto!

ባንካችን አቢሲንያ በቢሾፍቱ ከተማ ቢሾፍቱ መናኸሪያ ቅርንጫፉ በሚገኝበት ሕንጻ ላይ ለከተማው የመጀ | Bank of Abyssinia

ባንካችን አቢሲንያ በቢሾፍቱ ከተማ ቢሾፍቱ መናኸሪያ ቅርንጫፉ በሚገኝበት ሕንጻ ላይ ለከተማው የመጀመሪያ የሆነውን እንዲሁም አዲስ አበባ 5ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዝየም ቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከል አስመርቆ ሥራ አስጀመረ!
/
ባንካችን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች መሰል ቨርቿል ባንኪንግ አገልግሎት በማስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በቢሾፍቱ ከተማ የገነባውን ማዕከል አስመርቆ አገልግሎት አስጀምሯል።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ የባንካችን የሥራ ሃላፊዎች እና ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን ማዕከሉ 24/7 አገልግሎት የሚሠጥ ማዕከል በመሆኑ አጠቃላይ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው ማኅበረሠብ የተሻለ እና የተመረጠ ተደራሽ የባንክ አገልግሎት ማዕከል እንደሚሆን ታምኖበታል።
እንዲሁም በ5ኪሎ ብሔራዊ ሙዝየም መግቢያ በር አካባቢ በገነባው የቨርቿል ባንኪንግ ማዕከል ምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሠር አበባው አያሌው እና ሌሎች የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች፣ የባንካችን ዲፒዩቲ ቺፍ ሬቴል ቢዝነስ የሆኑት አቶ ወሰንየለህ አበራን ጨምሮ የባንካችን የሥራ ሃላፊዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።
ማዕከሉ በዋናነት የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱን ሠራተኞች በአካባቢው የሚመጡትን ቱሪስቶች፤ እና በአካባቢው ያሉ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን እና ማኅበረሰብን ከግምት በማስገባት የተከፈተ ቢሆንም 24/7 አገልግሎት የሚሠጥ ማዕከል በመሆኑ አጠቃላይ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው ማኅበረሠብ የተሸለ እና የተመረጠ ተደራሽ የባንክ አገልግሎት አማራጭ ይሆናል።