Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ደስ አላችሁ!! ባንካችን አቢሲንያ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ እ.ኤ.አ. በማርች ወር ላይ ባ | Bank of Abyssinia

እንኳን ደስ አላችሁ!!
ባንካችን አቢሲንያ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ እ.ኤ.አ. በማርች ወር ላይ ባካሄደዉ የሴቶች የተሰጥኦ ዉድድር ላይ ተሳትፈዉ ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ተለይተዋል፡፡
በድምፅ ዉድድር ተሳትፈዉ ከነበሩት ተወዳዳሪዎች በአንደኛነት በአምላክ ጌትነት መወዳደሪያ ኮድ (M2) (100,000) የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ በሁለተኛነት ኢትዮጵያ ኢሳያስ መወዳደሪያ ኮድ (M6) (75,000) ሰባ አምስት ሺ ብር ተሸላሚ እንዲሁም በሶስተኛነት ብሩክታዊት ቱጂ መወዳደሪያ ኮድ (M5) (50,000) ሀምሳ ሺ ብር ተሸላሚ በመሆን ያሸነፉ ሲሆን ዳኝነቱም የተካሄደዉ በያሬድ ትምህርት ቤት መምህራን እና በተመልካች ምርጫ ነበር፡፡
በቲክ ቶክ በነበረዉ ዉድድር ደግሞ በአንደኛነት ሜርሲ የቲክቶክ ስም (@enun088 ) (100,000) የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ በሁለተኛነት ካልኪዳን የቲክቶክ ስም (@kal.baba10) (75,000) ሰባ አምስት ሺ ብር ተሸላሚ እንዲሁም በሶስተኛነት ያይኔአበባ የቲክቶክ ስም (@yayne_a ) (50,000) ሀምሳ ሺ ብር ተሸላሚ በመሆን ለማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
የመዝጊያ መርሀግብራችንንም በቅርቡ የምናከናዉን ሲሆን ተወዳዳሪዎችን በድጋሚ እያመሰገንን አሸናፊዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡