Get Mystery Box with random crypto!

ባንካችን አቢሲንያ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በአቢሲንያ አሚን በኩል የተለያዩ ኢፍጣር ፕሮ | Bank of Abyssinia

ባንካችን አቢሲንያ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በአቢሲንያ አሚን በኩል የተለያዩ ኢፍጣር ፕሮግራሞችን አካሄደ።

ባንካችን አቢሲንያ የ2016 ዓ.ም. የረመዳን ጾምን ምክንያንት በማድረግ በአቢሲንያ አሚን በኩል በተለያዩ የሀገራችን ቦታዎች ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም አካሂዷል።
የኢፍጣር ፕሮግራሞቹ በዋናነት የተካሄዱት በአምስት የባንካችን ዲስትሪክቶች ሥር ሲሆን፣ በባህርዳር፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፤ ምሥራቅ አዲስ ዲስትሪክት እንዲሁም በደሴ ዲስትሪክት የሚገኙበት ሲሆን፤ በደሴ ዲስትሪክት ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለው በሎጊያ ከተማ ለሚገኙ ወገኖቻችን በኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን በኩል ለማፍጠሪያ የሚሆኑ ምግቦችን በአይነት በመግዛት ለተፈናቃዮቹ አበርክቷል።
የ ባንካችን ባህርዳር ዲስትሪክት በኩል በቻግኒ ከተማ የሚገኙ ምስኪኖችንና ከተለያዩ የሀገራችን ክፍል ተፈናቅለው በከተማዋ ተጠልለው ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር በመስጊድ ራህማን ኮሜቴዎች አማካኝነት በዕለቱ የሩዝ፣የዘይትና ፍየል ድጋፍ በማድረግ ያስፈጠረ ሲሆን፣ በተጨማሪም በጎንደር ከተማ በሚገኘው ነጃሺ መስጊድ በተካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም ላይም ተሳትፏል።
በተጨማሪም፡-
የሐዋሳ ዲስትሪክት አመራሮች ከሀላባ ፣ ከሻሸመኔና ይርጋ ጨፌ ከተማ ደንበኞቻችን ጋር የኢፍጣር ፕሮግራም በማዘጋጀት እንዲሁም ቤት ለቤት በመሄድ የኢፍጣር ፕሮግራም አከናውነዋል። በተጨማሪም የዲስትሪክቱ አመራር አባላትና ሠራተኞች የእርስ በርስ ትስስርና ትብብራቸውን ለማጠናከር በጋራ የአፍጥር ፕሮግራም አዘጋጅተው ያሳለፉ ሲሆን እንዲሁም፤-
የባንካችን ምሥራቅ አዲስ አዲስትሪክት በቦሌ ጃዕፋርና ጡሩ ሲና መስጊዶች እና በአያት ጣፎ ዳሩል ሠላምና በሲኤሲ አላምራን መስጊዶች ለምስኪኖች በተዘጋጀ የኢፍጣር ፕሮግራሞች ላይ የዱቄት፣ ዘይት፣ ቴምርና እሽግ ውሃ ድጋፍ በማድረግ ተሳትፏል። በተጨማሪም የዲስትሪክቱ አመራሮችና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን የኢፍጣር ፕሮግራም ላይ ድጋፍ በማፍረግ የተሳተፉ ሲሆን የምስራቋ ፈርጥ የሆነችው ከተማም ድሬዳዋ ዲሰትሪክት በሐረር ከተማ ሐረር አራተኛ ኢማሙ አሕመድ እና መስጂድ ጃሚዕ በኩል ለተደረጉ የኢፍጣር ዝግጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
በአጠቃላይ ባንካችን ታላቁን የረመዳን ፆም ምክንያት በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች በተጨማሪም በሌሎችም ቦታዎች ከእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹና ሙስሊም ማኅበረሰቡ ጋር ወሩን በጋራ እያሳለፈ መሆኑን እየገለጽን፣ መልካም የረመዳን የፆም ወራት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።