Get Mystery Box with random crypto!

ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነ | Bank of Abyssinia

ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” 3ኛ ዙር ሙዚቃ ውድድር የተጠናቀቀ ሲሆን ለውድድሩ ከቀረቡት የሙዚቃ ስራዎች ውስጥም አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት የሹምነሽ ታዬ ፣ ሜሮን ረጋሳ እንዲሁም ሰላማዊት አራጋዉ የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በቀጣይም ከሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭ ድምፅ 30% ፣እንዲሁም በዳኞች 70% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የሙዚቃ ስራዎች ከዚህ ጋር ተያይዘው የቀረቡ በመሆኑ ከዛሬ መጋቢት 20 እስከ መጋቢት 23 ቀን 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ ይህን የፌስቡክ ሊንክ https://www.facebook.com/share/v/wSpQRyEDry49Pf6Z/?mibextid=WC7FNe በመጠቀም በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በፌስቡክ ኮመንት ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡
መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!