Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሚስጥር

የቴሌግራም ቻናል አርማ belatenaw_belatenaw — አንድ ሚስጥር
የቴሌግራም ቻናል አርማ belatenaw_belatenaw — አንድ ሚስጥር
የሰርጥ አድራሻ: @belatenaw_belatenaw
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 213
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም🙏🙏
ገጻችን በተለያዩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የተከፈተ እና አላማዉን በተለያዩ ሱሶች ፣ አጉል ልማዶች ፣ በተስፋ መቁረጥ ፣ ተስፋ በማጣት ዉስት የተዘፈቁ ወጣቶችን ከተያዙበት አላስፈላጊ ሱሶች በተለያዩ ምክሮች ድጋፎች ነጻ በማዉጣት ተስፈኛ ፣ ሀገሩን የሚወድ ወጣት ማረግ ነዉ፡፡
ለሀሳብ ለጥያቄ እና አስተያየቶ @Mysecrettbot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-30 06:59:32 ተመስገን ዛሪ ቀኑ በጣም ደስ ይላል !

የግብህን ጉዞው ልመደው
ወደ አላማህ የሚያደርስህን መንገዶች ሁሉ ልመዳቸው ። የተዋሀዱህ ባህሪህ አድርጋቸው። ባህሪህ የሆነን ነገር ሳታስብና ሳትጨነቅ እንዲሁም በማንኛውም ቦታ ያለማንም አስታዋሽነት የምታደርገው ተግባር ይሆናል ።
እንበልና አንድ ሰው “እውቅ ደራሲ መሆን አለብኝ ” ብሎ የህይወት ግብ አወጣ ።እውቅ ደራሲ ለመሆን ጎበዝ አንባቢ መሆን እንዳለበት እውን ነው ። ታዲያ ይህ ሰው በሁሉም ቦታ ማንበብ እና መፃፍን ልምዱ ማድረግ ይኖርበታል ። ታክሲ ውሥጥ ፣አውሮፕላን ውስጥ ፣ወረፋ እየጠበቀ ፣ሻይ ቤት ውስጥ ፣ ቤት ውስጥ ቢሮ ውስጥ....ሁሉም ቦታ ማንበብን ልምዱ ሊያደርግ ይገባል ።
እናም ወዳጄ አላማህን ለማሳካት ምቹ ጊዜና ቦታን የሚጠብቁ ሰዎች ከግባቸው ለመድረስ ረዥም እርቀት መጓዝ ይጠበቅባቸዋል።

መልካም ቀን ይሁንልዎ!!
share
@baletark

@dmyenefewa
95 viewsዳመና መታፈሪያ, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 07:28:05 ተመስገን ዛሪ ቀኑ በጣም ደስ ይላል !

አልጋህ ላይ ተኝተህ አጉል አትቆዝም፡፡
የመኝታ ሰዓት ካለቀ ተነስ፤ መነሳትህ ካልቀረህ አነሳስህን የጀግና አድርገው፤ አትንቀራፈፍ፡፡ እግርህ ወለሉን ፈጥኖ ይርገጥ፤ ልብህ ለፈጣሪ ምስጋና ይስጥ፤
'ቀኑን ቀደም ብለህ በወኔ ጀምር
መልካም እና የስኬት ቀን ተመኘሁ
@dmyenegewa
@baletark
80 viewsዳመና መታፈሪያ, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 09:09:59 ሰላም ቤተሰቦቻችን
የአሸናፊ ሰዎች ምሰጢር የሆነው አንዱ ምስጋና
በጣም ትንሽ ለሚባሉ ነገሮች እንኳን ምስጋና ስናቀርብ ያመሰገናቸው ነገሮች በዝተው ይመጡልናል
ስላለን ገንዘብ ምስጋና ካቀረብን የበለጠ ገንዘብ እናገኛለን።
የተዋጣም ባይሆን ለግንኙነታችን ምስጋና ብማቀርብ ግንኙነቱ እየተሻሻለ ይሄዳል።
ስለራሳችን ምስጋና ካቀረብን በስራችንም ሆነ በህልማችን እንዲሁም በህይወታችን የተሻሉ መልካም አጋጣሚዎች ይመጡልናል።
ምክንያቱም
ምስጋና በህይወት ውስጥ ያለንን የሚያባዛ መሳሪያችን ነው።
እስኪ የዛሬዋን የንጋት ፀሀይ እንድናይ ስላረከን እናመሰግናለን እንበል።
@dmyenegewa
@baletark
80 viewsዳመና መታፈሪያ, 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 08:08:13 በጣም ከምወደው የ እዮብ ማሞ telegeram page ላይ ያየሁት እና፡ የተመቸኝን ሀሳብ ላካፍላችሁ
ራስን የመቀበል ጉዞ እንጀምር!
እንዴት ናችሁ ተከታታዮቼ? መልካም ቅዳሜ እና እሁድ እንዳሳለፋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እኔና እናንተ ስንሰራ ጥሩ ቤተሰብ እንገነባለን፡፡ ጥሩ ቤተሰብ ስንገነባ ደግሞ ጥሩ ሕብረተሰብና ሃገር እንገነባለን፡፡ ስለዚህ መማር፣ መወያየት፣ ሃሳብ መለዋወጥ አናቆምም፡፡
ራሳችሁን በመለወጥ ጎዳና ውስጥ ልትለማመዷቸው ከምትችሏቸው መልካም ልምምዶች መካከል አንዱ ራስን የመቀበል ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው በፍጹም ካልተመቻችሁ ለማስተካከል ትሞክራላችሁ፣ ካልቻላችሁና ከአቅማችሁ በላይ ከሆነ ትለዩታላችሁ፡፡ ራሳችሁን ግን እደዚያ ማድረግ አትችሉም፡፡ ሁል ጊዜ ከእናንተው (ከራሳችሁ) ጋር ስለሆናችሁ ራሳችሁን በደንብ አድርጋችሁ መቀበል አለባችሁ፡፡
ራስን መቀበል - ክፍል አንድ
ራስን መሆን
ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነቴን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደሆነ ከማመን ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም፡፡ ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡
ፈጣሪ በሰጠን ማንነት ስንደላደልና ስንቀበለው ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን፡፡
ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-
1. መለወጥ ወይም ማሻሻል የምችለውን መለወጥና ማሻሻል፡፡
በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው፡፡
2. መለወጥ ወይም ማሻሻል የማልችለውን መቀበል፡፡
ዘሬን፣ መልኬን፣ አወላለዴንና የመሳሰሉትን ከፈጣሪ የተቀበልኩትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ ወይም የማይቻል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ ራሴን ተቀብዬ፣ በተደላደለ አመለካከት ዓላማዬ ላይ በማተኮር በሰላም መኖር፡፡
3. አዎንታዊነትን ማዳበር፡፡
በራሳችን ላይም ሆነ በኑሯችን ላይ ያለንን አመለካከት ከጨለምተኝነት አውጥተን ወደ አዎንታዊነት የማሸጋገር ስራ ካለማቋረጥ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ይህ ነገሬ ጎዶሎ ነው እያልን ስንጨናነቅ ከመኖር፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት መመሪያዎች እየተከተልን አዎንታዊነትን ማዳበር ተመራጭ ነው፡፡

ይቀጥላል . . .
@dmyenegewa
@baletark
84 viewsዳመና መታፈሪያ, 05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 11:17:44
የዛሪው የምክክሰር እና የትምህርት ምሽታችን የሚሰጡ ሽልማቶች
1ኛ ለወጣ በጣም ድንቅ እና ልዩ ፕሮግራም የመግቢያ ትኬት
2ኛ ለጣ በጣም አስፈለጊ የሆነ የዳዊት ድሪም ትልቅ ህልም አለኝ መፀሀፍት 3ኛ ደግሞ የ 50 ብር ካርድ ባሉበት
በመሆን ይሸለሙ
77 viewsዳመና መታፈሪያ, 08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 08:18:19
ከባዱን አሁን ስራ!

ታሪክ በአንድ ጀምበር አይሰራም! ሁሌም የማይቆም ጥረት ማድረግ አለብህ፤ የምትፈልጋቸው ነገሮች በነፃ አይገኙም ዋጋ ያስከፍላሉ ዋጋ ለመክፈል ራስህን አዘጋጅ! ወዳጄ አሁን ከባዱን ካደረክ ህይወት ቀላል ትሆናለች፤ ቀላሉን ካደረክ ግን ህይወት ትከብድሀለች!


@baletark

Share ያድርጉ
@dmyenegewa

መልካም ቀን
73 viewsዳመና መታፈሪያ, 05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 06:59:27 ስለምፈልግ ሳይሆን ስለሚያስፈልገኝ!

ሱቅ ስገባ ያየሁትን የሚያምር ነገር ሁሉ የመግዛቴንና ያለመግዛቴን ነገር የሚወስንልኝ መግዛት የመቻሌና ያለመቻሌ፣ የመፈለጌና ያለመፈለጌ ሁኔታ ብቻ አይደለም፡፡ የሚያስፈልገኝንና የማያስፈልገኝን ነገር በሚገባ አውቃለሁ፡፡

ከምተዋወቃቸው ደስ የሚሉ ሰዎች ሁሉ ጋር ወዳጅ የመሆንና ያለመሆንን ምርጫ የሚወስንልኝ ጓደኝነት ለመፍጠር የመቻሌና ያለመቻሌ፣ የመፈለጌና ያለመፈለጌ ሁኔታ ብቻ አይደለም፡፡ ከዓላማዬና ከእሴቶቼ አንጻር የሚያስፈልገኝንና የማያስፈልገኝን ወዳጅነት ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

አንዳንድ ቦታዎች የመሄዴንና ያለመሄዴን ሁኔታ የሚወስንልኝ መሄድ መቻሌና አለመቻሌ፣ መፈለጌና አለመፈለጌ ብቻ አይደለም፡፡ መሄድ በሚያስፈልገኝና በማያስፈልገኝ ቦታ መካከል ያለውን ልዩነት አጥርቼ አውቃለሁ፡፡

አዋቂዎች አቅማቸውንና የሚፈልጉትን ያውቃሉ፣ በእውቀት ላይ ጥበብን የጨመሩት ደግሞ አቅምና ፍላጎት እያላቸው እንኳን የሚፈልጉትንና የማይፈልጉትን በሚገባ ያገናዝባሉ፡፡
ምንጭ D/eyob mamo page
@Dmyenegewa
@baletark
71 viewsዳመና መታፈሪያ, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 12:22:39 ሰላም ሰላም

በጉጉት ስትጠበቅ የነበረችው የመጀመሪያዋ ኩታ - መጽሄት ቅፅ አንድ ዛሬ ለንባብ በቅታለች።
ቤተሰብ እንፍጠር - ለወዳጅ ዘመድ ማጋራቶዎን አይርሱ።

መርሀባ
!

@more_more_more
@more_more_more
@more_more_more
99 views ናፌስ, 09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-02 16:12:10
165 viewsዳመና መታፈሪያ, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ