Get Mystery Box with random crypto!

በጣም ከምወደው የ እዮብ ማሞ telegeram page ላይ ያየሁት እና፡ የተመቸኝን ሀሳብ | አንድ ሚስጥር

በጣም ከምወደው የ እዮብ ማሞ telegeram page ላይ ያየሁት እና፡ የተመቸኝን ሀሳብ ላካፍላችሁ
ራስን የመቀበል ጉዞ እንጀምር!
እንዴት ናችሁ ተከታታዮቼ? መልካም ቅዳሜ እና እሁድ እንዳሳለፋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እኔና እናንተ ስንሰራ ጥሩ ቤተሰብ እንገነባለን፡፡ ጥሩ ቤተሰብ ስንገነባ ደግሞ ጥሩ ሕብረተሰብና ሃገር እንገነባለን፡፡ ስለዚህ መማር፣ መወያየት፣ ሃሳብ መለዋወጥ አናቆምም፡፡
ራሳችሁን በመለወጥ ጎዳና ውስጥ ልትለማመዷቸው ከምትችሏቸው መልካም ልምምዶች መካከል አንዱ ራስን የመቀበል ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ሰው በፍጹም ካልተመቻችሁ ለማስተካከል ትሞክራላችሁ፣ ካልቻላችሁና ከአቅማችሁ በላይ ከሆነ ትለዩታላችሁ፡፡ ራሳችሁን ግን እደዚያ ማድረግ አትችሉም፡፡ ሁል ጊዜ ከእናንተው (ከራሳችሁ) ጋር ስለሆናችሁ ራሳችሁን በደንብ አድርጋችሁ መቀበል አለባችሁ፡፡
ራስን መቀበል - ክፍል አንድ
ራስን መሆን
ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነቴን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደሆነ ከማመን ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም፡፡ ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡
ፈጣሪ በሰጠን ማንነት ስንደላደልና ስንቀበለው ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን፡፡
ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-
1. መለወጥ ወይም ማሻሻል የምችለውን መለወጥና ማሻሻል፡፡
በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው፡፡
2. መለወጥ ወይም ማሻሻል የማልችለውን መቀበል፡፡
ዘሬን፣ መልኬን፣ አወላለዴንና የመሳሰሉትን ከፈጣሪ የተቀበልኩትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ ወይም የማይቻል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ ራሴን ተቀብዬ፣ በተደላደለ አመለካከት ዓላማዬ ላይ በማተኮር በሰላም መኖር፡፡
3. አዎንታዊነትን ማዳበር፡፡
በራሳችን ላይም ሆነ በኑሯችን ላይ ያለንን አመለካከት ከጨለምተኝነት አውጥተን ወደ አዎንታዊነት የማሸጋገር ስራ ካለማቋረጥ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ይህ ነገሬ ጎዶሎ ነው እያልን ስንጨናነቅ ከመኖር፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት መመሪያዎች እየተከተልን አዎንታዊነትን ማዳበር ተመራጭ ነው፡፡

ይቀጥላል . . .
@dmyenegewa
@baletark