Get Mystery Box with random crypto!

ስለምፈልግ ሳይሆን ስለሚያስፈልገኝ! ሱቅ ስገባ ያየሁትን የሚያምር ነገር ሁሉ የመግዛቴንና ያለመግ | አንድ ሚስጥር

ስለምፈልግ ሳይሆን ስለሚያስፈልገኝ!

ሱቅ ስገባ ያየሁትን የሚያምር ነገር ሁሉ የመግዛቴንና ያለመግዛቴን ነገር የሚወስንልኝ መግዛት የመቻሌና ያለመቻሌ፣ የመፈለጌና ያለመፈለጌ ሁኔታ ብቻ አይደለም፡፡ የሚያስፈልገኝንና የማያስፈልገኝን ነገር በሚገባ አውቃለሁ፡፡

ከምተዋወቃቸው ደስ የሚሉ ሰዎች ሁሉ ጋር ወዳጅ የመሆንና ያለመሆንን ምርጫ የሚወስንልኝ ጓደኝነት ለመፍጠር የመቻሌና ያለመቻሌ፣ የመፈለጌና ያለመፈለጌ ሁኔታ ብቻ አይደለም፡፡ ከዓላማዬና ከእሴቶቼ አንጻር የሚያስፈልገኝንና የማያስፈልገኝን ወዳጅነት ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

አንዳንድ ቦታዎች የመሄዴንና ያለመሄዴን ሁኔታ የሚወስንልኝ መሄድ መቻሌና አለመቻሌ፣ መፈለጌና አለመፈለጌ ብቻ አይደለም፡፡ መሄድ በሚያስፈልገኝና በማያስፈልገኝ ቦታ መካከል ያለውን ልዩነት አጥርቼ አውቃለሁ፡፡

አዋቂዎች አቅማቸውንና የሚፈልጉትን ያውቃሉ፣ በእውቀት ላይ ጥበብን የጨመሩት ደግሞ አቅምና ፍላጎት እያላቸው እንኳን የሚፈልጉትንና የማይፈልጉትን በሚገባ ያገናዝባሉ፡፡
ምንጭ D/eyob mamo page
@Dmyenegewa
@baletark