Get Mystery Box with random crypto!

ተመስገን ዛሪ ቀኑ በጣም ደስ ይላል ! የግብህን ጉዞው ልመደው ወደ አላማህ የ | አንድ ሚስጥር

ተመስገን ዛሪ ቀኑ በጣም ደስ ይላል !

የግብህን ጉዞው ልመደው
ወደ አላማህ የሚያደርስህን መንገዶች ሁሉ ልመዳቸው ። የተዋሀዱህ ባህሪህ አድርጋቸው። ባህሪህ የሆነን ነገር ሳታስብና ሳትጨነቅ እንዲሁም በማንኛውም ቦታ ያለማንም አስታዋሽነት የምታደርገው ተግባር ይሆናል ።
እንበልና አንድ ሰው “እውቅ ደራሲ መሆን አለብኝ ” ብሎ የህይወት ግብ አወጣ ።እውቅ ደራሲ ለመሆን ጎበዝ አንባቢ መሆን እንዳለበት እውን ነው ። ታዲያ ይህ ሰው በሁሉም ቦታ ማንበብ እና መፃፍን ልምዱ ማድረግ ይኖርበታል ። ታክሲ ውሥጥ ፣አውሮፕላን ውስጥ ፣ወረፋ እየጠበቀ ፣ሻይ ቤት ውስጥ ፣ ቤት ውስጥ ቢሮ ውስጥ....ሁሉም ቦታ ማንበብን ልምዱ ሊያደርግ ይገባል ።
እናም ወዳጄ አላማህን ለማሳካት ምቹ ጊዜና ቦታን የሚጠብቁ ሰዎች ከግባቸው ለመድረስ ረዥም እርቀት መጓዝ ይጠበቅባቸዋል።

መልካም ቀን ይሁንልዎ!!
share
@baletark

@dmyenefewa