Get Mystery Box with random crypto!

Bahir Dar University,Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ bahir_dar_university — Bahir Dar University,Ethiopia B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bahir_dar_university — Bahir Dar University,Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @bahir_dar_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.56K
የሰርጥ መግለጫ

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses!

www.bdu.edu.et

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-28 16:26:48 የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ

የባሕር ዳር
ዩኒቨርሲቲ ባሕል ማዕከል እና የዩኒቨርሲቲው 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ኤግዚቪሽን ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከባሕር ዳር ከተማ ከካቶሊክ ት/ቤት፣ከSOS ትምህርት ቤት፤STEM ትምህርት ቤቶች የመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከባሕር ዳር ዩኒቨርቲ ግቢዎች መካከል ሰላም ካንፓስ፣ የቴክኖሎጂ ተቋም (ፖሊ) እና ፔዳ ግቢን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ የከፈቱት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ክፍል የሳይኮሎጂ መምህር አቶ ታምሩ ደለለኝ ስለ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጠቅለል ያለ መረጃ ከአመሰራረቱ ጀምሮ አሁን እስካበት ደረጃ ያለውን የ60 ዓመት ጉዞ ታሪክ እና ያሳለፋቸውን ሁነቶች እንዲሁም በዚህ ዩኒቨርሲቲ ተምረው ትላልቅ ደረጃ ስለደረሱ፣ በአመራር ላይ ስላሉ ግለሰቦች፣ ስለ ትምህርት አሰጣጥ ጥራቱ ለተማሪዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመቀጠልም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሙዚየም ባለሙያ ወ/ሮ ኤልዳና ደሳለኝ የዚህ ጉብኝት ዓላማ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ60ኛ ዓመት ጉዞው ውስጥ ምን እንዳደረገ እና የት እንደደረሰ ለማስተዋወቅ በተጨማሪም እኒህ የሚጎበኙ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲውን ምንነት አውቀው ለወደፊቱ ተመራጭ እንዲያደርጉት፣ ስለዩኒቨርሲቲ ያላቸው ንቃተ ህሌናም ከፍ እንዲል ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወ/ሮ ኤልዳና ወደ ፊት በባህር ዳር ከተማ ስር ያሉ ሌሎች የመንግስት ተማሪዎችም በዚህ ጉብኝት እንደሚሳተፉ እና ፕሮግራሙም እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም እንደሚቆይም ገልጸዋል፡፡ ከትምህርት ቤቶች የመጡ ተማሪዎች ስለጉብኝቱ ከሰጡት ሀሳብ መካከል ከSTEM ማበልጸጊያ ማዕከል የመጣው ተማሪ ዮናታን አባይነህ ጉብኝቱ ጥሩ እንደሆነ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት ተመልክቶ ታሪኮችን ሰምተናል፡፡ የሰማነው ታሪክ ደስ የሚል ነበር፤ እኛም በዚህ ዩኒቨርሲቲ ገብተን እንዲህ ያለ ታሪክ እንደሚኖረን ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡ ተማሪ ዮናታን አክሎም የተለያዩ ነገሮችንም አይተናል ይህን እድል ያላገኙት ሌሎች ተማሪዎችም እንዲጎበኙ ዩኒቨርሲቲው ቢያመቻችላቸው ሲል ሀሳቡን ገልጿል፡፡
ከSOS ትምህርት ቤት የመጣችው ተማሪ አና ያረጋል ጉብኝቱ አስደሳች እንደሆነና ሌሎች ተማሪዎችም እድሉ ቢመቻችላቸው እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደፊት የመማር እድሉ ቢገጥመኝ ደስተኛ ነኝ ብላለች፡፡ ሌላዋ ተማሪ ከካቶሊክ ትምህርት ቤት የመጣችው ናርዶስ ኃይሌ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመቱን አስቦ እኛን በመጥራቱ ደስተኛ ነን፡፡ ምክንያቱም የብዙዎቻችን ህይወት እዚህ ዩኒቨርሲቲ ላይ በመመስረቱና ብዙ ነገሮችን ማየት በመቻላችን ደስተኛ ነን ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን አይተን አናውቅም እናም ይህን እድል በማግኘታችን እናመሰግናለን፤ ትምህርት ቤቱ ወደ ፊትም እንዲህ አይነት ጉብኝቶችን ቢያዘጋጅ ጥሩ ነው ለተማሪዎች መነሳሳትን ይፈጥራል ብላለች፡፡

https://t.me/bahir_dar_university
2.1K viewsedited  13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 16:44:38 #TGSH
ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ሕክምና በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል!!!
===============================================

(መጋቢት 18፣2015 ዓ.ም፣ባሕር ዳር)፦በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምና ትምሕርት ክፍል Fight Blindness in Ethiopia ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት እየሰጠ ነው።

የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱም በሞራ ግርዶሽ ምክኒያት ለማየት የተቸገሩ ታካሚዎችን እይታ ለመመልስ ያለመ ሲሆን እስከ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም  የሚሰጥ ይሆናል።

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
SHARE SHARE
2.0K viewsedited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 14:39:00
Original Airpods
#wireless Earphone
ይዘዙን ካሉበት ግቢ #ያለተጨማሪ ክፍያ እናመጣለዎታለን!!!  Free delivery

ወደ መሀል ከተማ መምጣት ለምትችሉ ይህንን አድራሻ መጠቀም ትችላላችሁ
አድራሻ: ለምለሚቱ ህንፃ ፊት ለፊት  ለምለም የሞባይል  ማዕከል ሱቅ ቁ.8A(ጣና-ቴክ)

0909524780 / SMS
0993489110  ይደውሉ ወይም
@Online9110  ያናግሩን

Contact: @Seen311

Join us
@tanatechshop
@tanatechshop
2.1K views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 14:04:50
የጥሪ ማስታወቂያ
በ2015 ዓ/ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ“Remedial” ፕሮግራም ለመከታተል ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

https://t.me/bahir_dar_university
1.7K viewsedited  11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 06:48:53
3.8K views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 06:48:33 127ኛውን #የአድዋ_ድል ብሔራዊ ቀን ዋዜማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተከበረ

(የካቲት 22/2015 ዓ/ም ፣ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 127ኛውን የአድዋ ድል በዓል በማስመልከት የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር ድረስ ሳህሉ፣የጥንታዊ ኢትዮጱያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የአማራ ክልል የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ዳኝነት አያሌዉ፣ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በዊዝደም ህንፃ ጥበብ አዳራሽ በኪነ ጥበብ ስራዎችና በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

“አድዋ! የኢትዮጱያ ሕብረ ብሔራዊነት ቋሚ መዘክር፤የአፍሪካውያን ነፃነት ቀንድል” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የ127ኛው የድል በዓል ዋዜማ ላይ ለተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ የአድዋ ጦርነት በየካቲት 23 ቀን 1896 ዓ.ም በኢትዮጵያና በኢጣሊያ መካከል የተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ውጊያው በኢትዮጵያ አሸናፊነት የተጠናቀቀ እና የጣሊያኖች የቅኝ ግዛት መስፋፋት እቅድ ሳይሳካ የቀረበት ታላቅ ድል ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር እሰይ አክለውም የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማህተም፤የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል እና የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ፤ የአንድነታችን አርማ በመሆኑ ሁሌም ስንዘክረው እንኖራለን ብለዋል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የባሕርዳር ከተማ ከንቲቫና የዩኒቨርስቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር ድረስ ሳሕሉ በበኩላቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በዓሉ የዚያን ዘመን አድዋ እያከበርን የዛሬ የኛን አድዋ ድል ለማድረግ የምንሰራበት ነው ብለዋል። በመካከላችን መከባበርና መደማመጥ፣ የታሪክን ጠቃሚ ክፍል መገንዘብና ለጋራ እሴት መስራት ትልቅ ቁምነገር ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት ተናግረዋል።

በታላቅ ድምቀት በተከበረው በዚሁ የዋዜማ ዝግጅት ላይ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና በተጋባዥ እንግዶች ግጥሞች፣ መነባንቦች እና በዓሉን የሚያወድሱ ሙዚቃዎች ለተሳታፊዎች ቀርበው ታዳሚውን በደስታ አስፈንድቀዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመረማሪ የሆኑት ዶ/ር ገረመዉ እስከዚያ በዓሉን አስመልክተው ለተሳታፊዎች በአቀረቡት ፅሁፍ በጦርነቱ ወቅት 7000 አካባቢ የጠላት ወታደሮች ሲገደሉ፤ 470 ጣሊያን እና 958 ጥቁር ወታደሮች በጠቅላላዉ 1428 የጠላት ወታደሮች ቆስለዋል፤ 3000 ደግሞ የጦር ምርኮኞች ሆነዋል፤ 11000 ጠመንጃ እና 56 መድፎች በሙሉ ተማርከዋል፤ በኢትዮጵያዊያን በኩልም ደግሞ 4000-6000 ተዋጊ ሲሞት 8000 ደግሞ መቁሰላቸውን የተለያዩ ዋቢዎችን በመጥቀስ የገለፁ ሲሆን ጀግኖች አባቶቻችን አድዋ ላይ በከፈሉት መስወዕትነት ኢትዮጵያ አገራችን ነጻነቷን አስከብራ የአፍሪካ ብቸኛ ነጻ ሀገር ሆና ለመቆየት በቅታለች ብለዋል፡፡ አክለውም የአድዋ ድል ለአፍሪካ እና በጠቅላላዉ ለጥቁር ሕዝቦች መመኪያና ኩራት ሆኖ ይኖራል ብለዋል፡፡

https://t.me/bahir_dar_university
3.7K viewsedited  03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 23:12:47 ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም #አዲስ_ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው

(የካቲት 20/2015) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ሳይንስ ኮሌጅና በግሽ ዓባይ ግቢ አዲስ የተመደቡ ተማሪዎችን የተማሪዎች ቅበላ ግብረ-ሃይል ከተማሪዎች ዲን፣ ከስምሪትና ትራንስፖርት ክፍል እና ከተማሪዎች ህብረት የተውጣጣ ቡድን እየተቀበለ ነው፡፡

አዲስ ከሚገቡ ተማሪዎች መካከልም ከማቻከል ወረዳ፣ ሸለል ቀበሌ የመጣ፣ ተማሪ መኮነን አዲስ ከመናኸሪያ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው በአውቶብስ እንደመጡ እና አቀባበሉ ጥሩ እንደሆነ ይገልፃል፡፡ ሌላዋ ከደብረዘይት ቢሾፍቱ ከተማ የመጣችው ተማሪ ገሊላዊት እንደሻው ስትሆን በር ላይ አስተባባሪዎች ሻንጣቸውን ተቀብሎ እንዳስገቧቸውና በታም ደስ የሚል አቀባበል ዩኒቨርሲቲው እንዳደረገላቸው፣ ምግቡም እንደተመቻት እና ዶርማችንንም አዘገጃጅተን ጨርሰናል። አሁን የቀረን ግቢውን ማየት ነው በአጠቃላይ አቀባበሉ በጣም እንዳስደሰታት ተናግራለች፡፡ ከሰሜን ወሎ ዞን የመጣው ተማሪ ድስታው ተመስገን አቀባበሉን ከጠበቅኩት በላይ ነው ያገኘሁት በጣም ተመቶኛል ይላል፡፡

ልጆቻቸውን ሊያደርሱ ከአዲስ አበባ የመጡት አቶ አምለክ የበረከት አምላክ አባት እንዲሁም ከጎንደር የመጡት እና የተማሪ ፍቅሩ ደሳለኝ እናት የሆኑት ወይዘሮ ሀና ጌጡ እጅግ መልካም አቀባበል ነው ዩኒቨርሲቲው ያደረገልን አሰራራቸው ጥሩ ነው፤ ይበል የሚያሰኝ ነው ሲኔር ተማሪዎችንም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

የባሕር ዩኒቨርሲቲ ዘንዘልማ ካምፓስ የተማሪ አቀባበል አስተባባሪ የአራተኛ አመት ተማሪ የሆነችው መክሊት ሙሏለም ተማሪዎችን ከጠዋት ጀምሮ እየተቀበሉ እንዳሉና ተማሪዎችን በሚቀበሉበት ጊዜ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠማቸው ያለው ድባባ ደስ እንደሚል ገልጻለች

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
3.7K views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 21:32:09
3.2K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 21:31:48 ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ
********

(የካቲት17/2015 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ/ም በመደበኛው መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲው የተመደቡ የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከባሕር ዳር ከተማና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮች፤የጸጥታ አካላት፤የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎች እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የሰላም ምክር ቤት ኮሚቴ አባላት ጋር የተማሪዎችን አቀባበል በተመለከተ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች  ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ   እንደገለጹት  ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በዚህ አመት  5,187 ተማሪዎች መርጠውታል፡፡ ዩኒቨርሲቲውም ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት አድርጓል፡፡ ይህ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አንጻር ሲዎዳደር በጣም ትልቅ  ቁጥር ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ እንድንመረጥ ያደረጉንም በጣም ብዙ ምክኒያቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ የመማር ማስተማር ስራዎች አቅምና ብቃት፤ የመልካም አስተዳደር ስራዎች፤ ዩኒቨርሲቲው  የሚገኝበት  ከተማ እና ማኅበረሰብ ሰላማዊ መሆን ከምርጫው ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው ብለዋል፡፡
ዶ/ር እሰይ ከበደ አክለውም  ባሕር ዳር እንደቤቴ መርሀ ግብርም ለአንድ አዲስ ተማሪ አንድ  የቃል ኪዳን  ቤተሰብ ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ልክ እንደ ቤተሰብ ሆኖ በቆይታቸው ተንከባክቦና ደግፎ  እንደቤታቸው  እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራጋው ብዙዓለም በበኩላቸው ተማሪዎች አንድን  ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ከተማሪዎች ባሻገር የቤተሰብ ይሁንታም  ትልቁን  ቦታ ይይዛል፡፡ ቤተሰብ ስለ ዩኒቨርሲቲው መገኛ አካባቢ ያለው መረጃ እና የሚሰማው ስሜት በራሱ ትልቅ ድርሻ  ይኖረዋል፡፡  ባሕር ዳር ውበቷና ድምቀቷ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተፈጥሮ ለሚዋደዱ ሰዎች እንደ ጣና ያለ መዝናኛ  ያላት፡፡ መንፈሳዊ ነገር ለሚያሻቸው ደግሞ ገዳማቷ አይጠገቡም ብለዋል፡፡ ሁሉም ባለድርሻ አካላትም በትኩረት በተማሪዎች ቅበላ ላይ በመሳተፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አቶ አራጋው ብዙዓለም ገልጸዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጸጥታና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ኢኒስፔክተር ሀብታሙ መለሰ እንደተናገሩት ተማሪዎች ደህንነትና ሰላምን ጠብቆ ቅበላውን ለማካሄድ የዩኒቨርሲቲው የጸጥታ አካላት ከሌሎች በከተማው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት እና የፌዴራል ፖሊስ ጋር በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ዶ/ር በላይ ተፈራ ተማሪዎችን ለመቀበል አስፈላጊው ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ተማሪዎች የሚገቡባቸውን ግቢዎች የማሳወቅና የዶርም እና የአልጋ ድልድል እና ተያያዥ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋርም ተማሪዎችን በቅንጅት ለመቀበል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡
የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ጥበበ ሰሎሞን በበኩሉ ተማሪዎች የሚገቡባቸው የዘንዘልማና የግሽ ዓባይ ግቢዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ተማሪዎችን ለመቀበል ህብረቱ ከተማሪዎች ዲን ጽ/ቤት ጋር በመሆን እየሰራ ሲሆን አዲስ ተማሪዎችም ስለዩኒቨርሲቲው ህግና ደንብ እንዲሁም ስለግቢዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዝግጅት ተደርጓል ብሏል፡፡

https://t.me/bahir_dar_university
3.2K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 22:24:03 #ለዲስ ገቢ ተማሪዎች ነባር ተማሪዎች መረጃ ሊሰጧችሁ ዝግጁ ናቸው !
ሁላችሁንም እናመሰግናለን!

#1. Mechanical engineering....0906304335/@habutii1
#2. Accounting and finance 3rd yr username høpz
#3.  Civil Eng.
User name   @Ab3093
#4. 0704726457...medicine
#5. Daniel Hailemariam.
2nd veterinary medicineat zenzelima 0983581906

#6. Yibab campus
0982777167
#7. @wub1624
Poly , 2nd information system
#8. habtu    poly mechanical [0963815904
#9.@Harris631
.Name harris toyb
.Desaster and risk management  and food security
Zenzelim 0964310308

#10. @ELIAS_E101
CS  2nd year   
0920526295

#11.Rediat,informatin system 4th 0703532788
#12. Name Ake, Zenzelima
0928116602
#13. @ansteb1102
3rd textile engineering
#14. @Merrrrry
Management department

ሌሎችም  @bdu2015bot ላይ ላኩልን

አስተያየትና መረጃ ለመስጠት  @bdu2015bot

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university

Share share share
1.9K viewsedited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ