Get Mystery Box with random crypto!

Bahir Dar University,Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ bahir_dar_university — Bahir Dar University,Ethiopia B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bahir_dar_university — Bahir Dar University,Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @bahir_dar_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.56K
የሰርጥ መግለጫ

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses!

www.bdu.edu.et

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-09-03 11:58:15 #TGSH
ታላቅ የምስራች
==========
ከነሐሴ 30- ጷግሜ 4/2014 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------

1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ህሙማን ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እንሳተላልፋለን::

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

@bahir_dar_university
@bahir_dar_university
share
441 viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:08:23
3.3K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:08:20
3.3K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:07:08 #TGSH,BDU
እንኳን ደስ አላችሁ (Congratulations)!!!
============================
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6515 ተማሪዎችን በደማቅ ሥነ-ስርዓት አስመረቀ።

(ነሐሴ 21፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከቅድመ-ምረቃ እስከ ድኅረ-ምረቃ በተለያዩ የትምህርት መስኮች የክብር እንግዶች እና በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት 6515 ተማሪዎችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት በዛሬዉ እለት አስመረቀ።

ከተመራቂዎች መካከል 237 የሚሆኑት ከሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲሆኑ 127 ተመራቂዎች ደግሞ የሕክምና ዶክተሮች ናቸዉ። ኮሌጁ በተጨማሪም 70 የ2ኛ እና 2 የ3ኛ ድግሪ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በእለቱ በትምህርት ቆይታቸዉ ከፍተኛ ዉጤት ለአስመዘገቡ ተማሪዎች የእዉቀናና የሽልማት መርሀ-ግብር ተካሂዷል። በዚህም መሰረት ከሕክምና ምሩቃን መካል 3.77 ዉጤት በማምጣት 1ኛ የወጣዉ ዶ/ር እንዳለ ለማ መታፈሪያ ሲሆን የሜዳሊያ ተሸላሚም ሆኗል። ዶ/ር ንብረቴ ታደሰ አልማዉ 3.73 አማካይ ዉጤት በማምጣት 2ኛ ወጥታለች። ዶ/ር ቢኒያም ፍስሀ አበራ ደግሞ 3.67 አማካይ ዉጤት በማምጣት 3ኛ ሆኗል።

ከሴት ተመራቂ የሕክምና ዶክተሮች መካከል ዶ/ር ንብረቴ ታደሰ አልማዉ 3.73 በማምጣት አንደኛ ሆናለች።

ሌላዉ የሽልማት ዘርፍ ሐኪሞች በሆስፒታል ዉስጥ በአረቱ የሕክምና ትምህርት ክፍሎች በሚሰጡት የሕክምና አገልግሎት የላቀ ዉጤት ለአስመዘገቡ (Best Intern Award) የ'ምርጥ ኢንተርን ሽልማት‘ሲሆን በዉስጥ ደዌ ሕክምና ዶ/ር ስሜነህ ጋሹ ሽፈራዉ፣ዶ/ር ማስተዋል ደበበ ታደሰ እና ዶ/ር አማኑኤል አማረ ኪዳኔ እንደቅደም ተከተላቸዉ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመዉጣት ሽልማቱን አሸንፈዋል። ከሕጻናት ሕክምና ደግሞ ዶ/ር ሀይለሚካኤል ዋሴ ምስጋናዉ፣ዶ/ር መንግስቱ ሙሉቀን ሀይሌ እና ዶ/ር ኤግላ ሰለሞን ቤየነ በቅደም ተከተል ከ1ኛ-3ኛ በዉጣት የሽልማቱ አሸናፊ ሆነዋል።እንዲሁም ከቀዶ ጥገና ሕክምና ዶ/ር ስሜንሀ ጋሹ ሻረዉ፣ዶ/ር ቤቴል ዮሃንስ በቀለ እና ዶ/ር ንብረቴ ታደሰ አልማዉ እንደ ቅደም ተከተላቸዉ ሽልማቱን አሸንፈዋል። ከማህጸንና ጽንስ ደግሞ ዶ/ር ምንግስቱ ሙሉቀን ሀይሌ፣ዶ/ር ንብረቴ ታደሰ አልማዉ እና ዶ/ር ስሜንሀ ጋሹ ሻረዉ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በማሸነፍ ሽልማታቸዉን ከክብር እንግዶች እጅ ተረክበዋል።

ሌላኛዉ የሽልማት ዘርፍ የ‘ፕሮፌሰር ዕደማሪያም ፀጋ አካዳሚክ ልህቀት በሕክምና ሽልማት’ (Professor Edmariam Tsega Academic Excellence Award in Medicine) ሲሆን ከተመራቂ የሕክምና ዶክተሮች መካከል ዶ/ር ንብረቴ ታደሰ አልማዉ ተሸላሚ ሆናለች።

በሽልማት መርሀግብሩ ላይም የሐኪም ወርቅነህ መላኩ በያን ሶሳይቲ (Hakim Workneh and Melaku Beyan Society Inc.) ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘርጋባቸዉ አስፋዉ ተገኝተዉ ለተመራቂዎች መልት አስተላልፈዋል።

ከ2ኛ ድግሪ ተመራቂዎች መካከል ምርጥ (Best Thesis Award) የምርመር ስራ ሽልማት ዘርፍ ደግሞ ፍቃደ ዳኘዉ ባዬ ከጤና ሳይንስ ትምሕርት ቤት፣ምንይችል ብርሀኑ በለጠ ከሕብረተሰብ ጤና ትምሕርት ቤት እንዲሁም ዘላም ብርሃን ከተማ ከሕክምና ትምህርት ቤት አሸንፈዋል።

በእለቱ ዩኒቨርሲቲዉ ለሀገራችን በአበረከቱት ከፍተኛና ዘመን አይሽሬ አስተዋጽዋቸዉ ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ እና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ሽልማ ሰጥቷቸዋል።

በድጋሜ ዉድ ተመራቂዎች፣ መምህራንና የተመራቂ ቤተሰቦች፤
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
3.0K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:47:51
3.0K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:46:21
#textile,BDU
የኢትዮጵያ ቴከስታይልና ፋሸን ቴክኖሎጂ ኢንስትዩት በሁለቱም ፆታዎች የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ የሆኑ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርቃት በዓል ላይ የኢትዮጵያ ቴከስታይልና ፋሸን ቴክኖሎጂ ኢንስትዩት በወንድም ሆነ በሴት የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ የሆኑት ተማሪ ሰላም ዋለ እና ተመሰገን ሁሴሳ ናቸው።
ሁለታችሁንም እነኳን ደሰ አላችሁ ውድ ተማሪዎቻችን!
3.0K viewsedited  14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 17:51:44 የጥሪ ማስታወቂያ
ለነባር PGDT ክረምት ተማሪዎች በሙሉ

https://t.me/bahir_dar_university
1.9K viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 06:15:11
3.7K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:21:03
4.9K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ