Get Mystery Box with random crypto!

Bahir Dar University,Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ bahir_dar_university — Bahir Dar University,Ethiopia B
የቴሌግራም ቻናል አርማ bahir_dar_university — Bahir Dar University,Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @bahir_dar_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.56K
የሰርጥ መግለጫ

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses!

www.bdu.edu.et

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-06 07:40:36 #አስደሳች_ዜና
==========
ከሀምሌ 19- 23/2015 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች
------------------------------------------

1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ህሙማን ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት የአግልግሎቱ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እንሳተላልፋለን::

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!

መረጃው የተገኘው ከጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

https://t.me/bahir_dar_university
12.6K views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 19:31:40
14.2K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 19:31:40 ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህፀን ካንሰር ሰብ-ስፔሻሊቲ ሀኪሞችን አስመረቀ *****የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ላለፉት ሁለት ተከታታይ አመታት በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ / gynecology oncology subspecialty / ከፍተኛ ትምህርት ያሰለጠናቸውን ሀኪሞች በዛሬው ዕለት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘን ጨምሮ የፍሪቦርግ ዩኒቨርሲቲ አለም አቀፍ ፕሮፌሰሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ በተገኙበት አስመርቋል፡፡ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የተሰጠውን ስልጠና አጠናቀው በዛሬው እለት ለምረቃ የበቁት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማሕፀን እና ፅንስ ስፔሻሊቲ ሐኪም የሆኑት ዶ/ር እያያ ምስጋን እና ዶ/ር ዳውድ ሙሐመድ ከሰኔ 20/2015 ዓ.ም ጀምሮ በማህፀን ካንሰር ህክምና ሰብ-ስፔሻሊቲ /gynecology oncology subspecialty/ በመሆን የምርቃት ሰርቲፊኬታቸውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትን ዶ/ር ፍሬው ተገኘ እና ከአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ እጅ ተቀብለዋል፡፡በስልጠናው አስተዋፆ ለነበራቸው ጀርመን ሐገር ለሚገኜው ሆፕ ፕሮጀክት እና ለኢትዮጵያ ማሕፀን እና ፅንስ ሐኪሞች ማሕበር ተወካይ ለሆኑት ለፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ለዶ/ር ታደሰ ኡርጌ የእውቅና ሰርፊኬት ከዶ/ር ፍሬው ተገኘ እጅ ወስደዋል፡፡በመጨረሻም የሁለቱ ተቋማት ተወካይ የሆኑት ፐሮፌሰር ክርስቶፍር ቶምሰን እና ዶ/ር ታደሰ ኡርጌ እንደሀገር የተያዙ ተመሳሳይ የስልጠና ቦታዎች መካከል የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጊዜው እና በሰዓቱ ሙያው በሚጠይቀው ልክ ስልጠናውን በስኬት ያጠናቀቀ ተቋም በመሆኑ ምስጋና አቅርበው የሰልጣኞች ተነሳሽነት እና የዩኒቨርሲቲውን ማኔጅመንት ለስልጠናው የነበራቸውን ቁርጠኝነት አመስግነው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት ለሚሰራቸው ማንኛውንም የጤናነክ ፕሮጀክቶች ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

https://t.me/bahir_dar_university
13.3K viewsedited  16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 19:31:40
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!
9.5K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 12:00:05
15.3K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 12:00:04
13.5K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 05:06:05
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
1.5K viewsedited  02:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 13:01:29 ለዩኒቨርሲቲው ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታማ የስራ ልማድ (Effective Work habit) ላይ ስልጠና ተሰጠ
ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ውጤታማ የስራ ልማድ (Effective Work habit) የተሰኘ የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ከመጋቢት 23-24/2015 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሁሉም ግቢ ለሚገኙ አካል ጉደተኛ ተመራቂዎች በፔዳ ግቢ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ለአካል ጉዳተኛ ተመራቂዎች ስልጠናውን ያዘጋጁት የዩኒቨርሲቲው የውጤታማ ትግበራ የስራ ክፍልና   ከፍታ ፕሮጀክት የተሰኘ ድርጅት በጋራ ሲሆኑ የዩኒቨርሲቲው የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክተር ዶ/ር ቀረብህ አስረስ የስልጠናው ዓላማ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲያውቁና ከሌሎች በተሻለ መልኩ ስራ ለማፈላለግ ብሎም ከቀጣሪ ድርጅቶች ጋር በቀላሉ ተግባብተው ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ  ታልሞ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ቀረብህ በማስከተል ተማሪዎች ከፅንሰ ሃሳቡ ትምህርት ጋር ይህ ስልጠና ተግባር ተኮር በሆነ መልኩ መሰጠቱ ከትምህርቱ ዓለም ወደ ስራው ሲቀላቀሉ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በቀላሉ እንዲተገብሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በዘንዘልማ ግቢ ለሚሰለጥኑት ተመራቂዎች የስልጠናውን ጠቀሜታ ያስገነዘቡት የዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ወርቁ አበበ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ከቅበላ እስከ ምረቃ ድረስ ተገቢውን እውቀት እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን አውስተው ተመርቀው ከወጡ በኋላም ወደ ስራው ዓለም በቀላሉ ለመቀላቀል ግንዛቤ ያገኙ ዘንድ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ወርቁ አክለውም ስልጠናው ከሌሎች ስልጠናዎች ለየት ያለና ተመራቂዎች በቀላሉ ስራ ለማፈላለግ የሚያግዝ ስልጠና በመሆኑ ለዘንዘለልማ ግቢ ተማሪዎች ቅድሚያ ቢሰጥም የመማር ማስተማሩን መርሃ ግብር በማይነካ መልኩ ለሁሉም ተመራቂዎች ስልጠናው ተደራሽ እንደሚሆን አስገንዝበው ተማሪዎች በነቃ ተሳትፎ ስልጠናውን እንዲከታተሉ አስገንዝበዋል፡፡
https://t.me/bahir_dar_university
2.5K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 14:57:12 ኑ!ኑ!ኑ!

Reunion Weekend: Are you a former graduate of #Peda, #Poly or #BDU?
Have you missed your dormmates and campus friends; your former instructors and services providers; the lounge and cafe; classrooms, library, laboratory and workshops? TV rooms and cultural center (Auditorium); the palm and canopy streets and gardens; sport courts and intramural tournaments? Bahir Dar city, views of Abay and Tana?

Then, come and refresh your campus memories on the special occasion of Poly-Peda-BDU students' reunion weekend in the closing days of BDU'S 60th anniversary.

Date June 10 & 11, 2023 ( Sene 3& 4, 2015 E.C)

https://t.me/bahir_dar_university
2.0K viewsedited  11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 16:26:49
2.1K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ