Get Mystery Box with random crypto!

አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም

የቴሌግራም ቻናል አርማ askignkeldoch — አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም
የቴሌግራም ቻናል አርማ askignkeldoch — አስቂኝ ቀልዶችና ሌሎችም
የሰርጥ አድራሻ: @askignkeldoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.68K
የሰርጥ መግለጫ

ያፈቀረን ማሳቅ ለኛ ኖርማል ነው አያሳስብም😉
#Join ያርጉና የትም
ባልተሰሙ ቀልዶቻችን ፈታ እያሉ በውብ የፍቅር ቃላቶች ይደመሙ😍
ዘፈን ግጥም ጠቃሚ ምክሮች...
ከቻልክ❤️ ፍቅርን ተናገር፣ኑር!
ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉 @Get_mu 👉 @just_811
Please😊Don't Leave ችግር ካለ አናግሩን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 22:20:42 #እራስህን_ሁን
በአንድ መንደር የሚኖር አንድ ድንጋይ ጠራቢ ነበር ንጉሱ ነዋሪዎችን ሁሉ እራት ይጠሩና ወደዚያ ይሄዳል በር ላይ የነበሩትም ጥበቃዎች ሀብታሞችን እያስገቡ እሱን ግን ንቀውት አናስገባም ብለው ይከለክሉታል ወደቤቱም ተመልሶ በኑሮው በጣም ይማረርና ምን አለ ንጉስ ብታረገኝ ድንጋይ ጠራቢ ከምታረገኝ እያለ ፀሎት ቤቱ ገብቶ እያነባ ፈጣሪን ሲያማርር አመሸ ይደክመውና እንቅልፍ ይወስደዋል ወዲያውም ህልም ማለም ጀመረ በህልሙም ንጉስ ይሆንና ህዝቡን ሰላም እያለ ሲሂድ ፀሀይዋ ታቃጥለዋለች ወዲያውም ምን አለ ፀሀይ ብታረገኝ አለ ፀሀይም ሆነና ማብራት ጀመረ ከዛ ደመና መቶ ጋረደው ምን አለ ደመና ብታረኝ አለ ደመናም ሆኖ መዝነብ ጀመረ ከዛም ሲዘንብ ዛፎች ሁሉ ዝቅ ሲሉና ወዲ ወዲያ ሲወዛወዙ አንድ ቋጥኝ ግን ምንም ሳይነቃነቅ አየ ከዛም ምን አለ ቋጥኝ ብታደርገኝ አለ ቋጥኝም ሆነ አንድ ጠራቢም መጥቶ ሲጠርበው በጣም ያመውና ወዲያውኑ ምን አለበት #ጠራቢ ብታረገኝ አለ ጠራቢም አረገው ወደራሱም ተመልሶ ከእንቅልፉ ነቃ ወደ ልቡም ተመለሰ ፈጣሪውንም አመሰገነ ይባላል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን እራሳችንን ሳይሆን ሌላ ሰውን ለመሆን ምንሞክር ? አለም አሁን ያለችበትን ቅርፅ ያሲያዟት እኮ እራሳቸውን የሆኑ ሰዎች ናቸው እስቲ አስቡት ሶቅራጠስ እራሱን ባይሆን ኖሮ ፍልስፍናን ከተሰቀለችበት ማን ያወርዳት ነበር ? አዲስ አለማየው ኳስ ተጫዋች ለመሆን ቢሞክሩ ኖሮ እነ ፍቅር እሰከ መቃብርን የት እናገኛቸው ነበር ? ሮናልዶና መሲ አትሌት ለመሆን ቢሞክሩ ኖሮ እነዛን የኳስ ጥበቦች የት እናያቸው ነበር ? ዳቬንቺ ገጣሚ ለመሆን ቢሞክር ኖሮ ሞናሊዛን ማን ይስልልን ነበር ? አልበርት አን አንስታይን ሙዚቀኛ ለመሆን ቢሞክር ኖሮ እነዛን የፊዚክስ ፎርሙላዎች ማን ያገኛቸው ነበር ? እኚ ሁሉ እራሳቸውን ስለሆኑ ነው ከኖሩበት ዘመን አልፈው እኛም ምናስባቸው ሁላችንም የራሳችን የሆነ ውብ ማንነትና ለዚችም አለም ምናበረክተው ነገር አለ እሱን መፈለግና መሆን ለአለምም አውጥቶ ማበርከት ያስፈልጋል ሁላችንም እራሳችንን ስንሆን ፈጣሪም ከላይ ወደታች ሲመለከት የሚያምር ህብረ ቀለም ይመለከታል እኛ ሌላ ሰውን ለመሆን ስንሞክር የኛ ቦታ ባዶ ይሆናል አለም ላይም ክፍተት ይፈጠራል ስለዚህ Be your self. እራስህን ሁን
558 views...typing, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 22:19:34 ETHIOPIA(ኢትዮጵያ)

➊ በአፍሪካ በቀኝ ግዛት ያልተገዛች ብቻኛ ሀገር ናት።
➋ ከሌሎች በተለየ አስራ ሶስት ወር ያላት ሀገር ናት።
➌ ከ80 በላይ ቋንቋ ይነገርባታል።
➍ የቡና ተክል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
➎ 13 ቅርሶችን በ UNESCO በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚ ናት።
➏ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው መርካቶ የፍሪካ ትልቁ የገበያ ማእከል ነው።
➐ በአሁጉራችን በህዝብ ብዛት ናይጄሪያን በመከተል ሁለተኛውን ስፍራ ይዛለች።
➑ በዓለማችን የባህር ወደብ ከሌላቸው ሀገራት በህዝብ ብዛት ቀዳሚ ናት።
➒ በአፍሪካ የራሷ ፊደልና ቁጥር ያላት ብቸኛዋ ሀገር ናት።
➓ በዓለማችን ብዙ ርቀት በመጓዝ ቀዳሚ የሆነው የአባይ ወንዝ መነሻ ናት።
➊➊ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ናት።
➊➋ ከ200 በላይ የቋንቋ ዘዬ ይነገርባታል።
➊➌ የሀገሪቷ ሰም በመጽሐፍ ቅዱስ(42+)ና በቁራን በርካታ ጊዜ ተጠቅሷል።
➊➍ በአፍሪካ የመጀመሪያው የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያስገኘው ኢትዮጵያዊው አበበ በቂላ ነው።
➊➎ ከሌሎች ሀገራት የተለየ የሰዓት እና የካላንደር አቆጣጠር አላት።
➊➏ ከአርመንያ በመቀጠል ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖቴ ነው ብላ የተቀበለች ሁለተኛዋ ሀገር ናት።
➊➐ በአፍርካ የመጀመሪያው መስጊድ መገኛ ናት።
➊➑ በቀንድ ከብት ብዛት ከአሁጉራችን ቀዳሚናት።
➊➒ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የቀኝ ክፍሉ የሚገኝባት ሀገር ናት።
➋0 በኢትዮጵያ ውስጥ 924 የአእዋፍ ዝርያ ያሉ ሲሆን 23 ያህሉ በሌላ ዓለማት የማይገኙ ናቸው።

@askignkeldoch
1.7K views...typing, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:17:05 May be such story gives you a littel bit self worth and self understanding.
በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር።
ይህ ሰው ውሀ ከወንዝ እየቀዳ ቤተ-መንግስት ዘወትር ያመላልስ ነበር። ውሀ የሚያመላልስባቸው ሁለት እንስራዎችም ነበሩት በነዚህ እንስራዎች
ውሀ እየሞላ ወደ ቤተመንግስት ይውስድባቸው ነበር። ከሁለቱ እንስራዎች አንዱ ግን ቀዳዳ ነበረው፤ እና ምንም እንኳን ከወንዙ ሁለቱንም እኩል
ውሀ ሞልቷቸው ቢሄድም ቤተመንግስት ሲደርስ ግን አንደኛው እንስራ ሙሉ፤
ቀዳዳ ያለበት እንስራ ደግሞ ጎዶሎ ይሆን ነበር። በዚህ ሁኔታ ሰውዬው
በሁለቱ እንስራዎች አንድ ሙሉ እንስራ ውሀ፤ በሌላኛው ደግሞ ጎዶሎ ውሀ
እያመላለሰ ለረጅም ጊዚያት ቆየ።

ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ ቀዳዳ ያለበት እና ዘወትር እያንጠባጠበ የሚሄደው
እንስራ እንዲህ ሲል ለሰውዬው አቤቱታ አቀረበ፡፡

እንስራው፦ "እኔን እና ጓደኛዬን እየተሸከምክ ውሀ ማመላለስ ከጀመርክ እንሆ ቆየህ።
ሰባራ ሆኜም እንኳን ስታመላልስብኝ ሰነበትክ አሁን ግን ዘወትር ከጌታዬ ፊት
ጎዶሎ ውሀ እየያዝኩኝ መቅረብ አሳፈረኝ። ጓደኛዬ ዘወትር ሙሉ ውሀ ሲወስድ እኔ ግን ሁሌ ጎዶሎ ማቅረቡ አንገቴን አስደፈኝ። እናም በኔ ውሀ ማመላለሱ ቢበቃህ ይሻላል።" አለው። ይህን የእንስራውን አሳዛኝ ንግግር የሰማው ሰውዬ በማስተዋል ቀዳዳውን
እንስራ እየተመለከተ፡-

ሰውዬው፦ "ዛሬ ውሀ ቀድተን ስንመለስ አንድ ነገር አሳይሀልሁ" ሲል ነገረው።

ውሀ ቀድተው ሲመለሱ ሰውዬው የሚያንጠባጥበውን እንስራ ወደ መሬት
እያስተዋለ እንዲሄድ ነገረው። እንስራውም እንደተባለው አደረገ።

በእሱ በኩል እጽዋቶችን ተመለከተ ፍሬ ያፈሩ አትክልቶችን አስተዋለ
የሚያማምሩ አበባዎችን አየ። በዛኛው እንስራ በኩል ግን ምንም አልነበረም።

ምንም እንኳን ዘወትር በተመሳሳይ መንገድ ቢሄዱም እንደዛሬው አስተውሎ
አያውቅም ነበር።

ሰውዬው፦ "አየህ ወደጄ አንተ እንደምታንጠባጥብ ሳውቅ ባንተ በኩል ዘሮችን ዘራሁ፤ ዘወትር ካንተ በሚንጠባጠበው ውሀ ጥማታቸውን አራሱ፣ ፍሬ አፈሩ፣ አበቡም። ይህ የምትመለከተው አትክልት ሁላ ባንተ በኩል ብቻ ነው ያለው ሌላኛውን
እንስራ በምሸከምበት በኩል ምንም ነገር የለም እናም ጥቅም የለኝም አትበል።
ሌላው ቢቀር ደካማ ጎንህ እንኳን ለሌሎች ጥቅም አለው" ሲል አስረዳው።


*አንዳንዴ ልዩነታችንን አይተን፤ በንጽጽር ብቻ ጥቅም የለኝም እርባና ቢስ ነኝ
ብለን እናስብ ይሆናል። ሌላው ሰው የቻለውን እኛ ባለመቻላችን ብቻ ጎዶሎ እንደሆንን እናስባለን።

*ሰባራው እንስራ ሌላኛው እንስራ ሙሉ ውሀ መውሰዱን ተመለከተ እንጂ በሱ ውሀ ስንት የእጽዋት ነፍስ እንደበቀለ አላስተዋለም።

*እኛም እንዲህ ነን የየራሳችን ብርሀን አለን ነገር ግን የሌላው ሰው ጭላንጭል ያስቀናናል።

*የኛ ቀዳዳ የሌላውን ጉድለት እየሞላ ይሆናል

*ሌሎች ሙሉ ውሀ መሸከም ቢችሉ እንዳንተ ነፍስ መዝራት አይችሉም። አንተ
እንደነሱ ሙሉ ውሀ መሸከም ቢያቅትህ ጉድለትህ ሌሎች እንዲያብቡ ያደርጋል።
2.1K views...typing, 11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 22:45:04 #እመን
አንድ የተነፉ ፊኞችን በመሸጥ የሚተዳደር ሰው ነበር። ገበያ ሲቀዘቅዝበትም ፊኞችን እየነፉ ወደ ላይ ይለቃቸዋል ። ልጆችም ያንን ሲያዩ መጥተው ይገዙታል ። ይህንን ተግባሩን ከሩቅ ሆኖ ሲመለከት የነበረ አንድ ህፃንም ወደሱ ቀረብ ብሎ ጥቁር ፊኛም እንደነሱ በአየር ላይ መንሳፈፍ ይችላል ? ብሎ ጠየቀው ። ሰውዬውም ማሙሽዬ ፊኞቹ በአየር ላይ እንዲንሳፈፉ የሚያደርጋቸው እኮ ቀለማቸው አይደለም ። በውስጣቸው ያለው አየር ነው አለው ። እኛንም በህይወት ላይ በኑራችን በስራችን በምናደርጋቸው ነገሮች ላይ በስኬትና በአሸናፊነት እንድንንሳፈፍ የሚያደርገን ውስጣችንን የሞላው እምነታችንና አመለካከት ነው። መልካም ነገሮች ሁሉ ይገቡኛል ። ጥሩ ስራ ጥሩ ፍቅረኛ መልካም ትዳር ይገቡኛል የሚል እምነት ያስፈልገናል። መፅሀፉስ ቢሆን " አለምን የሚያሸንፈው እምነታችን ነው " ፣ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አይደል የሚለው ። ወዳጄ አንተ ሰዎች ነህ የሚሉህንም አይደለህም በቃ አንተ ማለት ፈጣሪ ነህ ያለህን ነህ ። ፈጣሪ ለትልቅ ነገር እንደ ፈጠረህ እመን። እኔ አልረባም ዋጋ የለኝም አትበል ። የደም ዋጋ ተከፍሎልሀል። ብኖር ባልኖር ማልጠቅም ሰው ነኝ አትበል ። 1 ጄኔራል ታንከኛ በሚያስፈልግበት ቦታ ላይ እግረኛ ልኮ ወታደሮቹን አያስፈጃቸውም ። ከጀነራል በላይ ሚያስበው ፈጣሪም በማታስፈልግበት ጊዜ ላይ አምጥቶ አያስፈጅህም። አንተ አሁን የተፈጠርከው አንተ የምታስፈልግበት ጊዜ አሁን ስለሆነ ነው በፈጣሪህ እምነት ይኑርህ ። በራስህ ተማመን ። ለትልቅ ህይወት እንደ ተፈጠርክ አስብ ። ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ እስከ ሞት የወደን አምላክ አለን። እመን መልካም ነገሮች ሁሉ ይገቡሃል ።



share, invite and join
@askignkeldoch
2.4K views...typing, 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:05:58 ሁለቱ ሕጎች

“የውሸተኛ ቅጣቱ በሰዎች ያለመታመን ብቻ አይደለም፣ ከዚያ የከፋው ቅጣቱ እርሱ ራሱ ማንንም ለማመን አለመቻሉ ነው” - George Bernard Shaw

አንዳንድ ሰዎች መልካምና ጨዋ የሚሆኑት ካላቸው ጨዋ ማንነት ወይም የመልካም ስነ-ምግባር ዲሲፕሊን ተነስተው ሳይሆን ቅጣት ስሚፈሩ ብቻ ነው፡፡ ይህ ጠባብ አመለካከት ወደተበላሸ ማንነት እንድንወርድ የሚዳርግ አመለካከት ነው፡፡ ከአንድ ትክክል ካልሆነ ነገር መቆጠብ የሚገባን ዋና ምክንያት፣ ነገሩ ትክክል ስላልሆነና ጎጂ ስለሆነ ሊሆን ሲገባው፣ ለጊዜው ከቅጣት ለማምለጥ ወይም ጊዜያዊ ጥቅምን ለማግኘት ከሆነ ሁኔታው የማንነትን ብልሹነት አመልካች ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ማንኛውም ክፉ ተግባራችን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከቅጣት አያመልጥም፡፡

በአለም ላይ ሁለት አይነት ሕጎች አንዳሉ በማሰብ መጀመር እችላለን፡፡ አንዱን ሕግ “የተፈጥሮ ሕግ” በማለት መሰየም ስንችል፣ ሁለተኛውን ሕግ ደግሞ “ሰው-ሰራሽ” ሕግ በማለት ልንሰይመው እንችላለን፡፡ ማንኛውም ተግባራችን ከእነዚህ ከሁለቱ ሕጎች በአንዱ ከመዳኘት በፍጹም አያመልጥም፡፡

“ሰው-ሰራሽ” ብለን የሰየምነው ሕግ አንድ የተከለከለ ነገር አድርገን ስንያዝ በተደነገገው ሰው-ሰራሽ ሕግ መሰረት ስንዳኝና ስንቀጣ ማለት ነው፡፡ “የተፈጥሮ ሕግ” ብለን የሰየምነው ደግሞ ምንም እንኳ ለጊዜው ከሰው-ሰራሽ ሕግ የምናመልጥበትን መንገድ ብናመቻች የሰራነው ስራ ቀስ በቀስ ዘሩ በቅሎ ሊቀጣን የመቻሉ ሁኔታ ነው፡፡
የምናደርጋቸውንም ሆነ ከማድረግ የምንገታባቸውን ነገሮች በሙሉ ከእነዚህ ሁለት ሕጎች አንጻር ብንመለከታቸው አመለካከታችንን የማስፋት ጠቀሜታ አለው፡፡

የምናደርጋቸውና ከማድረግ የምንገታቸው ክፉም ሆኑ ደግ ተግባሮቻችን የሚዳኙት በሁለት ሕጎች መሆኑን መገንዘብ የአመለካከት ዘይቤአችንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የመቀየር ጉልበት አለው፡፡ ዛሬ የማደርገውም ሆነ የምናገረው ጤና-ቢስ ነገር እጅ በእጅ ባይቀጣኝም ፈጠነም ዘገየም ፍሬው በቅሎ ጭማቂውን እንደምጎነጨው ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡

እያንዳንዱ ተግባሬ እንደዘር ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ዛሬ አንድ መልካም ነገር ማድረግ እንደሚገባኝ እያወኩኝ ምንም እንኳን ማድረግ ባልፈልግና እጅ-በእጅ የሚከፈለኝ ዋጋ እንደሌለ ባስብም፣ በውስጤ ካለው መርህ የተነሳ በማድረጌ ምክንያት ነገ የሚበቅለውን ጣፋጭ ፍሬ መመገቤ አይቀርም፡፡ ይህ በፍጹም ሊሻር የማይችል ዘላቂ ሕግ ነው፡፡ ወይ እንተባበረዋለን፣ ወይም ደግሞ በተቃራኒው ሄደን የማንፈልገውን ውጤት ስንቀበል እንኖራለን፡፡ ምርጫው የእኛው ነው፡፡

ለህሊና እንኑር … ለሕዝብ እንኑር … ለመልካምነት እንኑር !

@askignkeldoch
3.0K views...typing, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 18:35:06 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደረችሁ

ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡

ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፤ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን።

በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤ የሚገባበትን አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤ በቃ መጥፎ ዜናውን ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።

በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።

አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው።

#NB በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል። እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!

መልካም ቀን
3.1K views...typing, 15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 11:18:10 አሉታዊ ነህ ወይስ አዎንታዊ ?

አሉታዊ ስህተትን ይፈላልጋል ፤ አዎንታዊ መፍትሄን ያገኛል ፡፡ አሉታዊ ከንፈር የሚመጥለት ሰው ይፈልጋል ፤ አዎንታዊ መፍትሄን ይፈልጋል ፡፡ አሉታዊ በሰዎችና በሁኔታዎች ሲፈርድ ይታያል ፤ አዎንታዊ ሁኔታዎችንና ሰዎችን ለመቀየር ራሱን ያቀርባል ፡፡ አሉታዊ በእጁ ላይ ስላለው ጥቂት ፍሬ ሲነጫነጭ ይታያል ፤ አዎንታዊ ተነስቶ ይዘራዋል ፡፡

አሉታዊ በፊቱ መከራና ውድቀት እንዳለ ያስባል ፤ አዎንታዊ የስኬት ዘመንን ወደ መኖር ለማምጣት ይሰራል ፡፡ አንድ ሰው አሉታዊውን አመለካከት በመጣል ወደ አዎንታዊው ለመዝለቅ ራሱ ማስለመድና አመለካከቱን ንድፍ መቀየር የግድ ነው ፡፡ አዎንታዊን ዝንባሌ ያዳበሩ ሰዎች እይታዎቻቸው አስገራሚና ለስኬት አመቺ ናቸው ፡፡ የሚከተሉትን የአዎንታዊ ሰዎች አመለካከት እንመልከት ፡፡

የዛሬ አለመሳካት ዘላቂ እንዳልሆነ ማወቅ “ጸሃይ የጠለቀችው በአዲስ ሁኔታ ልትወጣልኝ ነው” - Robert Browning ፡፡ በአዎንታዊ አመለካከት የተሞላ ሰው እይታው ይህ ነው ፡- የጠለቀ እንደገና ይወጣል ፤ የወደቀ እንደገና ይነሳል ፤ የጠፋ እንደገና ይገኛል ፤ የተበላሸ እንደገና ይታደሳል ፡፡

ነገሮች ከዚህ የከፉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ “ሁል ጊዜ የተበላሸውንና የጠፋውን ሳይሆን የተረፈውን አስብ” - Robert H. Schuller ፡፡ አዎንታዊ ሰው ነገሮች ተበላሽተው እያሉ እንዳልተበላሹ ለማስመሰል አይኑን አይጨፍንም ፡፡ በምትኩ እውነታውን ለመጋፈጥ አይኑን ይከፍታል ፣ የሚያተኩረው ግን የተበላሸው ላይ ሳይሆን የተረፈው ላይ ነው ፡፡

በስሜትና በጊዜአዊ ግምት አለመመራት “ነገ ዓለም ያከትምላታል ብባልም እንኳ ዘርን ከመዝራት አልመለስም” - Martin Luther ፡፡ ለአዎንታዊ ሰው ነገር የሚያከትምለት በርግጥም ሲያከትምለት ብቻ ነው ፡፡ እስከዚያው ድረስ እንደሚሳካ ፣ ሁኔታዎች እንደሚለወጡና ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ከማሰብ አያቆምም ፡፡ በአሉባልታና ለጊዜው በተናፈሰ መረጃ-ቢስ ወሬ አደራረጉን አይለውጥም ፣ ወደ ፊትም ከመገስገስ አይገታም ፡፡

የስህተትን አይቀሬነት መቀበል “አብዛኛዎቹ እርሳሶች ለመጻፊያ ሰባት ኢንች ርዝመት ሲኖራቸው ለማጥፊያ ደግሞ ግማሽ ኢንች ላጲስ አላቸው - አዎንታዊ አመለካከት” - Robert Brault ፡፡ ከአንድ እርሳስ ጋር አብሮ ማጥፊያ ላጲስን መስራት የአዎንታዊ ሰው እይታ እንጂ የአሉታዊ አይደለም ፡፡ አዎንታዊ ሰው ነገሮች እንደተጀመሩ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ያውቃል ፡፡ ከዚህ እውቀቱ ጋር ግን የተበላሹ ነገሮች ሊሰረዙና ሊሻሻሉ እንደሚችሉ ጽኑ እምነት አለው ፡፡
═════════❁✿❁ ═════════
3.3K views...typing, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:16:15 ስኬታማ ለመሆን በመጀመሪያ እመን ...ድፈር.. .ከዚያም ተለወጥ...ተራመድ..በመጨረሻም ተማመን... አስተውል...!

እመን፦ ነገር ለበጎ መሆኑን ተቀበል እና ከእያንዳንዱ የህይወትህ ገጠመኝ የሚበጅህን ከውን።

ድፈር፦ ከለመድከው የምቾት ቀጠና (Comfort Zone) ለቀህ ለመውጣት አታቅማማ፣ ይልቁንስ አዳዲስ ነገሮችን ሞክር።

ተለወጥ፦ የለውጥ ጉጉት ይኑርህ፣ ፈተናዎችን በፀጋ የመቀበል ልማድን ፍጠር።

ተራመድ፦ ወደፊት እንጂ ወደኋላ በጭራሽ እንድትጓዝ፣ ከትላንትህ ትምህርት ወስደህ ዛሬ ላይ ለነገ አላማህ የሚጠቅምህን ፈፅም።

ተማመን፦ በራስህ እና በችሎታህ ተማመን እናም ተአምራቶች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ ትመለከታለህ።

አስተውል፦ ፍቅር፣ ፀጋ እና በረከት ብዙሪያህ እንንዳለ እንዳትዘነጋ።

ወደ ፊት!

#ጥበብ እና #ማስተዋል ለሰው ልጅ በሙሉ!
-ሣሙኤል ተክለየሱስ
(የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
========================
ሙዳዬ ንዋይ - የቢዝነስ ልህቀት
3.7K views...typing, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:19:45
እህቴ የጎዳኝ ሰው በይቅርታው ያድነኛል ብለሽ አትጠብቂ!

ይልቅስ አንቺ ይቅር በማለትሽ ለሌላ ሰው ሳይሆን ለአንቺ ለራስሽ ከበቀል ደዌ ፈውስ ታገኛለሽ ።

የይቅርታው ንጉስ ኔልሰን ማንዴላ (Madiba) እንዲህ ይላሉ...."በቀል ማለት መርዙን እራስ ጠጥቶ ሌሎች እንዲሞቱ የመጠበቅ ሞኝነት ነው።"

ስለሆነም ይቅርታሽ በውስጥሽ ካለው የበቀል መርዝ ያሽርሻል።

ለዚህም ነው #ይቅርታ 'የአለም ውዱ ስጦታ ነው' የሚባለው!

ልብ አድርጊ ይህን ውድ ስጦታ የምትሰጪው ለጎዳሽ፣ ላሳመመሽ፣ ላስለቀሰሽ፣ ላወረደሽ...በጥቅሉ ለማይገባው ሰው ነው።

ለምን ቢባል ደግሞ በይቅርታው ስጦታ አንቺ ከህመምሽ ስለምትፈወሺ ነው !

እህቴ እዚህ ጋር አንድ ነገር እንዳትረሺ.....

በይቅርታሽ ከባለፈው ትምህርት ትወስጃለሽ እንጂ የጎዳሽን ሰው ወደ ህይወትሽ እንደገና እንዲመልስ ትፈቅጅለታለሽ ማለት ግን አይደለም።

እርምጃሽ በማስተዋል ይሁን!

#ጥበብ እና #ማስተዋል ለሰው ልጅ በሙሉ!
-ሣሙኤል ተክለየሱስ
(የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
========================
ሙዳዬ ንዋይ - የቢዝነስ ልህቀት
3.5K views...typing, 09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 15:48:11 Live stream started
12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ