2022-07-10 15:21:43
ከጠቀማችሁ!
፩) ለአንድ ሰው ከሁለቴ በላይ አይደውሉ። ምናልባት የማያነሱ ከሆነ ወይ አላዩትም፣ ወይ ለማንሳት የሚመች ቦታ አይደሉም፣ ወይ ደግሞ ማንሳት አልፈለጉም። ስለዚህ መልሰው እስኪደውልሎት ይጠብቁ።
፪) የተበደራችሁትን ገንዘብ አዳሪው ከማስታወሱ ወይም ከመጠየቁ በፊት ይመልሱ። ይሄ የታማኘነታችሁ ወይም የመልካም ስብዕናችሁ መገለጫ ነው። ምናልባት ምልሰቱ ከእስክሪብቶ፣ ከእስርሳስ ሊጀምር ይችላል።
፫) አንድ ሰው ሆቴል ሲጋብዛችሁ ውድ ምግቦችን እና መጠጦችን ከማዘዝ ይቆጠቡ። ምክንያቱም ያስገምታችኋል።
፬) "እስካሁን ለምን አላገባህ/ሽም፤ ልጆች ለምን አልወለድክ/ሽም፤ አይነት በጣም ደባሪ ጥያቄዎችን አይጠይቁ። በፈጣሪ ስም! ይሄ የእናንተ ችግር አይደለም።
፭) ከኋላችሁ የሚመጣ ሰው ካለ ሁሌም በሩን ከፍታችሁ አስገቡት። ሴት ትሁን ወንድ፤ ታላቅ ይሁን ታናሽ ማተር አያደርግም። ሰዎችን በማክበር እናንተ አትዋረዱም።
፮) ጓደኛችሁ ዛሬ የታክሲ ከከፈለ፣ ነገ እናንተ ለመክፈል ሞክሩ።
፯) ልዩነቶችን ያክብሩ። ለእናንተ 6 ቁጥር የመሰለው ለሌላው 9 ቁጥር ሊመስል ይችላልና ሐሳቡን እንደተቀናቃኝ ሳይሆን እንደአማራጭ ይውሰዱት።
፰) የሰዎችን ንግግር አያቋርጡ። እስኪጨርሱ በሚገባ አድምጠው የእርሶን ይቀጥሉ።
፱) ሰው ላይ አፊዘው ደስተኛ ካልመሰለ በድጋሚ እንዳትቀልዱባቸው። ምክንያቱም የእርሶ ሽንቁር ሌላውን ለማስገብት ትሞክራለች።
፲) በማንኛውም ነገር እርዳታ ስታገኙ "አመሰግናለሁ" ማለትን ይልመዱ።
፲፩) ሰውን በሕዝብ ፊት ያወድሱ፣ ለብቻ ይገስፁ።
፲፪) የሰው መልክ፣ ቁመና፣ ፀባይ፣ ውፍረት… ላይ ምንም አስተያየት የመስጠት በቂ ምክንያት የላችሁም። የምትሏቸው ነገር ቢኖር "ውብ ናችሁ" ብቻ ነው። የምትናገሩት መልካም ካልሆነ ግን ዝምታን ይልመዱ።
፲፫) ሰዎች አንድ ፎቶ ብቻ ሊያሳዯችሁ ፈልገው ስልካቸውን ከሰጧችሁ ወደፊት፣ ወደኋላ አያድርጉ። ምክንያቱም ቀጣዩ ምን እንደሆነ አታውቁም።
፲፬) ጓደኛችሁ የሕክምና ቀጠሮ እንዳላቸው ከነገሯችሁ ምን እንደሆነ በፍፁም እንዳትጠይቋቸው። "እንደሚሻልህ/ሽ ተስፋ አደርጋለው" ብቻ ይበሉ። የጤና እክላቸውን ተናግረው የሚረብሽ ኹኔታ ውስጥ እንዳትከቷቸው ተጠንቀቁ። እነሱ መንገር ከፈለጉ ያለናንተ ጥያቄ ይነግሯችኋል።
፲፭) ለዶክተር፣ ለባለስልጣን፣ ለባለፀጋ ክብር በምትሰጡት ልክ ለፅዳት ሰራተኛም፣ ለተራው ዜጋም፣ ለነዳዲያንም ስጡ። ሰውን መናቅ ብልግናችሁን ቢሆን እንጂ ሌላ ምንም አያሳይም። ሁሉንም ሰው በእኩል አይን ማክብር ትልቅነት ነው።
፲፮) ሰዎች ፊት ለፊት እየተመለከቱ ሲያናግሯችሁ ሞባይል፣ ኮምፒተር ወይም መጻሕፍትም ቢሆኑ ተተክላችሁ አትመልሱ። ተገቢ አይደለም። በወቅቱ ቀዳሚው መሆን የሚገባው ሰዎቹ እንጂ ቁስ አይደለም።
፲፯) ከረጅም ጊዜ በኋላ ጓደኛችሁን ወይም ወዳጃችሁን ካገኟችኋቸው እነሱ ለመናገር ካልፈቀዱ በስቀር ስለኑሯቸው፣ ስለሕይወታቸው ከመጠየቅ ተቆጠቡ።
፲፰) በቀጥታ የካልተመለከታችሁ በስተቀር በማያገባችሁ ጉዳይ አትግቡ።
፲፱) ሰዎች እመንገድ ሲያናግሯችሁ የአክብሮት ምልክት በመሆኑ የፀሐይ መነፅራችሁን የማውለቅ ልምድ ይኑራችሁ። ከቃላት እኩል የአይን ግንኙነት ጠቃሚ ነው።
፳) ስለባለፀግነታችሁ በነዳዲያን ፊት ከመለፍለፍ ይቆጠቡ። በተመሳሳይ ስለልጆች በመሃኖች ፊት አያንሱ።
፳፩) ካልተጠየቃችሁ በስተቀር ለማንም ምክር ለመስጠት እትሞክሩ። "ባንተው ምክር ሄጄ፣ ባንተው አስጨከነኝ" እንዳለው ድምፃዊው አንተስ ምን እያደረክ ነው ካላችሁኝ ምናልባት ይሄ በጥቆማ ደረጃ ከተወሰደ ቢሆን እንጂ ምክር መሆን የሚችል አይመስለኝም።
2.8K views...typing, 12:21